Tuesday 11 February 2020

ሊቁ ኤራቅሊስ ይህንን ጉዳይ አስረግጦ ሲናገር "ሰው በሆነበት ግብር ሊቀ ካህናት ነው፡፡" ሃይማኖተ አበው 49:39 ሊቁ ቄርሎስም "ሰው በመሆኑ ሊቀ ካህናት ሆነ፡፡" 79:14 

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው በሆነበት ግብር ሊቀ ካህናት የተባለው እጠቀም ብሎ አይደለም፡፡ እኛን በአገልግሎቱ ያድነን ያጣናትን ልጅነት ይመልስልን ዘንድ እንጂ ሰው በመሆኑ ከእግዚአብሔርነት የተለየም አይደለም በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨመርበት ሰው ሆነ እንጂ፡፡ ጌታ ሰው በሆነበት ግብር ሊቀ ካህናት ነው፡፡ "ዕሩቅ ብእሲ /ተርታ ሰው/ ነው የሚል የተወገዘ ነው ይኹን ሰለ ራሱም ራሱን መሥዕዋት አድርጎ አቀረበ የሚል የተወገዘ ይሁን ያድነን ዘንድ በተለየ አካሉ ሰለ እኛ በፈቃዱ ራሱን መሥዕዋት አድርጎ አቀረበ እንጂ" ሃይማኖተ አበው ቃለ ግዘት ዘቅዱስ ቄርሎስ 10:35-37


No comments:

Post a Comment