Sunday 9 February 2020

ድርሳነ ሚካኤል ፣ ድርሳነ ገብርኤል ፣ ድርሳነ ሩፋኤል ፣ ድርሳነ ራጉኤል ፣ ድርሳነ ፋኑኤል ፣ ድርሳነ ሳቁኤል ፣ ድርሳነ አፍኒን።

‹‹መላእክት›› የቃሉ ትርጉም

መላእክት የሚለው ቃል በ3 መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡

‹‹መላእክት›› ማለት፡- መልእክተኞች፣ ተላላኪዎች ማለት ነው፡፡
ይህን ተግባር የሚፈፅሙት ቅዱሳን ሰማይውያን መላእክት ናቸው፡፡ የእርቅ መልእክተኞች ናቸውና፡፡
‹‹መላእክት›› ማለት አለቆች፣ ገዢዎች ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ በሥልጣን ኮርቻ ላይ ላሉ ሰዎችና ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች አለቆች የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ ራዕይ 1¸20 ‹‹በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፡፡ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፣ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው›› እንዲል፡፡
‹‹መላእክት›› ማለት ከክብር ይልቅ ኃሣርን መርጠው የተዋረዱትን ርኩሳን መናፍስት አጋንንትን መላእክት ይላቸዋል፡፡
ማቴ 25 41 ‹‹እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክተኞቹ ወደተዘጋጀ ወደዘለዓለም እሳት ከእኔ ሄዱ›› እንዲል፡፡
ቅዱሳን መላእክት ለምንና እንዴት ተፈጠሩ?


 የቅዱሳን መላእክት የተፈጥሮ ሁኔታ /ኩነተ ተፈጥሮ/

ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ኢመዋትያን /የማይሞቱ/ ናቸው፡፡ ዝንተ ዓለም በቅድስና ቆመው እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ይኖራሉ፡፡
ቅዱሳን መላእክት ፈጻምያነ ፈቃድ ናቸው የእግዚአብሔርንና የሰውን ፈቃድ ሲፈጽሙ ይኖራሉ፡፡
ቅዱሳን መላእክት (አልቦ ፍፃሜ ለመዋዕሊሆሙ) ለዘመናቸው ፍፃሜ አይነገርላቸውም፡፡
ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ከእሳትና ከነፋስ ነው፡፡
መዝ 103¸4 ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዩቹን የእሳት ነበልባል›› እንዲል

ነገር ግን ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ሲል ግብራቸውን ለመግለፅ እንጂ እንደምናየው እሳትና ነፋስ ቢሆኑ ኖሮ እንደእኛ ሰዎች ፈርሰው በስብሰው በቀሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእውነተኛ አምላክ ብርሃን ተፈጥረዋልና እንደ እሳት ኃያላን፣ እንደእሳት ብሩሃን አእምሮ፣ እንደነፋስ ፈጣን፣ እንደነፋስ ረቂቅ መሆናቸውን ለመግለጽ ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ይላቸዋል፡፡

ዓለመ መላእክትና አሰፋፈራቸው

ከሰባቱ ሰማያት መካከል ሦስቱ ሰማያት ማለትም ዓለመ መላእክት የመላእክት ከተማ /መኖሪያ/ ሲሆኑ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን በነገድ መቶ (100) በከተማ አሥር (10) አድርጐ በሦስቱ ሰማያት በኢዮር፣ በራማና በኤረር አስፍሯቸዋል፡፡
Show less 

No comments:

Post a Comment