Sunday 9 February 2020

ው ዕፅዋት መልካም ናቸው አንዳንድ ዕፅዋት ግን ዛር ሊያድርባቸው ይችላል ፡፡ እናም አንዳንድ ዕፅዋቶች የዚህ የሚያፈዙ ዛሮች ያደሩባቸው አሉ እና ሲዋረሱት ዶሮ ያርዱለታል አረቄ ይቀቡታል 7 ቀን ወይም 40 ቀን ልክ እንደፈጣሪያቸው ይሰግዱለታል ከዛ በኋላ ያዛር ለዚ ሰው የማፍዘዝ ስልጣን ይሰጠዋል ሰወችንም ያፈዝለታል፡፡ ሌላ ደግሞ የተለያዩ የዛር ህቡዕ ስሞችን እየጠሩ ለወንዝ ሰግደው ስሙን ተዋርሰው ሰው የሚያፈዙም አሉ፡፡
ባጠቃላይ ሌቦች የሚሰሩት አፍዝዝ አደንግዝ ባብዛኛው እንደዚህ ከጥበብ የወጣ ነው፡፡
ታዲያ ወደመፍትሔው ስመጣ ከዚህ ምስሉ ላይ የምታዩትን ጥበብ ከብራና የሰለሞን መፅሐፍ ላይ ነው ያገኘሁት እና ጥበቡ ምንድነው አሰራሩ ፡ -
1፡ ድጋሙን በቀጭን ሸንበቆ(ቀስም) ፳፩(21) ጊዜ ደግማቹህ በጥቁር ሐር ጠምጥማቹህ በኪስ መያዝ ነው፡፡ከዛ በየ 7 ቀኑ በቃል መድገም ነው፡፡
2 ፡ ድጋሙን በዕለት በዕለት 7 7 ጊዜ ብትደግሙትም ሌባ አፍዝዞ አይሰርቃችሁም፡፡እርግጠኛ ነኝ፡፡
3 ፡ ድንገት ሌባ ሌላ ሰው አፍዝዞ ሲሰርቅ ካያቹህ ሄዳቹህ በቀኝ ጎኑ ቁማቹህ 3 ጊዜ ብትደግሙት ሌባው ያፈዘዘው ሰው ይነቃል ከመሰረቅ አዳናችሁት ማለት ነው፡፡ ይህንን ራሴም ሞክሬዋለው፡፡
በየትኘውም እምነት ያላቹህ ሰዎች ወንዶችም ሴቶችም ይህንን መጠቀም ትችላላቹህ፡፡
ጥበቡ ጉዳት የለውም ምንም አይነት የውርሻ ቃል የለውም፡፡
በሸንበቆ የምትሰሩት ከሆነ ግን በየ 41 ቀን በእሳት ሸንበቆውን ለብልበው ጥበቡ በእጥፍ ይታደሳል ይለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment