Sunday 23 February 2020

✥ይቅር ማለት አሸናፊነት ነው ይቅርታ መጠየቅ ብልህነት ነው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አስተማሪ ጽሁፍ እንሆኛ ያንብቡ ።

አዘጋጅ በለጠ ከበደ(የጣፈጡ ልጅ)

✥የደብብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ በነፃነት ትግል ወቅት ታስረው ነበር ጊዜ በኋላ ትግሉ ውጤታማ ሆኖ ማንዴላ የደብብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ከሆኑ ከጊዜ በኋላ አንድ ቀን ጠባቂዎቻቸውን ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።

✥አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ።

✥ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። ሰውዬው እየተመገበ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር። ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማንዴላ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነው መሰለኝ ።

✥እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር"ይላቸዋል ማንዴላ "አይደለም!ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር ። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናብኝ ነበር" አሁን ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም ።

✥ የግል ምልከታ የሰው ልጅ ሁል ጊዜ ልክ አይሁንም ሁሌም አይሳሳትም ይቅር የማይል ሰው እርሱ ጊዜ ደርሶ ሁኔታዎች ገጥመው መሳሳቱ አይቀርም እና ይቅር ባላለ ልቡ ይቅርታን አይጠይቅም ቢጠይቅም ፍጹም ሰላም አይሰማውም። ይቅርታ ማድረግ የሕሊና እረፍት ነው ይቅር አለማለት የክፋት እስር ቤት ነው ። ይቅር የምንል ከሆነ ብናጠፉም ይቅር ለመባል ለወደፊቱ ተስፉ አለን ከሰው በናገኝው እንኳን ፍጹም ማህሪ ከሆነው አምላክ ምህረት ይገኛል ። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና ይቅር ማለት አሸናፊነት ነው በፈጣሪ ዘንድ ምህረት ምናገኝባት ።

✥ይቅርታ መጠይቅ ውርደት ሳይሆነ ብልህነት ነው። በጥፋታችን ያጣነውን ጉደኘ ፣ ተአማኝነት፣ የበጠስነውን የሕይወት ገመድ ዳግም ለማሰር የምንጓዝበት መንገድ ነው።

ሰዎች ሁላችን ይቅርታ ባንጠይቅ የተጠየቅንም ይቅር ባንል የሰው ልጆች ሁላችን በአንድ ላይ መኖር አንችልም ምክያቱም አውቆንም ይሁን ሳናውቅ እንበድላለን እንሳሳታለን ታዲያ በዚህ መሃል ይቅርታ የማንጠይቅ ስንጠየቅም ይቅር የማንል ከሆነ እንዴት መኖር እንችላለን ። እስራኤላውያን በመሴ ክፉ አስበው በድንጋይ ለሚግሩት ቢነሱ እርሱ በኃጢአታቸው እንዳይጠፉ ይቅር ብሎ ምህረት ይለምናል ።
ጌታችን ላይም አይሁዶች በክፉት እሮማዊያን ጨክነው በስቅሉት ጊዜ እርሱ ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ በደላቸውን ሳይቆጥር ይቅር ብሎ እኛ ይቅር እንድል ምሳሌ አርያ ሆኖ አሳይቶናል የፈለገ ብንበደል ፣ በንገፋ፣ በንሰደብ ፣በንመታ በጌታችን ላይ ከደረሰው የበለጠ መከራ አልደረሰብንም እና እርሱን አረያ አብነት አድርገን ይቅር እንበል ይቅር እንድንባል ማቴ 6:14-15።

ሀገር ትዳር ጓደኝነት የሚቀጥሉት ይቅር በማለት እና ይቅርታ በመጠየቅ ነው።

የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏🙏

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇... ...... 👉አስተማሪ ጹሁች ለማግኝት ከስር ያለውን በመጫን ላይክ 👍 ይቀላቀላሉ https://www.facebook.com/%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0-%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-232318137666445/
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

በቴሌ ግራም መዝገበ ሃይማኖት ወይም @mezgebehaymanot ይቀላቀላሉ 🤳

beletekebede03@gmail.com

ጥቅምት 2009 ዓ.ም
አዲስ አበባ(ጣፎ)የተፃፈ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ጥር 21-እረፍታ ለእግዚእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ

Image may contain: 14 people, indoor
«ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ -ሞት ለሚሞት /ለሟች/ ይገባል የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል»
እንኳን ለአስተርእዮ ማርያም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥር 21-እረፍታ ለእግዚእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
(በገብረሥላሴ)
«ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡» ቅዱስ ያሬድ፡፡
‹‹አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡፡›› ቅዱስ ዳዊት፡፡
‹‹ወዳጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ!›› ጠቢቡ ሰሎሞን፡፡
ከመጽሐፈ ተአምሯ፡- እመቤታችን ከዚህ ዓለም ታልፍ ዘንድ የጸለየችው ጸሎት ይህ ነው፡- ‹‹ልመናዋ ክብሯ ለዘለዓለሙ በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተአምር ይህ ነው፡- አምላክን የወለደች እመቤታችን በቤተልሔም ተቀምጣ ሳለች ‹አቤቱ ቸር ጌታዬ ሆይ! ከዚህ ሑከትና ኀዘን ከመላበት ዓለም ደገኛውን መልአክህን ልከህ ወደኝ› ስትል በጸለየች ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸላት፡፡ እንዲህም እያለች ስትጸልይ ሰማይ ተከፈተ፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ወደ እመቤታችን ወርዶ ‹ጸጋን የተመላሽ ሆይ! ደስ ይበልሽ› በማለት የደስታ መልእክት ነገራት፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነሆ ጸሎትሽ ከአንቺ ከተወለደው ከእግዚአብሔር ዘንድ ደረሰ፡፡ እንደፈቃድሽ ከዚህ በኃላፊው ዓለም ወደ ዘላለም ሕይወት ትሄጂ ዘንድ ልመናሽ ተሰምቶልሻል›› አላት፡፡
እመቤታችንም ይህንን ነገር ከመልአኩ በሰማች ጊዜ ወደ በዓቷ ተመለሰችና ከዚያ የሚያገለግሏትን ደናግል ሰብስባ ‹አይሁድ ሁልጊዜ የልጄን መቃብር ይጠብቃሉና ስለዚህ የእኔን ከዚያ መገኘት አንድ ቀን ይገለጽላቸውና ከዚያ መግባት ይከለክሉኛል ብዬ ፈራሁ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ራሳችሁን ችላላችሁ በሰላም ትኖራላችሁ እኔ ወደ ቤተልሔም እሄዳለሁና› አለቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉም በአንድነት ቃላቸውን አስተባብረው ‹ከአንቺ ጋር እንሄዳለን፡፡ ስለ አንቺ እናት አባታችንን፣ እኅት ወንድሞቻችንን ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሻልና እነሆ አሁንም አንቺ ከሄድሽበት እኛም አብረንሽ እንሄዳለን፣ ባለ ዘመናችን ሁሉ ከአንቺ አንለይም› አሏት፡፡ እመቤታችንም በዚያን ጊዜ ይዛቸው ወደ ቤተልሔም ሄደች፣ በዚያም ተቀመጠች፡፡ እንዲህም ያለቻቸው ስለ አይሁድ ፍራቻ ሳይሆን ከዚህ ከኃላፊው ዓለም በሞት የመለየቷ ጊዜ ስለመድረሱ ነበር፡፡ እናንት የፍቅሯን ፈለግ የተከተላችሁና በፍቅሯ ቀምበር የተጠመዳችሁ የወንጌል ልጆች ሆይ እንግዲህ እመቤታችን በቤተልሔም ተቀምጣ ሳለች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከዚህ ዓለም በሞት የምትለይበትን ጊዜ በክብር እንደነገራት አስተውሉ፡፡ ልመናዋ ክብሯ ለዘለዓለሙ በዕውነት ይደርብን፡፡እረፍታ ለእግዚእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፡- በ50 ዓ.ም ገደማ በዕለተ እሑድ ጌታችን እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ ‹‹እናቴ ሆይ! ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜ፣ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ ጌታችንም በሲኦል የሚሠቃዩ ነፍሳትን አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ! ሞትሽ ለእኒህ ቤዛ ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ለፍጥረታት ሁሉ እጅግ የምትራራ እመቤታችንም ‹‹እነዚህን ከማርክልኝስ ይሁን ልሙት›› አለችው፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ቅድስት ነፍስዋን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ ‹‹እመቤታችሁን ቅበሩ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ይዘዋት ወደ ጌታ ሰማኔ ወሰዷት፡፡አበው ‹‹እመቤታችን ሆይ! ሞትሽ ሠርግን ይመስላል›› እንዳሉት የእመቤታችን እረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት እንዳለበት የሰው ሞት አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደ ሠርግ ቤት ቅዱሳን መላእክት በውዳሴ፤ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት እንጂ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለች፤ በዚያም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች›› በማለት ዘምሯል፡፡ የእመቤታችን ሥጋዋ ከጌቴሴማኔ ወደ ገነት መፍለሱን አስቀድሞ አባቷ ቅዱስ ዳዊት በትንቢት ሲናገር ‹‹አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› በማለት ተንብዮዋል፡፡ መዝ 131፡8፡፡ ይህም ‹‹ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህ ዓለም ከኖረች በኋላ ነብሷ ከሥጋዋ ተለይቶ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ‹‹ታቦት›› ያላትም ማደሪያው ስለሆነች ነው፡፡
ጠቢቡ ሰሎሞን በምሳሌ ሲናገር «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ፣ ዝናቡም አልፎ ሄደ፣ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ፣ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነይ» አለ፡፡ መኃ 2፡10-14፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ሲተረጎም በውስጡ ብዙ ምሥጢራዊ ነገሮችን ያያዘ ነው፡፡ «በክረምትና በዝናብ» የተመሰሉ የእመቤታችን መከራዎች ናቸው፡፡ የመከራሽ ጊዜ አልፏል ሲላት «አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ» ማለቱ ከልጅሽ እግር ሥር ቁጭ ብለው ተምረው ወንጌልን የተቀበሉ ሐዋርያት አንቺን በእናትነት የተረከቡ የሐዋርያት ድምፅ ወይም ስብከት በምድር ሁሉ መሰማቱን ያጠይቃል፡፡ጠቢቡ ሰሎሞን «የዜማ ጊዜ ደረሰ» ያለው የመከሩን ወቅት ነው፡፡ መከር የፍሬ ጊዜ እንደመኖኑ ሐዋርያት የዘሩት ዘር ማለትም ስብከታቸው ፍሬ አፈራና ክርስቲያኖች በዙ፤ «በለሱ ጎመራ» በጎ ምግባር የሌላቸው ሰዎች በሐዋርያት ስብከት ተምረው ምግባር መሥራት ጀመሩ፤ «ወይኖች አብበዋል መዐዛቸውንም ሰጥተዋል» በመላው ዓለም ያሉ ምዕመናን በሃይማኖት ማበብ፣ መዐዛ ምግባራቸውን ማቅረብ መስጠት ጀመሩ በማለት ሊቃውንት አባቶች ምሥጢሩን ያብራሩታል፡፡ በዚህ ትርጓሜ ‹‹ወደጄ ሆይ! ተነሽ›› እያለ የሚናገረው ተወዳጁ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ድንግል ማርያምን በመለኮታዊ ስልጣኑ ከሙታን ለይቶ ማስነሣቱን ሲያስረዳን ነው፡፡ስለዚህ ድንቅ ምስጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› (መዝ 131፡8) ብሎ የተናገረው ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕረፍትና ትንሳኤ እንዲሁም ፍልሰት (ዕርገት) ከማሳየቱም በተጨማሪ የአምላክ እናት በልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት በክብር መኖሯንም በግልጽ ያስረዳል ያስገነዝባል፡፡ ‹‹በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› (መዝ 44፡9) የሚለውን የቅዱስ ዳዊት ትንቢታዊ ቃል ሊቃውንት አባቶች በተለይም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መተርጉማን ‹‹ንግሥተ ሰማይ ወምድር ድንግል ማርያም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና›› ተሸልማና አጊጣ በሰማያዊው ዓለም በልጇ መንግሥት በክብር መኖሯን የሚያመለክት መሆኑን አስረግጠው አስረድተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ሰማያዊው አባታቸውን እግዚአብሔርን ‹‹አቡነ ዘበሰማያት፤ በሰማያት የምትኖር አባታችን›› እያሉ ዘወትር ሲያመሰግኑ፤ በአንጻሩ ደግሞ መንፈሳዊት እናታቸውን ድንግል ማርያምን ‹‹በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፤ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ›› እያሉ ዘወትር ያከብሯታል ያመሰግኗታልም፡፡ ሉቃ 1፡28፡፡ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዘወትር በምንጸልየው የእሑድ የእመቤታችን ውዳሴ ላይ ‹‹ምልዕተ ጸጋ፣ ምልዕተ ክብር፣ ምልዕተ ውዳሴ የሆንሽ ድንግል ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልኝ ዘንድ ለአንቺ ይገባል፡፡ አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ፤ ከቅዱሳን ነቢያት፣ ከቅዱሳን ሐዋርያት ከሰብዓ አርድእትም ትበልጫለሽ፡፡ ዳግመኛም ከሱራፌልና ከኪሩቤል ይልቅ የሚበልጥ የመወደድ የመፈራት ግርማ አለሽ፡፡ በእውነት የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ፡፡ ለሰውነታችንም ሕይወትን፣ ድኅነትን የምትለምኚና የምታማልጅን አንቺ ነሽ›› በማለት የእመቤታችን ልዕልናዋን የጸጋዋን ፍጹምነትና የክብሯን ታላቅነት በአጽንኦት ገልጾ መስክሯል፡፡
እመቤታችን በጥር ሃያ አንድ ቀን በታላቅ ክብር ካረፈች በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በፈቃደ እግዚአብሔር ከያሉበት መጥተው በኢየሩሳሌም ተሰብስበው የፈጣሪያችን እናት ድንግል ማርያምን በጸሎትና በማዕጠንት አክብረው ገንዘው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና «ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተቀብሮ ሳለ ተነሣ እያሉ ሕዝቡን አስኮበለሉ አሁን ደግሞ እናቱን ሞታ ተነሣች እያሉ እንዳያውኩ ሥጋዋን እናቃጥል» በሚል የክፋት ምክር ተነሳሱ፡፡ በተለይም ደግሞ በእመቤታችን ላይ በክፋትና በተንኮል ከተነሳሱት ከእኒህ አይሁድ መካከል ታውፋንያ የተባለው አይሁዳዊ
አማናዊት ታቦተ እግዚአብሔር የሆነችው የድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋ ያረፈበትን አልጋ ለመያዝ እጁን በድፍረት ዘረጋ፡፡ በዚህን ጊዜ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን (2ኛ ሳሙ 6፡6፤ 1ኛ ዜና 13፡7-10) ላይ የአሚናዳብ ልጅ ዖዛ እጁን በታቦተ ጽዮን ላይ በድፍረት በመዘርጋቱ ምክንያት ተቆጥቶ እንደቀጣው ታውፋንያንም ሰማያዊው መልአክ ሰይፍ እጆቹን ቀጣው ቆረጠው፡፡ «እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን የሚዘረጋ ንጹሕ አይሆንም (1ኛ ሳሙ 26፡9) እንደተባለ እጆቹም አልጋው ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡
ታውፋንያም ስለተቆረጡት እጆቹ ወደ እመቤታችን አምኖ ወደ እርሷ ቢጮህ ቢማጸናት፤ በቅዱስ ጴጥሮስ አማካይኝነት እጆቹን እንደ ቀድሞ ሆነው ድነውለታል፡፡ በጌታችን ትእዛዝ መልአኩ የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር በክብር አኑሮታል፡፡ቅዱሳን ሐዋርያት ዮሐንስ ከተመለሰ በኋላ ‹‹እመቤታችን እንደምን አለች?›› አሉት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም «ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች» አላቸው፡፡ እነርሱም ዮሐንስ ዐይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ፡፡ ጥር አርፋ በነሐሴ ወር ሁለት ሱባኤ ይዘው ሲጨርሱ በነሐሴ 14 መልአኩ ቅዱስ ሥጋዋን ከገነት አምጥቶ ሰጥቷቸው በጸሎትና በምሕላ ቀብረዋታል፡፡ በዚህ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም፡፡ በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ተነሥታ ስታርግ፣ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፡፡ በዚህ ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው፣ ለእርሱ የቀረበት መስሎት አዝኖ ‹‹በፊት የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ፤ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ከደመናው ለመውደቅ ተመኘ፡፡ በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አጽናናችው፡፡ ከእርሱ በቀር ትንሣኤዋን ሌላ እንዳላየ ነገራው ለምስክር እንዲሆነው ሰበኗን/መግነዝ ሰጥታው ዐረገች፡፡
ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ ክብርት እናቱ እመቤታችም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጇ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ ‹‹እንደ ልጅዋ ትንሣኤ›› ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ምስጢሩን ደብቆ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› አላቸው፡፡ ሐዋርያትም ‹‹አንተ ተጠራጣሪ ነህ›› ብለው መቃብሩን ሊያሳዩት ሲከፍቱ አጧት፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹እመቤታችን ተነሥታ አርጋለች›› ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው፡፡ ‹‹ለምስክር ይሁንህ›› ብላ የሰጠቸውንም ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን አይተው ትንሣኤዋን አመኑ። ሰበኗን ቆራርጠው ለበረከት ተከፋፍለው ወደየሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል፡፡ ዛሬም በመጾር መስቀልና በካህናት እጅ መስቀላቸው ላይ የሚያስሯት ‹‹መሀረብ›› የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው፡፡ በዓመቱም ሐዋርያት ‹‹ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን!›› ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በነሐሴ 16 ቀንም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አሳርጎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቅዳሴ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም የመቤታችንን ትንሣኤና ዕርገቷን በዓይናቸው አይተውና በሚገባ ተረድተው ዓለምን ዙረው አስተምረዋል፡፡ ልመናዋ ክብሯ ለዘለዓለሙ በዕውነት ይደርብን፡፡
ከመጽሐፈ ስንክሳር፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከመሞቷ በፊት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብሩ ቦታ ትጸልይ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለእመቤታችን ከዚህ ዓለም እንደምትለይ ነገራት፡፡ ጌታችንም በደብረ ዘይት ላሉ ደናግላን ነግሯቸዋልና ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፍጥነት መጡ፡፡ እርሷም መንፈስ ቅዱስ የነገራትን ለእነርሱ ነገረቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ጸለየች፡- ‹‹ልጄ ወዳጄ፣ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ልመናየን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም ሕያዋን የሆኑትን ሐዋርያትን ሁሉንም ነፍሶቻቸውን የለየሃቸውንም ሁሉ ወደ እኔ አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋን አምላክ ነህና ለአንተም ምስጋና ይሁን አሜን›› አለች፡፡በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ቅዱስ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን አደረሰችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በፊቷ ሰገደላትና እንዲህ አላት፡- ‹‹ሰላምታ ይገባሻል፣ ጌታችንን ፈጣሪያችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሽው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ከዚህ ዓለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሄጃለሽና፡፡ ይህም ስሙ ክቡር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቅ ድንቅ ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኋላ ነው›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እግዚአብሔርንምእንዲህ ብላ አመሰገነችው፡- ‹‹ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን፣ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና፡፡ አሁንም ነብሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊይሳርጓት ከሚመጡ ቅዱሳን መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ›› አለችው፡፡ በዚያም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- ‹‹እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ፡፡ ሐዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ፡፡ ወዲያውም ሁሉም ሐዋርያት የሞቱት ከመቃብራቸው ተነሥተው በሕይወት ያሉትም ሁሉም ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ ‹‹አምላካችን ከአንቺ የተወለደ ጸጋን የተመላሽ ሆይ! ደስ ይበልሽ፣ እርሱ ከዚህ ዓለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከእርሱ ጋር ያሳርግሻልና›› አሏት፡፡በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በዐልጋዋ ላይ ተቀመጠችና ሐዋርያትን እንዲህ አለቻቸው፡- ፈጣሪዬ ፈጣሪያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን ዐወቅሁ፡፡ ከዚህ ከሥጋዬ ወጥቼ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እሄዳለሁ፡፡ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፣ እኔ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ዐወቃችሁ?›› ብላ የጠቀቻቸው፡፡ በመጀመሪያ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚያም ሁሉም ሐዋርያት ‹‹ወደ አንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፣ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አሏት፡፡
እመቤታችንም ይህን ነገር ከሐዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- ‹‹ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሰግናለሁ፣ የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል›› አለች፡፡ ጸሎቷንም ስትጨርስ ሐዋርያትን ‹‹ዕጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት›› አለቻቸው፡፡ እነሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ፡፡ በዚያም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክቱ አጅበው እያመሰገኑት መጣና እመቤታችንን አረጋጋት፡፡ ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት፡፡ በዚያም ጊዜ ድንቆቸ የሆኑ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ዓይነ ሥውራን ማየት ቻሉ፣ ደንቆሮች መስማት ቻሉ፣ ዲዳዎች ተናገሩ፣ ለምጻሞች ነጹ፣ ሐንካሶች መሄድ ቻሉ፣ ደዌ ያለበትም ሁሉ ዳነ፡፡ የብርሃን እናቱ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ወደ አለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌአቸው ሁሉ ይፈወሳሉና፡፡ከዚህም በኋላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ‹‹በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሣ ከእሳት ባሕርም የተነሣ እፈራለሁ›› ባለችው ጊዜ እርሱም ‹‹እናቴ ሆይ ከእነርሱ ለማንም በአንቺ ላይ ሥልጣን የለውም›› አላት፡፡ ከሥጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትንና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት፡፡ እመቤታችንም እጇን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ጌታችን ቅድስት ንጽሕት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሃን ልብስ አጎናጽፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት። ሥጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው፤ ወደ ጌቴ ሰማኒ ተሸክመው እንዲወስዷ ሐዋርያትን አዘዛቸው፡፡ ነፍሷ ከሥጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሃን እያየች ነበር፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችንም ‹‹እንግዲህ ሥጋሽን ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ፡፡ ዳግመኛም ሥጋሽን ከነፍሽ ጋር አዋሕጄ አስነሥቼ መላእክት በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት አምሳያ በሌለው ተድላ ደስታ ባለበት መኖሪያ አኖርሻለሁ›› አላት፡፡
እመቤታችንም እንዲህ አለች፡- ‹‹አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሠራህ አመሰግንሃለሁ፤ ሁለተኛም ልመናየን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ፤ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሁኖ ስሜን ጠርቶ ወደ አንተ የሚለምነውን ከመከራም ሁሉ አድነው፤ በሰማይም በምድርም በሥራው ላይ ሁሉ አንተ ከሃሊ ነህና መታሰቢያየን በውስጧ የሚያደርጉባትን ቦታ ሁሉ ባርክ፣ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መሥዋዕታቸውን ተቀበል›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት፡- ‹‹የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ ደስ ይበልሽ፣ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ጸጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህ ዓለምም በወዲያኛው ዓለምም ከቶ አይጠፋም›› አላት፡፡ እመቤታችንም በታላቅ ክብር ካረፈች በኋላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሊወስዷት ሐዋርይት ገንዘው ተሸከሟት፡፡ አይሁድም በሰሙ ጊዜ ሥጋዋን ሊይቃጥሉ ወጡ፡፡ ከእርሳቸውም አንዱ ከምድር ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ፡፡ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋው ላይ ጠንጠለጠሉ፡፡ ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ፡- ‹‹የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ሆይ! አንቺ በእውነት ድንግል ይሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ አለምንሻለሁ፡፡›› በሐዋርይትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ፡፡ሐዋርያትም እመቤታችንን በቀብሯት ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ፣ ዕረፍቷም የሆነው እሑድ ቀን ጥር ወር በ21 ቀን ነበረ፡፡ ጌታችንም ብርሃናውያን መላእክትን ላከ፣ እነርሱም ሥጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር አኖሯት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲያሳርጓት እመቤታችንን አገኟት፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ‹‹ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርይም ና እጅ ንሣ›› አሉት፡፡ እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ሐዋርያት ደረሰ፡፡ እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንዳረፈችና እንደ ቀበሯት ነገሩት፡፡ ቶማስም ‹‹ሥጋዋን እስከማይ አላምንም›› አላቸው፡፡ ሥጋውንም ያሳዩት ዘንድ ወደ መቃብሯት ባደረሱት ጊዜ በመቃብሩ ውስጥ ሥጋዋን አላገኙም፤ እነርሱም ደንግጠው እያደነቁ ሳለ ያን ጊዜ ቶማስ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችን እንዳገኛት ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን ዕርገቷን ስላላዩ እጅግ አዘኑ፡፡ ሥጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በተስፋ እስከ ነሐሴ 16 በተስፋ ኖሩ፡፡
የሕይወት የድኅነት አለኝታ የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ በጸሎቷም ከከፉ ነገር ይጠብቀን፣ በረከቷ ከእኛ በአማላጅነቷ ከምንታመን ከተዋሕዶ ልጆች ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ዕርገት ቊጥሩ ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱስ ኢቮዲየስ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ስለነበረ በጥር 21 ቀንና በነሐሴ 16 ቀን የተከናውን የእመቤታችንን ዕረፍትና በዓለ ዕርገቷን በዐይኖቹ የተመለከተውን ጽፎልናል፡፡ ይህንንም መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ‹‹የእመቤታችን አስደናቂ ዕረፍትና ዕርገት›› በሚል ርስስ ግሩም አድርገው ጽፈውታል፡፡ ሙሉ ጽሑፋቸውን ለማነበብ ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) ይጫኑ፡፡ https://m.facebook.com/photo.php?fbid=846179682110796&id=100001563172397&set=a.240113796050724.61033.100001563172397&refid=7&__tn__=%2Asየብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ከበዓሏ በረከት ትክፈለን፣ በጸሎቷ ታስምረን!!! የልጇንና የእሷን ሞት በሚመስል ሞት ሞተን ትንሣኤያቸውን በሚመስል ትንሣኤ እንተባበር ዘንድ ትርዳን በእውነት፡፡(ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርሃ ጥር፣ ተአምረ ማርያም፣ ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት፣ የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤትና የማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል መካነ ድር፣ የቅዱሳን ታሪክ)

ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገባ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን

1. ጫማ አድርጐ ወደ ቤተመቅደስ መግባት ክልክል
ነው፡፡ ዘጸ 3፡5 የሐዋ 7፡39 2ኛ ዜና7፡14
2. ለሃጩን የማዝረክረክ ነውር /ልጋግ/ ያለበት ሰው
ቤተክርስቲያን አይገባም
3. በቤተክርስቲያን አጸድ ግብዣ ማድረግ አይገባም፡፡ ፍት.ነገ.
አንቀጽ 1 ክርስቶስ ሥጋና ደም
ከሚሰዋበት ምዕመናን ሥጋወደሙን ከሚቀበሉበት
ከቤተክርስቲያን ራቅ ብሎ በደጀ ሰላም አቅራቢያ
በቤተ ምርፋቅ ካልሆነ በቀር በቤተመቅደስ ውስጥና
በዓውደ ምሕረት ላይ ሥጋዊ መብል መጠጥ
ማቅረብ መብላት መጠጣት አይገባም፡፡
4. የቤተክርስቲያን መገልገያ ንዋያተ ቅዱሳትን ለግል
አገልግሎት ማዋል አይገባም፡፡ ዳን 5፡35-31 ፍት.
ነገ. አን.1 ረስጣ 28
5. በቅጽረ ቤተክርስቲያን ገበያ መገበያየት አይገባም
ዮሐ2፡14-17 ፍት.ነገ. አን. 1
6. በቤተመቅደስ በማኅበር ጸሎት ወቅት የግል ጸሎት ማድረግ
ክልክል ነው፡፡
7. በቤተመቅደስ በቅዳሴ ሰዓት አቋርጦ መውጣት
ክልክል ነው፡፡ ማቴ 26፡26 ዕንባ2፡2ዐ
8. ሴት ልጅ በወር አበባ ወቅት ወደ ቤተመቅደስ
መግባት አይፈቀድላትም፡፡ ዘሌዋ 15፡18-30 ፍት.
ነገ. 14፡583 9. ወንድ ልጅ ሕልመ ሌሊት /ዝንየት/ ከመታው
በዕለቱ ወደ ቤተመቅደስ አይገባም፡፡ ዘሌዋ 15፡2-18
10. የሌሊት ልብስ /የአረማውያን ልብስ/ ለብሶ ወደ
ቤተመቅደስ መግባት ክልክል ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ 11፡5-14
11. ባልና ሚስት ከተራክቦ በኋላ ዕለቱን ወደ
ቤተመቅደስ ለመግባት አይፈቀድላቸውም፡፡
«ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹሕ ቢሆንም
በቤተክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከተራክብ በኋላ
ዕለቱኑ ወደ መቅደስ መግባት አይቻልም፡፡ ቅዱስ
ጳውሎስ «ለጸሎት በመፈቃቀድ ካልሆነ በስተቀር ባልና ሚስት
አይከላከሉ» እንዳለው ባልና ሚስት
ከተራክቦ የሚርቁት በበዓላት፣ በአጽዋማት፣
ለጸሎትና ለቅዳሴ በሚዘጋጁበት ዕለታት በሰንበት
ነው፡፡ ስለዚህ ጠዋት ለቅዳሴ በሚዘጋጁበት ጊዜ
ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል፡፡ 1ኛ ቆሮ 7፡5 ኩፋሌ
34፡12 ዘጸ19፡15
12. በቤተ መቅደስ ውስጥ መሳቅ፣ መሳለቅ፣
ዋዛፈዛዛ ነገር መነጋገር ክልክል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
«በምድራዊ ንጉሥ ፊት በቆምክ ጊዜ በምንም
ምክንያት ቢሆን ለመሳቅ አትደፋፈርም ታዲያ
በሰማያዊ ንጉሠ ነገሥት ፊት ትስቃለህን? ብሏል፡፡
ተግሣጽ ዘዮሐንስ አፈወርቅ አንቀጽ 6 «በቅዳሴ ሰዓት /ጊዜ/
የሚስቅ ዓለማዊ ቢሆን ወደ ውጭ
ያውጡት ከቅዱስ ምሥጢር /ከቁርባኑ/ አያቀብሉት
ተብሏል፡፡ ቀኖና ባስሌዎስ አንቀጽ 79
13. አብዝቶ ጠጥቶና ሰክሮ መግባት ክልክል ነው፡፡
«እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ አንተና
ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክር ነገር ሁሉ አትጠጡ» ዘሌዋ
1ዐ፡8-10 ሉቃስ 21፡34 ምሳሌ
23፡29-35 ይሁንና ይህን ወይን አትጠጣ ቀምሰህ
ፈጣሪህን ለማመስገን ያህል ብቻ ይሁን እንጂ እንደ
ጢሞቴዎስ ብትታመም ከገድል ጽናት የተነሳ በድኑ
ደዌ ብትያዝ ግን ከወይን ጥቂት ጠጣ እርሱ ለሥጋ
ሕይወት ይሆንልሃልና፡፡ 1ኛ ጢሞ 5፡23 ሃይማኖተ አበው
ዘሠልስቱ ምዕት 21፡17-18
14. በቂም በቀል ሰውን አስቀይሞ የሰውን ገንዘብ
በማጭበርበር ወስዶ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ
መጸለይ ክልክል ነው፡፡ ማቴ 5፡23-24 ማር 11፡25
ሉቃስ 18፡9-14
15. «ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ . . .» (ከተቀደሰ ስፍራ እንደቆምክ አስተውል፡፡) መክ 5፡1
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላድቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር

የካቲት 2 -የመላእክት ወገን የሆኑ የገዳማውያን ሁሉ አለቃ የከበሩ አባ ጳውሊ ዕረፍታቸው ነው፡፡


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 2 -የመላእክት ወገን የሆኑ የገዳማውያን ሁሉ አለቃ የከበሩ አባ ጳውሊ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ የቅዱሳን ዐፅም ቃል በቃል በማናገር የሃይማኖትን ነገር የተረዱት የደብረ ዝጋጉ አባ ለንጊኖስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አስገራሚ ተአምራት በማድረግ ብዙዎችን አስተምሮ አጥምቋል፡፡
አባ ለንጊኖስ ዘደብረ ዝጋግ፡- ትውልዳቸው ኪልቂያ ሲሆን በልጅነታቸው ገዳም ገብተው በመመንኮስ የአባ ሉክያኖስ ደቀ መዝሙር ሆነው በተጋድሎ ኖረዋል፡፡ መምህራቸው አባ ሉክያኖስን አበ ምኔትነት ሊሾሟቸው ሲሉ ውዳሴ ከንቱን በመጥላት አባ ለንጊኖስን ይዘው በድብቅ ወደ ሶርያ ሄዱ፡፡ በአንዲት ቤተ ክርስቲያንም ተቀምጠው ብዙ አስገራሚ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ዜናቸው በሁሉም ዘንድ ሲሰማ አሁንም ውዳሴ ከንቱን በመራቅ በአባታቸው ምክር አባ ለንጊኖስ ወደ ግብጽ ሄደው ደብረ ጽጋግ ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም አበምኔቱ ሲያርፉ በእግዚአብሔር ትእዛዝ አባ ለንጊኖስን አበ ምኔት አድርገው ሾሟቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መምህራቸው አባ ሉክያኖስ መጥተው የመርከብ ጣሪያ እየሠሩ አብረው በአንድ ልብ ሆነው በተጋድሎ ኖሩ፡፡ ድንቅ ድንቅ ተአምራት እያደረጉ ብዙ ከኖሩ በኋላ አባ ሉክያኖስ ሲያርፉ ‹‹የውሾች ጉባዔ›› እየተባለ የሚጠራውና ጌታችንን ‹ሁለት ባሕርይ› የሚለው የሮም የረከሰ እምነት በጉባዔ ተወሰነ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ መርቅያኖስም በሀገሮች ሁሉ የጉባዔውን ደብዳቤ መላክ ጀመረ፡፡
የንጉሡንም ደብዳቤ መልአክተኞቹ ለአባ ለንጊኖስ አመጡላቸውና ‹‹በዚህ ጽሑፍ እንድታምኑና እንድትፈርሙበት ንጉሡ አዟል›› ብለው ሰጧቸው፡፡ አቡነ ለንጊኖስም ‹‹ከቅዱሳን አባቶቼ ጋር ልማከርበት እኔ ምንም ምን መሥራት አልችልም እንድንማከርበት እናንተም ከእኔ ጋር ኑ›› ብለው የቅዱሳን ዐፅም ወዳለበት ዋሻ ውስጥ ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ አባታችንም ለአፅሞቹ እንዲህ ብለው ተናገሩ፡- ‹‹የከበራችሁ ቅዱሳን አባቶቼ ሆይ! እናንተ ዐርፈን ተኝተናል አትበሉ፣ እነሆ አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ የሚያደርግ በውስጡ የተጻፈበትን ይህን ደብዳቤ አምጥተዋልና በቃሉ አምን ዘንድ በውስጡም እፈርም ዘንድ ታዙኛላችሁን?›› እያሉ ዐፅሞቹን ጠየቋቸው፡፡ ያን ጊዜም የተላኩት ሰዎች ሁሉ እየሰሙ ከቅዱሳኑ አስክሬን ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል ወጣ፡- ‹‹የአባቶቻችንን የሐዋርያትንና የ318ቱን የቀናች ሃይማኖትን አትተው፣ ይህንንም የረከሰ ደብዳቤ አትከተል፣ ከአስክሬናችን ቦታ አርቀው እንጂ›› የሚል ቃል ከቅዱሳኑ አስክሬን ወጣ፡፡ ይህንንም የሰሙት የንጉሡ መልእክተኞች እጅግ አድንቀው ወደ ንጉሡ አልተመለሱም፤ ይልቁንም ራሳቸውን ተላጭተው በዚያው መነኮሱ እንጂ፡፡ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ የከበሩ አባ ለንጊኖስም ያማረ ተጋድሎአቸውን ጨርሰው በሰላም ዐርፈዋል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
የከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ ተአምራት በማድረግ ብዙዎችን እንዳጠመቀ፡- ይኸውም ጌታችን ወዳዘዘው ቦታ የከበረች ወንጌልን ሊያስተምር በወጣ ጊዜ ከመንገድም ፈቀቅ ብሎ ሳለ መልኩ በጣም የሚያምር ድንገት የሞተ አንድን ጎልማሳ አገኘ፡፡ ቅዱስ ቶማስም ‹‹አቤቱ ይህን ጥፋት አይ ዘንድ ወደዚህ አመጣኸኝን ነገር ግን ፈቃድህ ይሁን›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ስለሞተው ሰው ጸለየ፣ ያንጊዜም ታላቅ ከይሲ ከድንጋዮች ውስጥ ወጥቶ በጅራቱ ምድርን እየደበደበ መጣና ‹‹የክርስቶስ ሐዋርያ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋራ ምን አለኝ? ሥራዬን ልትዘልፍ ልታጋልጥ መጣህን!›› ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ፡፡ ቅዱስ ቶማስም ‹‹ሥራህን ተናገር›› አለው፡፡ ከይሲውም ‹‹በዚህ ቦታ መልከ መልካም ሴት ነበረች፣ እኔ የምወዳት ናት፡፡ ይህም ጎልማሳ ሲስማት አየሁት፡፡ በሰንበት ቀንም ከእርሷ ጋር አደረ፡፡ ስለዚህም ነክሼ በመርዝ ገደልኩት›› አለው፡፡ ሐዋርያውም ‹‹በል አሁን መርዝህን ከእርሱ ትወስድ ዘንድ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዤሃለሁ›› አለው፡፡ ከይሲውም ሄዶ ከዚያ ከሞተው ሰው መርዙን መጠጠና ወሰደ፡፡ ወዲያውም ተነፍቶ አበጠና ተሰንጥቆ ሞተ፡፡ ሞቶ የነበረው ጎልማሳ ግን በሐዋርያው ጸሎት ከሞት ተነሣ፡፡ ስለዚህችም የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ ተአምር ብዙዎች በክብር ባለቤት በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ቶማስም የቀናች ሃይማኖትን አስተምሮ አጠመቃቸው፡፡
የቅዱስ ቶማስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ርዕሰ ገዳማውያን አቡነ ጳውሊ፡- አባታቸው የገንዘቡን መጠን እንኳን የማያውቁት እጅግ ባለጸጋ ነበሩ፡፡ አባታቸው ከሞቱ በኋላ ወንድማቸው ጴጥሮስ ንብረታቸውን በትክክል አላካፍላቸው ስላለ ተጣልተው ወደ ዳኛ ሄዱ፡፡ በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ ሰው ሞቱ ሊቀብሩት ሲወስዱት አይተው አባ ጳውሊ አገኟቸው፡፡ የሞተው ማን እንደሆነም ሲጠይቁ የሞተው ሰው እጅግ ባለጸጋ እንደነበር በኃጢአት ውስጥም ሆኖ እንደሞተ ተነገራቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ ጳውሊ ‹‹የዚህ የኃላፊ ዓለም ገንዘብ ለእኔ ምኔ ነው?›› ብለው ወደ ወንድማቸው ዞረው ወደ ዳኛ መሄዳቸውን ትተው ወደቤት እንዲመለሱ ለመኑት፡፡ የአባታቸውንም የተትረፈረፈ ሀብትና ንብረት ፈጽሞ እንደማይፈልጉት ነገሩት፡፡
ከወንድማቸውም ተደብቀውና ሸሽተው በመውጣት በአንዲት በመቃብር ቤት ገብተው መጸለይ ጀመሩ፡፡ በ4ኛ ቀናቸውም የታዘዘ መልአክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ ከአንድ በረሃ ውስጥ አደረሳቸው፡፡ አባ ጳውሊም ወደ አንዲት ኩርፍታ ገብተው ተጋድሎአቸውን ጀመሩ፡፡ በዚያች ዋሻ ውስጥም የሰውን ፊት ሳያዩ በጾም በጸሎት ብቻ ተወስነው 80 ዓመት ኖሩ፡፡
ልብሳቸውም ከሰሌን ቅጠል የተሠራ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ ነቢዩ ኤልያስ ቁራን እየላከ ምግባቸውን ይሰጣቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን የጳውሊን ክብር ይገልጥ ዘንድ መልአኩን ወደ አባ እንጦንስ ዘንድ ላከው፡፡ አባ እንጦንስም በበረሃ ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ በበረሃ መኖር የጀመሩት እሳቸው እንደሆኑ በልባቸው ማሰብ ጀምረው ነበር፡፡ መልአኩም ተገልጦላቸው ‹‹እንጦንስ ሆይ ከአንተ የሁለት ቀን ጎዳና ርቆ በበረሃ ውስጥ የሚኖር ሰው አለ፤ የዓለም ሰዎች ከሚረግጥባቸው የእግሩ ጫማዎች እንደ አንዲቱ ሊሆኑ የማይገባቸው ስለ እርሱም ጸሎት ዓለም ተጠብቆ የሚኖር ነው…›› እያለ የአባ ጳውሊ ክብር ነገራቸው፡፡
አባ እንጦንስም የአባ ጳውሊን በዓት ፈልገው አግኝተው ሄደው በብዙ ምልጃ በሩን ከፍተውላቸው ተገናኝተው ሁለቱም አብረው ከጸለዩ በኋላ ስለ ተጋድሎአቸውና ስለ አኗኗራቸው ተወያዩ፡፡ የታዘዘው ቁራ ሌላ ጊዜ የጳውሊን ምግብ የሚያመጣው ግማሽ እንጀራ ነበር ዛሬ ግን ሙሉ እንጀራ ስላመጣላቸው ሁሉቱም ቅዱሳን ደስ ተሰኝተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ አባ እንጦንስም ሥጋ ወደሙን ከወዴት እንደሚቀበሉ አባ ጳውሊን ሲጠይቋቸው በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ መልአክ እያመጣ ሥጋ ወደሙን እንደሚያቀብላቸው ነገሯቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አባ እንጦንስ ‹‹ይህ አስኬማ በምድር ላይ ይበዛ እንደሆነ ወይም አለመብዛቱን ትነግረኝ ዘንድ እሻለሁ›› አሏቸው፡፡ አባ ጳውሊም ወደፊት ስለሚመጡ መነኮሳት በመጸለይ ወደ ሰማይ ካዩ በኋላ በመጀመርያ ፈገግ አሉ፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ምን አየህ?›› ቢሏቸው አባ ጳውሊ ‹‹ነጫጭ ርግቦች በጠፈር መልተው አንተ እየመራሃቸው ተከትለውህ ሲሄዱ አየሁ›› አሏቸው፡፡ ‹‹ይህስ ምንድን ነው?›› ቢሏቸው ‹‹እሊህማ በዚህ በቆቡ የምትወልዳቸው ንጹሐን ጻድቃን ልጆችህ ናቸው›› አሏቸው፡፡ ‹‹ሁለተኛ አመልክትልኝ›› አሏቸው፡፡ ጳውሊም ካመለክቱ በኋላ አዝነውና ተከፍተው ተመለከቷቸው፡፡ ‹‹ምነው?›› ቢሏቸው ‹‹በክንፋቸው ጥቁር ተቀላቅሎባቸው አየሁ›› አሉ፡፡ ‹‹ምንድን ናቸው?›› ቢሏቸው ‹‹ጽድቅና ኀጢአት እየቀላቀሉ የሚሠሩ ልጆችህ ናቸው›› አሏቸው፡፡ እንጦንስም ካዘኑ በኋላ ‹‹ሦስተኛም አመልክትልኝ›› አሏቸው፡፡ አባ ጳውሊም ለሦስተኛ ጊዜ ካመለከቱ በኋላ በድንጋጤ ቃላቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ምነው?›› ቢሏቸው አባ ጳውሊ እንዲህ አሉ፡- ‹‹ነገር ግን በመጨረሻ ዘመን የሚነሡቱ እንደ ቁራ ጠቁረው አየሁዋቸው›› አሉ፡፡ ‹‹ምንድን ናቸው?›› ቢሏቸው ‹‹ሀሳሲያነ ሢመት (ሹመት ፈላጊዎች)፣ መፍቀሪያነ ንዋይ (ገንዘብ የሚወዱ) እና ከመኳንንትም ጋር በጥዋት ማዕድ የሚቀመጡ በፍጻሜ ዘመን የሚነሡ ኀጥአን ልጆችህ ናቸው›› አሏቸው፡፡ ይህን ጊዜ አባ እንጦንስ ‹‹ያለ ንስሓ ባይጠራቸው እስኪ አመልክትልኝ›› አሉ፡፡ አባ ጳውሊም አመለከቱ ነገር ግን የዚህ ምላሽ አልመጣላቸውም፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ጳውሊ አባ እንጦንስን ወደ በዓታቸው ሄደው ቈስጠንጢኖስ ለሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ የሰጣቸውንና አትናቴዎስ ደግሞ ለእሳቸው የሰጧቸውን የከበረች ልብስ አምጥተው በእርሷ ይገንዟቸው ዘንድ ጠየቋቸው፡፡ አባ እንጦንስም አባ ጳውሊ የተሰውረውን ሁሉ በማወቃቸው አደነቁ፡፡ ዳግመኛም አባ ጳውሊ ስለ ቆቡ አባ እንጦንስን ‹‹እንግዲህ ይህን ከራስህ ያደረግኸውን ለኔ ስጠኝ ላንተ ሌላ ሠርተህ አድርግ›› አሏቸው፡፡ አባ እንጦንስም ‹‹ይህንንስ እንዳልሰጥህ ከባለቤቱ ተቀብዬዋለሁ፡፡ ነገር ግን ሥራውን ለምጄዋለሁ ሌላ ሠርቼ ላምጣልህ›› አሏቸው፡፡ ጳውሊም ‹‹እንግዲያስ አትዘግይ ቶሎ ሠርተህ አምጣልኝ›› አሏቸው፡፡ እንጦንስም የ2 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ወደ በዓታቸው ሄደው ቆቡን ሠርተው ይዘው ሲመጡ ጳውሊ ዐርፈው ነፍሳቸውን መላእክተ ብርሃን ይዘዋት ሲያርጉ ተመለከቱ፡፡ መላእክቱም ‹‹ጳውሊ ዐርፏልና ሄደህ ቅበረው›› አሏቸው፡፡ ‹‹ይህንሳ የያዝኩትን ቆብ ልተወውን?›› ቢሏቸው፡፡ ‹‹አትተው አድርግለት›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ይህም በምንኩስና የሠሩት ሥራ ከንቱ እንዳይደለ ለማጠየቅ ነው፡፡ አባ እንጦንስም ቢሄዱ አባ ጳውሊ መጽሐፋቸውን ታቅፈው፣ አጽፋቸውን ተጎናጽፈው፣ ከበዓታቸው ዐርፈው አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም የአባ ጳውሊን ሥጋ በልብሱ ሸፍነው በጸሎታቸው እንዲያስቧቸው እየተማጸኑ አለቀሱ፡፡ የሥጋቸውንም ጉዳይ ከእሳቸው ጋር እንዳልተማከሩ ሲያስቡ የታዘዙ አንበሶች መጥተው እጅ ከነሷቸውና እግራቸውን ከላሱ በኋላ የኣበ ጳውሊን ሥጋ የሚቀብሩበትን ቦታ አሳይተዋቸው ቆፈሩላቸው፡፡ አንበሶቹም ቆፍረው ሲጨርሱ ወጥተው ሰግደውላቸው እሳቸውም ባርከዋቸው ሄዱ፡፡ አባ ጳውሊንም በክብር ከቀበሯቸው በኋላ ወደ እስክንድርያ ሄደው ለአባ አትናቴዎስ የሆነውን ሁሉ ከነገሯቸው በኋላ የሰሌን አጽፋቸውን ሰጧቸው፡፡
የከበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስም ያችን የአባ ጳውሊን አጽፍ በክብር አስቀምጠው በዓመት ሦስት ጊዜ ብቻ ማለትም በልደት፣ በጥምቀትና በትንሣኤ በዓል ብቻ ይለብሷት ነበር፡፡ በሞተም ሰው ላይ ጥለዋት ሙት አስነሥተውባታል፡፡
የርዕሰ ገዳማውያን የአቡነ ጳውሊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ እና የማይፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት
እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት
ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት
እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት
ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው
ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም;
ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ
ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና
ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም
በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር
ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13
ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ
አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ
ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን
እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው::
ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ
አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::
===//============
በስሙነ ሕማማት በሚገኙ ዕለታት ስያሜ እና የተፈፀመባቸው ድርጊት:-
1ኛ ዕለት እሁድ ዕለተ ሆሳዕና
ሆሳዕና፡- የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን መድኃኒት፣ ‹‹አቤቱ እባክህን አሁን አድን›› የሚል ትርጉም አለው፡፡ (መዝ. 117፥25) ይህ በዓል በኦሪት (በብሉይ) የመጸለት 7ኛ ዕለት ሲሆን ለሐዲሱ ኪዳን ግን ከትንሣኤ በፊት ያለ እሑድ የሚከበር ነው፡፡ (ዘሌ.23፥39-44/ማር.11፥10/ዮሐ.12፥13)
በዚህ ዕለት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችን በአህያዋና በውርንጭላዋ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በሚገባበት ጊዜ ሕዝቡም የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት በማለት ማመስገናቸው ይታስብበታል (ዘፍ.49፥11/ሕዝ.9፥9-10/ኢሳ.40፥10/ዮሐ.12፥13)
ከላይ እንደተመለከትነው የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ ማመስገን በሕግ ከመነገሩ በፊት (ዘሌ.23፥39-44) አባታችን አብርሃም ይስሐቅን የመውለዱ ተስፋ በተፈጸመለት ጊዜ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ አመስግኗል፡፡ (መ.ኩፋ.13፥21) በመቀጠልም ሕዝብ እስራኤል በሕግ ታዘው ይፈጽሙት ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- ባሕረ ኤርትራ በተሸገሩ ጊዜ፣ ዮዲት ጠላትዋን ድል ባደረገች ጊዜ ይህንን ሥርዓት ፈጽመዋል፡፡ በዘመነ ሐዲስም ጌታችንን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው አመስግነውታል፡፡ (ማቴ.21፥1-11/ማር.11፥1-11/ ዮሐ.12፥12-16) ፡፡ ዛሬም ምዕመናን ከምሥጋናውም በረከትን ለማግኘት ተሳታፊዎች ለመሆን በካህናት የተባረከውን የዘንባባ ዝንጣፊ ወደ ቤታቸው ይወስዳሉ፡፡ በዚህ ዕለት ከሌሎች ጊዜ በተለየ ከበሮ ጸናጽል የሚያጅበው የምሥጋና መዝሙር የሌሊት ማኅሌት ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ለስሙነ ሕማማት ሁሉ የሚሆን ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግበት ዕለት ነው፡፡
2ኛ ዕለት ሰኞ
ይህ ዕለት አንጽሖተ ቤተ መቅደስ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለተ ነው፡፡ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል እንደተገለጠልን ጌታችን ከቢታንያ ወጥቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ተራበ፡፡ በለስም ከሩቅ አየ፣ በለስዋ ግን ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ምንም አላገኘባትም ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ አይገኝብሽ ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር አላት ያን ጊዜውንም በለሲቱ ደርቃለች (ማር.11፥12-19/ማቴ.21፥19/ሉቃ.1945-46)
በለስ የተባለች ኦሪት ናት፡- በለስ አገኘ ማለቱ ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት ሲል ነው፡፡ ወደ እርስዋም ሄደ ማለት ፈጻሜ ሕግ ተባለ (ሥርዓተ ኦሪትን ማለት በ8 ቀን መገዘር በ40 ቀን መሥዋዕት ማቅረብን… እየፈጸመ አደገ) ማለት ነው፣ ፍሬ አላገኘባትም፡. ሕግ ከመባል …..ድኅነትን አላደረገባትም ፍሬ አይገኝብሽ አላት ሲል፡- ባንቺ ድኅንነት አይደረግ አላት፡፡ ይህም ቅዱስ ዳዊት ‹‹መሥዋዕትን ቁርባንን አልወደድሁም ሥጋህን አንጻልኝ፣ የሚቃጠለውንና ስለኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም ሲል የኦሪትን ሕግ (አሠርቱ ትዕዛዛትን) አሳለፋቸው ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደነገረን በመሥዋዕተ ኦሪት ፍፁም ድኅንነት አለመገኘቱን አውቆ ማሳለፉን እና ፍፁም ድኅንነት የምናገኝበትን ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡›› አንድም በለስ ያለው ኃጢአትን ነው፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነ ኃጢአትን በዚህ ዓለም ሰፍና አገኛት፡፡ ወደ እርሷ ሄደ ፍሬም አላገኘባትም ማለት በአይሁድ አንደበት በሐሰት ኃጢአተኛ ተባለ እንጂ (ስለ እኛ መተላለፍ እንደበደለኛ ተቆጠረ እንጂ) ኃጢአትን አልሠራም ሲል ነው፡፡ ፍሬ አይገኝብሽ ሲል፡- ባንቺ በመጣ ፍዳ የሚያዝ አይኑር አላት ማለት ነው፡፡
ከዚህ በመቀጠል ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፡፡ ቤተ መቅደሱም ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ በዚያ ያሉትን ሁሉ አስወጣቸው፡፡ ይኸም በጠቅላላው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ለጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኙን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ማቴ.21፥12-17/ማር.11፥15-24/ሉቃ.19፥4)
ይቀጥላል …..
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::

2. የመላእክት በሩካቤ መታማት! Part Two (በአማን ነጸረ)

2. የመላእክት በሩካቤ መታማት!
መላእክት እንደማያገቡና እንደማይጋቡ ጌታ በማቴ.22 ቁ 30 ነግሮናል፡፡በሌላ በኩል በዘፍጥረት 6 ቁ.2 ‹‹የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፤ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ለመሆኑ እነዚህ በዘፍጥረት ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች››፣ወይም በግእዙ ‹‹ደቂቀ እግዚአብሔር››፣በእንግሊዝኛው <<Sons of God>> የተባሉ ፍጥረታት እነማን ይሆኑ? በሚል ጥያቄ ሲቀርብ ከሚሰጡት 3 መልሶች አንዱ መላእክት ሳይሆኑ አይቀርም የሚል ነው፡፡3ቱን ብሂሎች በጥቂቱ እንይ፡፡ብሂሎቹ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› የተባሉት፡- (1)አላውያን ነገሥታት ናቸው፣(2) መላእክት ናቸው፣(3) ደቂቀ ሴት ናቸው በሚሉ መላ ምቶች ዙሪያ ይሽከረከራሉ፡፡
2.1 አላውያን ነገሥታት (Despot) ናቸው የሚሉ የሚያቀርቧቸው ጥቅሶች አሉ፡፡(1) ‹‹አንሰ እቤ ‹አማልክት› አንትሙ ‹ወደቂቀ ልዑል› ኵልክሙ–እኔ ግን አማልክት ናችሁ ሁላችሁም ‹የልዑል ልጆች ናችሁ› እላለሁ›› የሚለው መዝ 81 ቁ. 6፣(2) በትንቢተ ዳንኤል 3 ቁ. 26 ‹‹የአራተኛውም መልአክ ‹የአማልክትን ልጅ› ይመስላል›› የሚሉት እና (3) በዘፍጥ 4 ቁ. 17 የቃየል ልጆች ከተማ መመስረታቸው መጻፉ እንዲሁም በዘፍጥ 6 ቁ.4 ጀምሮ የተጠቀሱት ኔፊሊም (Nephilim) ኃያልነት ድምር ነው ለኣላዊው ብሂል መነሻ፡፡ሆኖም ይሕ አመለካከት በፈንጆቹ ነው የሚንጸባረቀው፡፡የኛን ሊቃውንት አቋም በዚህ ቃል ዙሪያ እንይ ብንል ‹‹መለከ›› የሚለውን ቃል ‹‹ገዛ››፣‹‹ተመልአከ›› የሚለውንም ‹‹አለቃ ሆነ›› ብለው ይፈቱታል፡፡‹‹ኒቆዲሞስ…መልአኮሙ ለአይሑድ›› የሚል ቃል በቅ/ያሬድ ጾመ ድጓ ይደጋገማል፤ትርጉሙ ‹‹የአይሑድ አለቃ›› ማለት ነው፤መልአክ ማለት አይደለም፡፡ይሕን ግምት ውስጥ አስገብተን ሊቃውንቶቻችን ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› የተባለውን ትርጉም እንደ ፈረንጆቹ ለአላውያን ነገሥታት(የሕዝብ አለቆች) ሰጥተው ይተረጉሙታል ልንል እንችል ይሆናል፡፡ሆኖም እንሳሳተለን!ምክንያቱም አክሲማሮስ እንደሚተርከው ከዳዊት ጀምሮ ነው የነገሥታት ዘመን መቆጠር የሚጀምረው፡፡ አባቶቻችን የነቃየልን ዘመን ‹‹ዘመነ አበው›› እንጂ ‹‹ዘመነ-ነገሥት››(የአምባገነን አለቆች ዘመን) አይሉትም፡፡የዳንኤል ንባብም ቢሆን የተጻፈው ቅዱስ ገብርኤልን ለማመላከት ነው ተብሎ ታሪኩ ለታሕሳስ ገብርኤል ይተረካል፡፡ቅዱስ ያሬድ ‹‹ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር›› ይላል ምዕራፍ በተሰኘ ድርሰቱ፡፡Gabriel የሚለውን ቃል ለጎግል ብናጎርሰው የሚሰጠን ትርጓሜ Son of God የሚል ነው፡፡በአጠቃላይ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይሕ ለዘፍጥረት 6 ቁ.1-4 ላለው ቃል የተቀመጠ ‹‹የአላዊነት›› ትርጉም ተቀባይነት የለውም ብንል የምንሸነፍ አይመስለኝም፡፡
2.2 ነገሥታት ካልሆኑ ‹‹መላእክት›› ናቸዋ!በሚል የሚቀርበው መከራከሪያ ሌላኛው ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› ትርጓሜ ነው፡፡የመከራከሪያውን መሪ ጥቅሶች እናመላክት፡፡
(1) ኢዮብ 2 ቁ.1 ‹‹ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤‹የአምላክ ልጆች› በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ››፣
(2) ኢዮብ 38 ቁ.7 ‹‹አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ ‹የእግዚአብሔር ልጆች› ሁሉ እልል ሲሉ መሰረቶቿ በምን ተተክለው ነበር››፡፡
(3) 2ኛ ጴጥ 2 ቁ.4 ‹‹እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጭለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠብቁ አሳልፎ ሰጣቸው››፡፡
(4) ይሑዳ ቁ.6-7 ‹‹መኖሪያቸውንም እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን ‹መላእክት› በዘለዓለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል፡፡እንዲሁም ‹እንደ እነርሱ› ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘለዓለም እሳት እየተቃጠሉ ምሳሌ ሆነዋል፡፡ዘፍጥ 19 ቁ 24፡፡››፡፡
(5) ኩፋሌ 6 ቁ.9 ‹‹የአዳም ልጆች በዓለሙ ሁሉ ይበዙ ዘንድ በጀመሩ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው፡፡‹የእግዚአብሔር መላእክትም› በዚሁ ኢዮቤልዩ በአንዲቱ ዓመት እነዚህን አዩአቸው…ሚስት ሊሆኑአቸው አገቡአቸው፤ወንዶች ልጆችንም ወለዱላቸው እነዚህም ረዓይት ናቸው››፡፡
(6) ከላይ ያሉት ጥቅሶችና መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 2 ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› የተባሉ መላእክት ከሴቶች ጋር ልቅ ሩካቤ ፈጽመው ረዓይትን ወልደዋል ለሚለው አመለካከት ዋና መነሻ ሆነዋል፡፡የኢዮብ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› የሚሉ ቃላት ቀጥታ መላእክትን ስለሚያመላክቱ ከዘፍጥር 6ቱ ቃል ጋር ተናበው ‹‹የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ›› የተባለው ለመላእክት ነው የሚለውን አመለካከት ለመደገፍ ውለዋል፡፡የጴጥሮስና የይሑዳ መልእክታት በመላእክት የዝሙታዊ ድርጊትና ቅጣት መገለጫነት እንዲሁም ኩፋሌና ሄኖክ የመላእክትና የሰው ሩካቤ-ሥጋ ስለመኖሩ ቃል በቃል ጽፈዋል ተብለው በፈረንጅ ደባትር በተደጋጋሚ ተጠቅሰዋል፡፡ደባትሩ እንዳሻቸው!እነሱ እህ!ካሏቸው የማይሉት የለም፡፡እኔ ሀገራዊ የደብተራ ካባዬን ደርቤ ቀጥታ ወደ 3ኛው ኦርቶዶክሳዊ ብሂል እሻገራለሁ፡፡
2.3 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አቋም ‹‹የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ›› በሚለው የዘፍጥረት ጥቅስ ውስጥ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› ተብለው የተጠቀሱት ‹ሰማያውያን መላእክት አይደሉም፤ደቂቀ ሴት እንጂ› የሚል ነው፡፡የፊደል ተራ እየሰጠን የቻልነውን ያህል ከቤተክርስቲያናችን ያገኘናቸውን ማስረጃዎች እንጠቃቅስ!ከዚያ በፊት ግን ሴት ማለት አቤል በቃየል እጅ ከተገደለ በኋላ በአቤል ምትክ ለአዳምና ሔዋን የተወለደላቸው ወንድ ልጅ እንጂ እንደ አማርኛችን አነጋገር አንስታይ ጾታ ለመግለጽ የዋለ ቃል አለመሆኑ ይሰመርበት፡፡የስሙ ትርጓሜ ‹‹ምትክ›› ማለት መሆኑ በዘፍጥረት 4 ተጽፏል፡፡የሴት ዘሮች (ደቂቀ ሴት) ከቃየል ልጆች የተለዩ ቅዱሳን/ቅዱሳት፣ጸሎተኞች፣ምድር በጥፋት ውሃ ስትጠፋ በኖኅ በኩል ዘራቸው ተርፎ ከልጅ ልጃቸው ጌታ የተወለደ፣ለእግዚአብሔር ራሳቸውን የለዩ፣የመጀመሪያው ነቢይ፣ፀሐፊ፣መናኝና ወደ ብሔረ ሕያዋን የተነጠቀው ሄኖክ የወጣባቸው ቀደምት ቅዱሳን/ቅዱሳት ናቸው፡፡በቅድስናቸውና በንጽሕ አጠባበቃቸው የተነሳ መላእክት ተብለዋል፡፡ለዝርዝሩ ኦርቶዶክሳውያን መጻሕፍት ይጠሩ፡-
ሀ. መ/ር ተክለ ሚካኤል በተባሉ መተርጉም በኩል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት እጃችን የገባው ገድለ አዳም ደቂቀ ሴትን መላእክት ያሰኛቸውን አኗኗር እንዲህ ይተርከዋል፤ ‹‹አዳም ከሞተ በኋላም ሴት ከቃኤል ልጆች የእርሱን ልጅ፣የልጅ ልጆቹን ለየ፡፡ቃየልና ዘሩም አቤልን በገደለበት በስተምዕራብ ጫፍ(እንደ ዘፍ.4 ቁ 16 ከዔደን በስተምራቅ) ወረዱ፡፡ሴትና ልጆቹ ግን በቤተ መዛግብት በሚገኘው ተራራ ደቡባዊ ክፍል ተቀመጡ፡፡…ከእነርሱ(ከሴት ልጆች) አንዱ ስንኳን ወደ ቃኤል ልጆች ይወርድ ዘንድ አልፈቀደም፡፡ስለ ንጽሕናቸውና ‹ስለወደቁት ሠራዊተ-መላእክት› ፈንታ የእግዚአብሔር ልጆች ተባሉ›› ሲል መላእክት የተባሉበትን ምስጢር ይገልጽልናል(ገድለ አዳም፡ገ.122)፡፡አዳም ከገነት ከወጣ በኋላ በሩ ላይ ሱራፊ ቢቆምም በቀቢጸ-ተስፋ ርቆ አልሄደም፡፡በእግረ-ገነት ሆኖ መላእክት በአፀደ-ገነት ሲያመሰግኑ ይሰማ ነበር፤ልጆቹም ርቆ ከሄደው ቃየልና ቤተሰቡ ውጭ የመላእክትን ምስጋና እየሰሙ ‹‹…እነርሱም በገነት መንገድ ያመሰግኑ፣ያከብሩም ነበር፡፡…ዳግመኛ ገነት ከእነርሱ ሩቅ አልነበረችም፡፡በመንፈሳዊ/በመልአክ/ ክንድ 15 ክንድ ነው፤ይህም በሰው 45 ክንድ (ወይም 22.5ሜትር) ይሆናል፡፡ሴትና ልጆቹም በተራራው ላይና በተራራው ታች ይኖሩ ነበር፡፡አይዘሩም፤አይለቅሙም፡፡ሥጋዊ ምግብም ስንዴም አያዘጋጁም፡፡ቁርባን ብቻ ነው እንጂ፡፡ከማደርያቸው ተራራም ከሚጣፍጡ ዕፀዋት ፍሬ ይመገቡ ነበር›› ይላቸዋል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.124)፡፡ደቂ ሴት በዚህ የምስጋና ሕይወታቸው የተነሳ ‹‹እግዚአብሔርም መላእክት/ልጆቼ/አላቸው፤ታላቅ ደስታንም ተደሰተባቸው›› ተብሎላቸዋል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.139)፡፡እንዲህ የተባለላቸው ደቂቀ-ሴት ቃየል አቤልን ገድሎ ደርቦ ካገባት ውቢቷ መንትያ እህቱ ሉድ በተወለዱ ቆነጃጅት ተማርከው ከደብር ቅዱስ ቁልቁል ተመዝገዘጉ፡፡መላእክት የሰው ልጆችን አገቡ የተባለ በዚህ ምክንያት ነው፡፡አወዳደቃቸውን እንይ!
ለ. የኦሪት ዘፍጥረት 6 ቁ.2 ትርጓሜ ፡- ‹‹ወሶበ ርእዩ ደቂቀ እግዚአብሔር ከመ ሠናያት እማንቱ አዋልደ ደቂቀ እጓለ እመሕያው ነሥኡ ሎሙ አንስትያ እምእለ ኃረዩ፡፡…የእግዚአብሔር ልጆች የሚሆኑት ደቂቀ ሴት ደቂቀ ቃየልን መልከ መልካሞች እንደሆኑ ባዩ ጊዜ አንዱም አንዱ የወደዱዋትን የመረጡዋትን አንድ-አንድ አገቡ፤በአንዲት ሚስት ፀኑ ማለት አይደለም የጊዜውን መናገር ነው›› ይላል(መጻሕፍተ ብሉያት ክልኤቱ፡ገ.54)፡፡ በምን አይነት እይታ እንደወቀዱ ሲተርክ፤‹‹ከዕለታትም አንድ ቀን ደቂቀ ቃየል ሐፍረታቸውን አውጥተው እንደባዝራ እንደ አለሌ ሲንጠላጠሉ አይተው በሐፀ ዝሙት ተነደፉ፤ንዑ ንረድ ወንንሣዕ አሐተ አሐተ እምአዋልደ ደቂቀ እጓለ እመሕያው(ኑ!እንውረድ!ከሰው ልጆች ቆነጃጅት አንድ-አንድ እንውሰድ) ብለው ወርደው ቀርተዋል›› በማለት ነው(ዝኒ ከማሁ)፡፡‹‹ሰው›› የተባለ ቃኤል ነው፤‹‹መልአክ›› የተባለ ሴት!
ሐ. ቀሌምንጦስ ደቂቀ ሴት እንዴት ከንጽሕና ወደ ርኵሰት እንደወረዱ የሚተርክበት ቋንቋ እጅጉን ገላጭ ነውና እንሂድበት፤‹‹…የሴት ልጆች በሰይጣን ተታልለው የቃየል ልጆችን መከተል ጀመሩ፡፡በዚሁ በጣፈጠውም ዘፈን ዜማ ተመሰጡ፡፡ይህንንም መነሻ አርድገው ከደብር ቅዱስ እንደወረዱ ከክፉዎች የቃየል ልጆች ጋር ተጨመሩ፡፡የሴት ልጆች በዘፈን ተጠምደው ወደቁ፡፡በመብል፣በመጠጥና በዝሙት ተያዙ፡፡ሴቶች ጎልማሳዎችን በመከተል ተሯሯጡ፡፡ወንዶች እንደ ዱር አውሬ ዕራቁታቸውን እየሆኑ በገበያው ይዞሩ ጀመር፡፡…እጅግ ተሳሳቱ ሥጋቸውንም አረከሱ፡፡በቃየል ልጆች አመነዘሩ፤ብዙ የረከሰ አድራጎትን ፈጸሙ፤…ሰውነታቸውን አሳደፉ፡፡ነፍሳቸውን ረስተው በኃጢኣት ተጠመዱ፡፡…እንደ እንስሳት ሆነው ተገናኙ፡፡ግልጽ የአመንዝራነት ተግባር ፈጸሙ፡፡ሁለት ሦስት ሆነው ባንዲት ሴት ላይ ተገናኙ፤ምድርንም በመላዋ አረከሷት፡፡…በወደቀና በረከሰው ውድቀታቸው የሚያሰሙት ጩኸትና ዋይታቸው እንደ ባዝራ ፈረስ እስከ ደብር ቅዱስ ተሰማ›› ብሏል(መጽሐፈ ቀሌምንጦስ፣ምዕ.3 ቁ 40-44፡ገ.33-34)፡፡እነዚያ ከገነት በ22.5ሜትር ርቀት ላይ የነበሩ ንጹሐንና ንጹሐት ደቂቀ ሴት ባንድ ጊዜ እንዲህ ረከሱ፡፡ያገራችን ሰው ‹‹ጨረቃ ጥሶ የመጣ ዝናብ፣ቆብ ቀዶ የመጣ ሰይጣን መመለሻ የለውም›› ያለው የደቂቀ ሴትን ታሪክ ሰምቶ መሆን አለበት!
መ. በቀደመ ግብራቸው መላእክት የተባሉትን የደቂቀ ሴት በዝሙት የመውደቅ ታሪክ በመጽሐፈ ሄኖክና በመጽሐፈ ኩፋሌ እንዝጋው፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እነዚህን ቀደምት መጻሕፍት በብራና ጽፋ፣ደጉሳ፣ኋላ ኅትመት ሲመጣም ነጠላና አንድምታ ትርጓሜያቸውን አዘጋጅታ ቁጥራቸውን ከቅዱሳት መጻሕፍት በማካተቷ ያልተወራባት ነውር፣ያልተነገረባት ሐሜት የለም፡፡የሐሜቱ ትልቁ መነሻ 2ቱ መጻሕፍት ‹‹መላእክት ሩካቤ-ሥጋ ያደርጋሉ›› የሚል ምንባብ አለባቸው የሚል ነው፡፡ርእሱ በአጋጣሚ ሲነሳ ከዚህ በፊትም ነካክተነዋል፤ቢሆንም ሩካቤውን የተመለከተውን አመለካከት ነጥሎ ዳግም ማየቱ አይከፋም፡፡ዘርዘር አድርገን ሐሜቱን በኦርቶዶክሳዊ መንሽ እናበጥረው–እንዳቅማችን፡-
(1) በኦሪት ዘፍጥረት ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› ወይም በግእዙ ‹‹ደቂቀ-እግዚአብሔር›› የሚለው ምንባብ በኢኦተቤክ ‹‹የኦሪት ዘፍጥረትና ዘፀዐት ክፋይ (ኩፋሌ)›› በምንለው መጽሐፈ ኩፋሌ 6 ቁ.9 ‹‹የእግዚአብሔር መላእክት›› ወይም በግእዙ ‹‹መላእክተ-እግዚአብሔር›› ተብሎ ነው ደረቁ ንባብ የቀረበው፡፡መጋቤ ብሉይ ሠይፈሥላሴ ዮሐንስ ኩፋሌ 6.ቁ 9ን፤‹‹ደቂቀ ሴት…በደብር ቅዱስ እንደ መላእክት ቅዱስ!ቅዱስ!ቅዱስ! እያልን እንኖራለን፣ከደቂቀ ቃየል አንጋባም ብለው ነበርና ስለዚህ ‹መላእክት› አላቸው›› ሲሉ ትርጓሜውን አሰምተውናል፡፡መላእክት=ደቂቀ ሴት!
(2) ለቁጥር የሚያታክቱ ፈረንጅ የሥነ መለኰት ‹‹ተማራማሪዎች›› መጽሐፈ ሄኖክን ስለመላእክትና ስለሰው ሩካቤ ጽፏል እያሉ ያሳስታሉ፡፡እሱ ግን በግልጽ በምዕራፍ 4 ቁ.82-83፡- ‹‹አባቶቻቸው ከደብር ቅዱስ ከወረዱ ከደቂቀ ሴት ተወልደው ነበርና ወገኖቻቸው ከሚሆኑ ከሴት ክፉ ልጆች ተወለዱ፡፡ቀድሞ የንጽሕና መሰረት የነበሩ እነዚህም በዚህ ዓለም ክፉ ልጆች ይሆናሉ፤ክፉ ልጆችም ይባላሉ›› ሲል መላእክት የተባሉት ደቂቀ ሴት እንደነበሩ ይጠቁመናል፡፡
(3) በደቂቀ ሴትና በደቂቀ ቃየል ተራክቦ የተወለዱት ልጆች በግእዙ ‹‹ያርብሕ››፣በአንድምታው አማርኛ ‹‹ረዓይት››፣በመደበኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ‹‹ኃያላን››፣በእንግሊዝኛ‹‹Giants›› ይባላሉ፡፡ግእዛችን ‹‹ኔፊሊም›› የሚለውን ቃል አይጠቀምም፤‹‹ያርብሕ›› ነው የሚላቸው–አርበኛ ማለት ነው፡፡
(4) እርግጥ ነው፤የመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 2 ትርጓሜ ረዓይት 2ትና 3ሺሕ ክንድ የሚረዝሙ ግዙፍ ፍጥረታት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ሆኖም ግዝፈታቸው ከመላእክት ስለተወለዱ እንዳልሆነ እዚያው ዝቅ ብሎ በምዕራፍ 5 ቁ.1 ‹‹ወገኖቻቸው ከሚሆኑ ከደቂቀ ሴት የተወለዱ የረዓይት ሞታቸው በወጡበት ቦታ ነው›› ይላል፡፡ከሥጋ ለባሽ የተገኙ ሥጋ ለባሾች መሆናቸውን አልካደም፡፡ግዝፈታቸውም በዘፍጥረት 6 ቁ. 4 በግልጽ የተመለከተ ነው፤ልዩነቱ ሄኖክ ቁመታቸውን በክንድ አስቀመጠው፡፡
(5) የሄኖክ 2 አንድምታ ‹‹…የሰማያት ልጆች እነርሱን አይተው ወደዱአቸው፤መላእክት የተባሉ ደቂቀ ሴት ናቸው፤‹ወሰምዮ መልአከ በእንተ ንጽሑ› እንዲል ›› ይላል (መጽሐፈ ሄኖክ፣አንድምታ ትርጓሜ፡ገ.10)፡፡ሴትን ‹‹ስለ ንጽሕናው መልአክ ብሎ ጠራው›› እያለን ነው!
(6) እንደ መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 2 አንድምታ ‹‹የእግዚአብሄር መላእክት›› የሚለው ቃል ባለክንፍ ረቂቃን መላእክትን ሳይሆን ደቂቀ ሴትን የሚገልጽ አነጋገር ነው፡፡መላእክት የተባሉትም፡- በንጽሕናቸው፣ከፍ ካለው ደብር ከደብር ቅዱስ የመላእክትን ምስጋና እየሰሙና እያመሰገኑ በመኖራቸው፣መዓርጋቸው ከፍ ካለው መዓርግ ስለደረሰ ነው፡፡እንጂ ሥጋ ለባሽነታቸው አልተዘነጋም፤ቃሉም ለመላእክት ሳይሆን ለነሱ የተነገረ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው!ምነው እኛስ ‹‹እከሌ እኮ መልአክ ነው›› እንል የለ፤ሄኖክና ኩፋሌም እንዲያ ማለታቸው ነው፡፡
(7) የኦሪት ዘፍጥረት ከምዕራፍ 6 እስከ ምዕራ 11 የሚዘልቁ የፈጣሪ ቁጣ፣እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠሩ መፀፀቱ፣ኖኅን ለይቶ አስቀርቶ ሌላውን ትውልድ መደምሰሱ፣…የሚያሳዩት ከላይ በቀሌምንጦስና በዘፍጥረት አንድምታ የተገለጹ ነገር ግን በመደበኛው መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር ያልተገለጹ ኃጢአቶች በቃየልና በሴት ልጆች መፈጸማቸውን ነው፡፡
(8) ዘፍጥ 6 ቁ.5-6 ‹‹እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ። እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ። እግዚአብሔርም። የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና አለ›› ከማለት በቀር እግዚአብሔርን ያስቀየሙ የሰው ልጅ ዝርዝር የርኵሰት ተግባራትን አይገልጽም፡፡ይሕን ክፍተት ለመሙላት የኛዎቹን አንድምታዎች፣ትውፊታውያኑን መጻሕፍት፣ኩፋሌንና ሄኖክን ነጭ ደባትር ሳይቀሩ ይጠቀሙባቸዋል–መልሰው ለማጣጣል ቢፋጠኑም!
(9) ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ‹‹ረዓይት›› የሚለውን ቃል በመጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ገጽ 845 ሲያብራሩ፤‹‹ሰብአ ትካት፤እኩያን ዐርበኞች፣ርስ በርሳቸው የሚባሉ፣ኃይላቸውና መጠናቸው ከሰው ልክ ያለፈ(ና) የተረፈ፤እንደ ጥድና ዝግባ ያሉ፤ከጥድ ከዝግባም የሚበልጡ፡፡ከፍ ከፍ የሚሉ ገናኖች፣ረዣዥሞች፡፡ደቂቀ ሴት ያባታቸውን ሕግ አፍርሰው፣ርግማኑን ጥሰው ከቃየል ልጆች ቢጋቡ እንደዚህ ያሉ ሕዝብ ተወልደዋል፡፡ዘፍ.6 ቁ1.-7›› ሲሉ በመጽሐፈ ኄኖክ፣በምሳሌና በጥበብ የሚገኙ ግእዝ ኃይለ ቃላትን በማስረጃነት ጠቅሰዋል፡፡
(10) አንዳንድ ኦርቶዶክስን ለማደስ ‹‹የኃላፊነት ሹመት›› ለራሳቸው የሰጡ ቆናጽል ዘመዶቻችን ደግሞ የዘፍጥረት ምዕራፍ 6፣የይሑዳ ቁ.7፣የ2ኛ ጴጥ ምዕራፍ 2 የመሳሰሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ካነሱት ውጭ ኩፋሌና ሄኖክ የተለየ ቃል እንዳመጡ አድርገው ለተዛወሩበት ቡድን ማሊያ ማስተዋወቂያ ኩፋሌንና ሄኖክን ይሰዋሉ!ነውር!!!ያውም እኮ በ190ዎቹ መጀመሪያ በዘመቻ ፊልጶስ ፀረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ያሰለጠነንን፣በመጽሐፈ ሄኖክ ትርጓሜ ዙሪያ ተጠያቂ የነበረውን፣የኩፋሌንና የሄኖክን ትርጓሜ በመቅረጸ ደምጽ አኑሮልን ያለፈውን፣በ2000 ዓ.ም ከግእዙ ተስማምቶ ከኩፋሌና ሄኖክ ጋር ባንድ ላይ ተጠርዞ የወጣውን 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ በመሪነት ያዘጋጀውን፣ወዲህ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲያም ሲል ቤተሰቦቼ ከፈለቁባት ከማኅፀነ ግዮን በመፍለቁ የምኮራበትን ሊቅ መጋቤ ብሉይ ሠይፈሥላሴ ዮሐንስን ‹‹አባታችን›› እያሉ ነው ‹‹የኢኦተቤክ መላእክትና ሰው ተጋቡ የሚል ቅዱስ መጽሐፍ አላት›› እያሉ የሚፈላሰፉት፡፡ድንቄም ተፈላስፈዋል አያ!ተፈላስፈው ሞተዋል፡፡ይልቅስ ይህን በዚሁ አሳድረን ስለ ነገረ ሩካቤ ፈላስፎች የሚሉትን እንይ፤ከዚያ በፊት አንዲት ስርዋጽ….
ቀዳሚት ስርዋጽ፡- ሰው በቅድስት ሥላሴ አምሳል ተፈጥሯል ካልን ሥላሴ ጾታ አላቸውን?
ኦሪት ‹‹እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረው›› ትላለች፡፡ስለዚህ የሰው አካላዊ መዋቅርና ገጽታ የእግዚአብሔርን ይመስላል ማለት ነው፡፡እንደሱ ከሆነ ለቅድስት ሥላሴ እንደ ሰው የመራቢያ አካል አላቸው ማለት ይቻላልን?ጥያቄው ኅሊናችንን ሸምቀቅ ያደርጋል፡፡ቢሆንም ጥያቄው አዲስ አይደለም፡፡አበው አንስተውት የራሳቸውን አተያይ አኑረውልናል፡፡ከነጥያቄና መልሳቸው በራሳቸው ቋንቋ እንስማቸው! ‹‹የሥላሴ አባለ ዘርእ የላቸውም ካሉ ‹ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳሊነ› ብለው የፈጠሩት አዳም አባለ ዘርእ ይዞ ተገኘሳ?! ‹ለሥላሴ (አባለ ዘርእ) የላቸውም ማለት አካል ማጉደል አይሆንምን?!› ቢሉ ይህስ አካል ማጉደል አይባልም፡፡የማንኛቸው አለባቸው ይሏላ?!የአዳም አለባቸው እንዳንል ሔዋንን ፈጥረዋታል፡፡የሁለቱም አለባቸው ማለት ስድብ ነውና (ለሥም አጠራራቸው ምስጋና ይሑንና ‹ፍናፍንት› ያሰኝብናል)፡፡ስለዚህ ነገር ለሥላሴ አባለ ዘርእ የወንድም የሴትም የላቸውም ብሎ ያምኑ ዘንድ ይገባል፡፡የወንድም የላቸውም ካልን ‹አዳምን በማን አምሳል ፈጠሩታ?!› ቢሉ አዳምንስ መዋቲ ስለሆነ እንዲዋለድ ዘር እንዳይጠፋ አባለ ዘርእ ያለው አድርገው ፈጥረውታል፡፡…ለሥላሴ አባለ ዘርእ የሴትም የወንድም የላቸውም ካሉ ስለምን መጽሐፍ በሴትም በወንድም ይመስላቸዋል?!ቢሉ ይህስ የመጽሐፍ ልማድ ነው፡፡አባለ ዘርእ የሌለውን ሁሉ በሴትም በወንድም ይጠራል…››ይላል የቆጋዎች መጽሐፍ (ወልደ አብ፡ገ.77-78)፡፡
አባለ ዘርእ ሳይኖራቸው በወንድና ሴት አንቀጽ እየተለዋወጠ ከተጠሩት ውስጥ ነፍስን እናገኛለን፡፡ነፍስ በወንድ አንቀጽ ሲጠራ ‹‹መንፈስ እምከመ ወጽአ ኢይገብእ–ወጥቶ የማይመለስ መንፈስ ሥጋም እንደሆነ አስቦ…›› ይላል መዝ 77 ቁ.39፡፡‹‹እምከመ ወጽአ/ወጥቶ የማይመለስ›› የሚለው ሐረግ ነፍስን በተባእታይ ጾታ ይገልጻል፡፡ነፍስ በሴት አንቀጽ ስትቀርብ ‹‹አኀሥሥ ዘአፍቀረቶ ነፍስየ–ነፍሴ የወደደችውን…እፈልጋለሁ›› ትባላለች(መኃ.3ቁ2)፡፡ወንድነትና ሴትነት የሌላት ረቂቋ ነፍስ በአነጋገር በ2ቱም ፆታ ትጠራለች ማለት ነው፡፡ምሳሌው ለፀሐይም ይሠራል፡፡መጽሐፍ ፀሐይን ‹‹ፀሐይኒ አእመረ ምዕራቢኁ–ፀሐይ መግቢያውን ያውቃል›› ብሎ በመዝ 103 ቁ. 9 በወንድ አንቀጽ ይጠራዋል፤በሴት አንቀጽ እንዲሁ‹‹ ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ–እሳት ወደቀች ፀሐይንም አላዩአትም›› ይላታል ፀሐይን(መዝ.57 ቁ. 8)፡፡
ነፍስና ፀሐይ የተጠቀሱት ሥላሴን በሴትና ወንድ መጥራት ፆታ እንዳላቸው ለማመልከት ሳይሆን አጠራሩ የመጽሐፍ ልማድ ነው ለሚለው መከራከሪያ አስረጂ እንዲሆኑ ነው፡፡ሥላሴ በወንድ አምሳል ‹‹ቅዱስ!ቅዱስ!ቅዱስ!አሐዱ አምላክ›› ይባላሉ፡፡‹‹ቅዱስ›› የሚለው ቃል ለተባእት ነው የሚነገር፤አሐዱም እንዲሁ፡፡ለሴት ሲሆን አሐዱ ሳይሆን ‹‹አሐቲ›› ነው የምንል፡፡በዘፍጥረት 18 ቁ. 2 ያለው ‹‹ወናሁ ሠለስቱ ዕደው ይቀውሙ መልዕልቲሁ–እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ቁመው አያቸው›› የሚል ቃል ውስጥ የግእዙ ‹‹ዕደው›› ትርጉም ‹‹ወንዶች/ጎልማሶች›› ማለት ነው፡፡ስለዚህ ሥላሴ በወንድ አንቀጽም ይጠራሉ፡፡በሌላ በኩል ስለ ርኅራኄያቸው፣ስለ መጋቢነታቸው፣አርግዛ የምትወልድ እናት እናትነቷ እንደማይጠረጠር የፍጥረት አስገኝነታቸው ለማይጠረጠር ፈጣሪነታቸው በሴት አንጽ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› ይባላሉ፡፡‹‹ቅድስት›› ለሴት ብቻ የሚነገር የቅድስና ቃል ነው፡፡አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይህን ለመግለጽ ‹‹ኀበ ርኅራኄክሙ በዝኀ ወኀበ አልቦቱ መስፈርት፣እለ ትሰመዩ በሥመ ብእሲት፣ሥላሴ ዕደወ ምሕረት›› ሲል ርኅራኄያቸውን በሴት ከመጠራታቸው ጋር አያይዞ ተርኮታል፡፡በዚህ ርእስ ይብቃን፤ከዚህ በላይ ማለት አንችልም፡፡ሥሉስ ቅዱስን በሰጊድ እጅ ነስተን በእልባት ወደታጠፈው ርእሳችን እንመለስ…
3. ሩካቤ ሥጋ ከፍልስፍና አንጻር (ቁንጽል ንጻሬ)!
ነጮቹ ፈላስፎች በነገረ-ሩካቤ (Sexuality) ዙሪያ Metaphysical Sexual Pessimisim እና Metaphysical Sexual Optimisim በሚል እንደሚከፈሉ በዚህ http://www.iep.utm.edu/sexualit/ ተነግሮናል፡፡Metaphysical የሚለው ቃል በደርግ ዘመን በወጣው ሌኒኒስት ማርክሲስት መዝገበ ቃላት ‹‹ዲበ አካል›› ተብሎ ተተርጉሟል፤ከአካል በላይ የሆነ፣መንፈሳዊ ማለት ነው፡፡ሩካቤ ከሥጋዊም ባለፈ መንፈሳዊ ተመስጦ እንዳለው ለማመልከት ይመስላል የቃሉ ጠቋሚነት፡፡Pessimisim የሚለውን ‹‹ሕርመት/ትሕርምት›› ብለን ብንተረጉመው ያስኬዳል፡፡Optimisimን ‹‹ፍቅድ/መፍቅድ›› ብንለው ለቃሉ ትርጓሜ ይቀርባል፡፡ስናገጣጥማቸው 2ቱ ፍልስፍናዎች ‹‹ትሕርምተ-ሩካቤ- Sexual Pessimisim-›› እና ‹‹መፍቅደ-ሩካቤ–Sexual Optimisim›› ሊባሉ ይችላሉ፡፡ፈላስፎቹንም ‹‹ኅሩማነ-ሩካቤ››(ሩካቤን እንደ እርም የሚመለከቱ) እና ‹‹መፍቅድያነ-ሩካቤ››(ሩካቤን በበጎ የሚመለከቱ) ልንላቸው እንችላለን፡፡ፍልስፍናዎቹን በቁንጽል እጅግ በቁንጽል የድኩም ደብተራ ንባብ እንያቸው፡፡
3.1 ኅሩማነ-ሩካቤ (Pessimists) የተባሉት ፈላስፎች ሩካቤ ሥጋ አንድ ሰው ሌላውን ለፍትወት ማብረጃ የሚፈልግበት ሥርዓት በመሆኑ ከሩካቤ በፊትና በኋላ ሰውን እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ቁስ ወይም እንደ ዐላማ ማስፈጸሚያ መሳሪያ (Object of appetite) እንድናይ ያደርጋሉ ሲሉ ይተቹታል፡፡ከሩካቤ በፊት ተቃራኒ ጾታን ያልሆኑትን ሆኖ ለማሳመን አካላዊ (physical) ፣ ውሳጣዊ (psychological) ፣ ስሜታዊ (emotional) እና አእምሮአዊ (intellectual) ብልሃቶች ሁሉ ስለሚተገብሩ ሂደቱ ሰውን ከክቡር ተፈጥሮው ያወርዳል ይሉታል፡፡በሩካቤ ውስጥ ያለው ፍትወት (ፍላጎት) ትኩረቱ የተጓዳኙ ሰብእና ሳይሆን የተነሳሳው አባለ ዘርእ ተጣማጅ የሆነውና በዚያኛው ወገን ያለው የምኞት ማረፊያ የሆነ የተቃራኒ(?) ጾታ አባለ ዘርእ ነው፡፡በግብር መተዋወቅ ጊዜ 2ቱም አንዱ ባንዱ ልባቸው ተሰውሮ ራሳቸውንም ተጓዳኛቸውንም ይረሳሉ፤ይኸውም አንዱ ሌላውን እንደ መገልገያ (የእርካታ መሳርያ) ስለሚመለከት ነው፡፡
3.2 ስለሆነም ሩካቤ ለራስም ሆነ ለተጓዳኝ ክብረ-ሰብእና የኀሳር እንጂ የክብር ተግባር አይደለም ይላሉ እነ ኢማኑኤል ካንትና ቅዱስ ኦገስቲን፡፡በራሳቸው አማርኛ ‹‹…with its uncontrollable arousal, involuntary jerkings, and its yearning to master and consume the other person’s body. During the act, a person both loses control of himself and loses regard for the humanity of the other. Our sexuality is a threat to the other’s personhood; but the one who is in the grip of desire is also on the verge of losing his or her personhood.››. በእነ ካንት አመለካከት በ1ኛ ቆሮ 7 እንደተጻፈው ከሩካቤ መታቀብ ቀዳሚው የሕወት ምርጫ ነው፡፡ያ!ካልተቻለ ሩካቤ መደረግ ያለበት ሁለት የተለያየ ጾታ ያላቸው ተጋቢዎች አንድ ለአንድ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ለመዝለቅ ተስማምተው ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ ሆኖ እሱም ቢሆን ዘር ከመተካት ያለፈ ተራክቦ መሆን የለበትም፡፡ዘር ከመተካት ባለፈ ለፈቃደ-ሥጋ ብቻ የሚደረግ ሩካቤን አይደገፉም፡፡‹‹pessimistic metaphysicians of sexuality conclude that sexual activity is morally permissible only within marriage (of the lifelong, monogamous, heterosexual sort) and only for the purpose of procreation>>. ዘር ከመተካት የተለየ ዐላማ ያለው ለደስታና ለፈቃደ ሥጋ ማሳተገሻ የሚደረግን ተራክቦ ነውር ነው በእነሱ፤‹‹seeking pleasure is an impediment to morally virtuous sexuality, and is something that should not be undertaken deliberately or for its own sake. >>
3.3 መፍቅድያነ-ሩካቤ(Metaphysical sexual optimists) የተባሉት ፕላቶ፣ራስልና በመጠኑ ፍሮይድ መሆናቸውን ከላይ የቀረበው አድራሻ ነግሮናል፡፡በዚህ በኩል ያሉት፡- ‹ሩካቤ ሥጋ ሰዎች በገቢረ-ፈቃድና ያለገቢረ-ፈቃድ የሚተሳሰሩበት ተፈጥሮአዊ የደስታ ምንጭ ነው፤ሂደቱ ራስንም ሌላውንም ሐሴት ማላበስ ስላለበት የስሜት ቅብብሎሹ አንዱ ለአንዱ መሰጠትን ፈጥሮ ሰብአዊ ትስስርን የጠበቀና የጠለቀ ያደርጋል›› ይላሉ፡፡እነዚህ እንደሚሉት፡- ሩካቤ በራሱ መጥፎም ደግም አይደለም፤እንደ ገቢሩ ዓላማ ግብረ ገብነት የሌለበት (“vulgar” eros) እና ግብረ ገብነት ያለበት(“heavenly” eros) ሊኖር ይችላል፡፡ግብረ ገብነት የሌለበት ሩካቤ በማንኛውም መንገድ ለፍትወተ-ሥጋ እርካታን(ቃሉ ጸያፍ ሆነ እንጂ ‹‹ማብረጃ›› ቢባል ይሻል ነበር) ማግኘት ብቻ መፈልግና ስለ ተጣማጅ ደንታ ሳይኖር በራስ ወዳድነት ሩካቤን መሻት ነው፡፡(እዚህም ቃሉ ባያውከን ‹‹መቀንዘር›› የሚለው ቃል ነው ገላጩ፤((በቅንፍ-ቅንፍ ተሸሽገን ‹‹የቆመበት የቆመ አያይም!›› የሚለውን የገበና ተረት ብንተርተው ለ”vulgar” eros ልከኛ አማርኛ ተገኘ ማለት ነው))፡፡በሌላ በኩል ግብረ ገብነት ያለበት ሩካቤ (“heavenly” eros) ከማንኛውም ተጣማጅ ጋር ፍተወትን ለማርካት መጣደፍ ሳይሆን ከአንድ ተወዳጅ የሕይወት አጋር ተጎዳኝቶ የአጋሩን ማንነት፣ሰብእና፣ደኅንነትና ስሜት እንደ ራስ ወዶና ፈቅዶ የሚደረግ አእምሮአዊ፣አካላዊና መንፈሳዊ ተራክቦ ነው፡፡ይህች የተቀደሰች የሩካቤ መንገድ ሰው አእምሮና ለብዎ ያለውና ፍትወቱን የሌላውን ስሜት ባገናዘበ መልኩ በተፋቅሮ የሚገልጽ ክቡር ፍጡር መሆኑን ታሳያለች፡፡”Animals have sex and human beings have eros” መባሉም ለዚህ ነው ብለውናል ፈረንጆቻችን፡፡በአንዲት ቁንጽል መረጃ ፈረንጆቹን ከዳሰስን ወዲህ እንመለስ፡፡
3.4 ባገራችን የፈላስፎች በኩር ተደርጎ በስፋት የተነገረለት ዘርዐያዕቆብ (ጠቢቡ/ፈላስፋው) ከተመጠነች ድርሰቱ አንጻር ከታየ ቀላል የማይባል ቦታ ለጋብቻና ለተራክቦ ሰጥቷል (ለነገሩ ስለተራክቦና ስለ ፈጣሪ ባይሞግት ኖሮ በኛ አገር አመለካከት ፈላስፋ የሚለው አይገኝም ነበር!)፡፡ፈላስፋው የሙሴን ተከታዮች በሙሴ መጻሕፍት ውስጥ ከጥበበ-ፈጣሪና እና ከሕገ-ተፈጥሮ ያልተስማማ ስርዋጽ ጨምረዋል ሲል ይከስሳል፡፡ሙሴ ስለርኩሰትና መንጻት በዘሌዋውያን 12 የጻፈውን ዘርዐያዕቆብ የተቀበለው አይመስልም፡፡ይናገራል፤‹‹…የሰው ፍጥረት እንዳይጠፋ ልጆች ለመውለድ በፈጣሪ ፈቃድና በተፈጥሮ ሥርዓት ወንድና ሴት በሥጋዊ ግንኙነት ይገናኙ ዘንድ ታዟል፡፡እግዚአብሔር በሰው የተፈጥሮ ሕግ ውስጥ ያቆመው ይኽ የሥጋ ግንኙነት ርኵስ ሊሆን አይችልም፤ምክንያቱም እግዚአብሔር የእጁን ሥራ አያረክስም›› (ሐተታ ዘርዓያዕቆብ፣ትርጉም በፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡ገ.21)፡፡ቅ/ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ 7 ቁ. 1 ‹‹ይኄይሶ ለብእሲ ኢቀሪበ አንስት–ከሴት አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው›› ሲል የራሱን ድንግላዊ ሕይወት አብነት አድርጎ ጽፏል፡፡ይኽን ሐዋርያዊ ቃል ፈላስፋው ዘርዐያዕቆብ ‹‹…ጋብቻ ፈጣሪ ካቆማቸው ሥርዓቶች ውስጥ እንደሆነ ልቡናችን ይነግረናል፤ያስረዳናልም፡፡ምንኵስና ታዲያ የፈጣሪን ጥበብ ይሽራል፤ምክንያቱም ልጆች መውለድን ይከለክላል፤የሰውንም ፍጥረት ያጠፋል፡፡የክርስቲያን ሕግ ‹ምንኵስና ከጋብቻ ይሻላል› ስትል ውሸት ተናግራለች፡፡ከእግዚአብሔር አይደለችም፤ምክንያቱም የፈጣሪን ሕግ የሚያፈርስ ሥርዓት እንዴት ከእሱ ጥበብ ይሻላል?የሰው ሐሳብ የእግዚአብሄርን ሥራ ሊያሻሽለው ይችላልን?›› ሲል ይሞግታል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.23)፡፡
3.5 ቅ/ያሬድ ጾም ፍትወታተ-ሥጋን ለመግታት ያላትን ኃይል ‹‹ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ፣ወታጸምም ለኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ›› ሲል ያዜመውን ዜማ ዘርዐያዕቆብ ነጠቅ አድርጎ ‹‹የጾም ሕግ የተሠራው የሥጋን ፍትወት ለመግደል ነው የሚሉኝ ካሉ እንዲህ እላቸዋለሁ፤‹በሰው ላይ ያለ የሥጋ ፍትወት ወንድ ወደ ሴት የሚሳብበት ፣ሴትም ወደ ወንድ የምትሳብበት የፈጣሪ ጥበብ ነው፡፡ይኸንን ብታውቀው እሱ ፈጣሪ ባቆመው ሥርዓት፣በሥጋዊ መገናኘት ካልሆነ በቀር በሌላ መንገድ ማብረድ አይገባም፤ምክያቱም ፈጣሪያችን ይኸንን ፍትወት በሰውና በእንስሳት ሥጋ ሁሉ በከንቱ አላስቀመጠውም፡፡ይኸንን ፍትወት በሰው ሥጋ ላይ የተከለው ለዚች ዓለም ሕይወቱ መሠረት እንዲሆንና ፍጥረትን ሁሉ በአቆመለት ሥርዓት መንገድ እንዲያፀናው ነው›› ይላል(ዝኒ ከማሁ፡ገ.24)፡፡በዘርዐያዕቆብ ፍልስፍና ፍትወታችን ከወሰን እንዳያልፍ መፍትሄው ተፈጥሮአዊውን ሩካቤ ሥጋ መገደብ ሳይሆን የሚያስፈልገንን ብቻ እየተመገብን ራሳችንን ወዳላስፈላጊ ሩካቤ ከሚመራ ስካርና ጥጋብ መጠበቅ ነው፡፡እዚህ ላይ የሚገርመው በሐተታው መግቢያ ስለሰው ነጻ ፈቃድ የሚሰብከው ዘርዐያዕቆብ የምንኵስና ሕይወት በምርጫ ሊገባበት የሚችል የሕይወት መንገድ መሆኑን ባለመቀበል መልሶ ነጻ ፈቃድን (free will) መጻረሩ ነው፡፡ክርስትናን ከጋብቻና ምንኵስና አንጻር ያየበት መንገድ ምሬት የተሞላበት መሆኑ እውነታውን ለማየት ቀን ልቡና ሳያሳጣው አልቀረም ብዬ እፈራለሁ፡፡ስለሁሉም ስለሩካቤና ጋብቻ የኦርቶዶክሳዊውን ትውፊት አቋም ባቅማችን እንፈትሽ!ከዚያ በፊት ሚጢጢ ስርዋጽ እናስገባ…
ዳግሚት ስርዋጽ፡- ተመዝግበው ካገኘናቸው ፈንገጥ ያሉ የሩካቤ ገጠመኞች በጥቂቱ!
(ሀ). ለባሕልና ሃይማኖታችን ከበድ ካለው እንጀምር፡፡2 ሴቶች ጎንደር ውስጥ በጾታዊ ግንኙነት (ዛሬ ‹‹ሌዚቢያን›› የሚባለው) ተጎዳኝተው ይኖሩ ነበር፡፡አንዷ እንደ ባል ሌላዋ እንደ ሚስት እየሆነች ኖሩ፡፡በደንብ ኖሩ፡፡ሚስት የተባለችው አረገዘች፤ወለደች፡፡ባልዬዋ ጠፋች፡፡ሚስትዬዋ ‹ወ/ሮ ባል እንደ ልጅ አባትነቷ ተቆራጭ ታድርግልኝ› አለች፡፡ወ/ሮ ባል ጥያቄውን አልተቀበለችም፡፡ጉዳዩ ከንጉሡ ደረሰ፡፡ወ/ሮ ሚስት ከነልጇ በችሎት ቆመች፡፡ሊቃውንት ተጠሩ፡፡ተገረሙ፡፡ሆኖም ወ/ሮ ባልና ወ/ሮ ሚስት ጉድኝታቸውን አልካዱም፡፡በሌላ በኩል ሴትና ሴት በሚያደርጉት ግንኙነት ልጅ ሊወለድ እንደማይችል መጽሐፍም ተፈጥሮም ያስረዳሉ፡፡አንድ ሊቅ ተነሣ፡፡ወ/ሮ ባል ከወ/ሮ ሚስት ጋር ከመተኛቷ በፊት ከወንድ ጋር ግንኙነት አድርጋ እንደሆን ጠየቀ፡፡አመነች፤አድርጌያለሁ አለች፡፡አድራጊዋ (ወንዱ) ተጠራ፡፡መልኩ ለቀለብ ይቆረጥልኝ ክሱ ምክንያት ከሆነው አራስ ሕጻን ጋር ቁጭ!ሆነ፡፡ወ/ሮ ባል የወንዱን ዘር በአፈ ማኅፀኗ ይዛ ለተጎዳኘቻት ወላድ ማቀበሏ ታመነበት፡፡የቀለብ ወጪው ዳኝነት ተጠርቶ በመጣው ወንድ ላይ አረፈ፡፡ይህ ፍርድ የተሰጠው በንጉሥ አጼ ተክለ ሃይማኖት ዘመን (1762-1769) በአቃቤ ሰዓት ከብቴ ስለመሆኑ ፕ/ር ጌታቸው ኃይል ጽፈዋል(አንዳፍታ ላውጋችሁ፣ገ.177-178)፡፡መልአከ ምክር ከፍያለው መራሂ በበኩላቸው ፍርዱ የተሰጠው በአጼ ዮስጦስ ዘመን በነበሩት ቀዳማዊ አራት ዓይና ጎሹ የተባሉ ሊቅ መሆኑን አመልክተዋል(ዝክረ ሊቃውንት፡ገ.26-29)፡፡‹‹ገርመና’ሎ›› አሉ ኤርትራውያን!ምን ይሄ ብቻ!በሄኖክ ምዕራፍ 2 አንድምታ የቃየል ልጆች ለሴት ልጆች ‹‹ያንዱን ጽንስ ባንዱ፣ያንዱን ጽንስ ባንዱ ማሳደር፤አንድም ሰውን ፈረስ፣በቅሎውን ፈረስ፣በቅሎውን ሰው ማድረግ›› ማሳየታቸው ተጽፏል(መጽሐፈ ሄኖክ አንድምታ፡ገ.14)፡፡ጄኔቲክ ምህንድና፣የማኅፀን ኪራይ፣ክሎኒንግ…ወዘተርፈ…(የማላውቃቸውን) የሕክም ቃላት የሚያጠኑ ሰዎች የሄኖክ 2ን አንድምታ ቢመለከቱ ቢያንስ በታሪክ ደረጃ ብሔራዊ የትረካ መነሻ ሳያገኙ አይቀሩም፡፡
(ለ). ወደ ሴቶቹ ታሪክ እንመለስ!የነዚህ ሴቶች ታሪክ በአንዳንድ ነጮች ጆሮ ሳይደርስ አልቀረም፡፡መድረሱ ክፋት የለውም፡፡ነገር ግን ታሪኩን ከኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ጋር አያይዘው ያልሆነ-ያልሆነ ቁንጸል ጥናት ተብዬ ሳያራቡ አልቀሩም፡፡ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ትውልዷ ጎንደር ነው፤ስማዳ፡፡26 ዓመት በትዳር ቆይታ 3 ልጆችን ካፈራች በኋላ መነነች፡፡በሱስንዮስ ዘመን በገነኑት ካቶሊካውያን ተጋድሎ ከፈጸሙ ወገን ነው ቁጥሯ፡፡በምናኔ 36 ዓመት ኖራ በ80 ዓመቷ ኅዳር 18 ቀን አርፋለች፡፡ቅድስናዋ በኢኦተቤክ የታወቀ ነው፡፡በስሟ ጎንደር ውስጥ 2፣ጎጃም 5 አብያተ ክርስቲያናት አሉ–የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000 ዓ.ም የሚለው መጽሐፍ በገጽ 254 እንዳስነበበን፡፡ምናልባት የታሪኳ ቁንፀላ ከካቶሊካውያኑ ጋር በተያያዘ የተፈጸመባት ሥም ማጥፋት ሊሆን ይችላል–ሴራ(conspiracy) ፈጣሪ ካላሰኘን!አጼ ፋሲል የሱስንዮስን አዋጅ ለውጦ በካቶሊካዊት ሃይማኖት ምትክ የቀደመችው ተዋሕዶ ትመለስ የሚል አዋጅ በማሰማቱ ‹‹ሴቶችን ተገናኝቶ ሲያበቃ ባሕር ይጥላል›› የሚል ሐሜት የካቶሊክ መነኰሳት አስወሩበት፤አስጻፉበት እንደሚባለው ነው፡፡ባገራችን የካቶሊክ፣ቅብዐት፣ፀጋና ተዋሕዶ የምዕተ-ዓመታት ክርክሮች አንዱ ላንዱ ጸያፍ ሥምና ብሂል መስጠት፣መፈራረጅ አዲስ አይደለም፡፡የወለተ ጴጥሮስን የተዋሕዶ ብሂል ተቆርቋሪነት ለማጠልሸት ከተቃራኒ ብሂል የሆኑ ደባትር ጠልስመውና ከላይ የተገለጹትን ሴቶች ታሪክ ለወለተ ጴጥሮስ አስመስለው በጸያፍ አግብተው ለፈረንጆቹ አቀብለውም ሊሆን ይችላል፡፡ሆነም ቀረ ነጮቹ ደባትር ስተዋል!ይቦጭቃቸው!
(ሐ). መላ ምቱን ባለበት አቁመን ወደ ተመዘገቡልን የሩካቤ ታሪኮች እንለመስ፡፡በዚች ቅጽበት እያነበብኩት የሚገኘው የሞገደኛው ጋሞ፣የጨንቻው፣የኢጭአቱ ጓድ አሰፋ ጫቦ ‹‹የትዝታ ፈለግ›› መጽሐፍ አቶ አሰፋ ጫቦን ፊደል አስቆጥረው ለዲቁና ያበቁት መሪጌታ ብቅአለ ክበበው እና ወንድማቸው መሪጌታ ደመቀ ክበበው ‹‹ሂያጆች›› እንደነበሩ ያትታል(የትዝታ ፈለግ፡ገ.41)፡፡የሚገርመው ሁለቱም ዓይነ ስውር መሆናቸው፡፡መንገዱ ለዓይነ ስውርም አይጠፋ ጃል!ዓይነ ስውር ቢባል 4 ኪሎ የነበሩ ዓይነ ስውር ትዝ አሉኝ፡፡ተራክቦ ሲፈጽሙ መንገድ ሳቱ፡፡ተጓዳኛቸው ‹‹እረ የኔታ!እግዜር በፈጠረው›› ብላለች፡፡‹‹ውይ!ይቅርታ!ግን ይኽንንስ አንቺ ነሽ የፈጠርሺው?›› አሉ ተብሎ በሹክሹክታ ተሳስቀናል፡፡ከየኔታዎች ውስጥ አራት ዓይና ጎሹ፣አለቃ ገብረ ሃና እና የአለቃ ለማ ኃይሉ የዜማ መምህር (የአለቃ ለማን መጽሐፈ ታሪክ ገጽ 61 ተመልከት) የተመዘገበ ሂያጅነት ያላቸው ታላላቅ መምህራን ናቸው፡፡ሲራክ መምህራንን ሴትና መጠጥ እንደሚፈትናቸው መጻፉን አንብቤ ነበር፤ምዕራፍና ቁጥሩ ተዘነጋኝ!የመካከለኛው ዘመን ሰሎሞናዊ ገናና ነገሥታትና የገዳማውያኑ ትልቅ ያለመግባባት ምንጭ የነገሥታቱ መፍቀሬ-አንስት መሆን ነበር፡፡የሰሎሞን ዘር መሆናቸውን በምን ያሳዩ?!ዕቁባት መደርደርንና እንደ አቤሴሎም የአባቶቻቸውን ቅምጦች ሳይቀር መጎብኘት ይወዱ ነበር!ይህን ስርዋጽ በአለቃ ተክለኢየሱስ ዋቅጀራ እንዝጋው፡፡ሰሞኑን ድጋሚ በታተመ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ›› መጽሐፉ ገጽ 219 አለቃ ተክሌ አንድ አባ ወልደ ሥላሴ የተባሉ ቄስ የንስሐ ልጃቸውን ለምደው የተፈጠረውን አጋጣሚ ከነሥነቃሉ ጽፎልናል፡፡ቄሱ የንስሐ ልጃቸውን ለምደዋል፡፡የመጋኛ መድኃኒት አድርግላታላሁ እያሉ ባሏን አቁመው ሌላ ነገር ያደርጋሉ፡፡የዋሑ ባል ዘግይቶ ነቃ፡፡ከደጃች ተድላ ከሰሳቸው፡፡ደጃች ተድላ በባልየው ንዝህላልነት ተበሳጨ፡፡‹‹እንስሳ!አሰርረህ ትከስሳለህን?!›› ብሎ አባረረው፡፡የወገን እረኛ ሰማ፡፡እንዲህ አላገጠ፤
‹‹ጫንቃ ሰበር ይዞ፤ስረሩ ቢላቸው፣
አባ ወልደ ሥላሴ፤ምን ፍርድ አለባቸው፡፡
አባ ወልድ ሥላሴ፤ምናኔ ምናኔ፣
ቆብሁ ተግድግዳ፤አካላትሁ ተኔ፡፡›› እያለ ዘፈነባቸው፡፡አሁን ዘፈኑን ትተን ወደ ዓቢዩ ርእስ መቋጫ እንገሥግስ…
ይቀጥላል