Friday 2 October 2020

 " የኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነት..."

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
ሰላም ተወዳጆች! እንደምን አላችሁ? በባለፈው ፅሁፋችን " ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነት" ዚሩያ የሚነሱ ሙግቶችን መመለክከታችን ይታወሳል። ለዛሬም ከዛው በቀጠለ ርዕስ ላይ የሚነሳን ሌላ ሙግት እንመለከታለን። የኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅነት በመቃዎም ወገባቸዎን ገትረው ከሚሞግቹ የሙስሊም መምህራን መካከል ሰለምቴውን ኡስታዝ ወሒድ ኡመር አንዱ ነው ለዛሬም በዚህ ርዕስ ዙሪያ እርሱ ያዘጋጀዎን ጦማር ጌታ በፈቀደ መጠን የምንፈትሽ ይሆናል። (ለፅሁፉ ርዝመት ሲባል ኡስታዙ ያነሳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች እያነሳን የምናይ ይሆናል። ምላሹን ከማንበባችሁ በፊት ግን ለማነፃፀር እንዲመቻችሁ የኡስታዙን ፅሁፍ እንዲታነቡ እንመክራለን።https://t.me/Wahidcom/2055)
⭕ ኡስታዙ ጦማሩን በሌሎች ፅሁፎቹ እንደሚያደርገው በዚህም ፅሁፉ ላይ ከቁርአን በመጥቀስ ይጀምራል ፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا
📌 #ምላሻችን፦ ኡስታዙ ከመፅሀፉ ለራሱ ሲጠቅስ ለራሱ የሚመቸውንና ከሃሳቡ ጋር የሚስማማለትን በመገንተል የሚያፍርባቸውን ደግሞ ወደ ጓዳ በመክተት ነው። የቁርአኑን እሳቤ ሙሉ ምስል ለማግኘች ሌላ ተጨማሪ ጥቅስን እንጥቀስ፦
ጥቅሱ የላይኞቹን ጥቅሶች እሳቤ በማስፋት ሙሉ ምስሉ እንዲመጣል የሚረዳ ቢሆንም ምስሉን ለማጥራ ያክል ከተፍሲሮቻቸው እንጨምር፦
(How can He have children when He has no wife) 👉#for_the_child_is_the_offspring_of_two_compatible_spouses. Allah does not have an equal, none of His creatures are similar to Him, for He alone created the entire creation. Allah said;
وَقَالُواْ اتَّخَذَ الرَّحْمَـنُ وَلَداً - لَقَدْ جِئْتُمْ شَيْئاً إِدّاً
ከተፍሲሩ እንምንረዳው ልጅን ለማግስገኘት ሁለት ተቃራኒ ጾታወች ያስፈልጋሉ። ጥቅሱን በአመክንዮ ስንደረድረው ለአላህ ልጅ አለመውለድ ትልቅ እንቅፋትም የሆነበት ሚስት አለማግኘቱ እንጂ አላህ ልጅን የማይወልድ ሆኖ አይደለም ሚስትን ቢያገኝ አላህ ልጅን ይወልዳል። ስለዚህ የቁርአኖቹ ጥቅሶች እንደማነፃፀሪያ ሊቀርቡ የማይችሉ ናቸው ማለት ነው።
የቁርአኑ አምላክ ልጅ ለመውለድ ሚስት የሚያስፈልገው ቢሆንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ግን ይህ አይስማማውም። ልጅን ለመውለድ ሚስት እና ጊዜን የሚጠብቅ አይደለም። ከእኛ አዕምሮ በላይ በሆነ ውልደቱ ኢየሱስን ቅድም አለም ያለ እናት ወልዶታል።
⭕ ኡስታዙ፦
"እግዚአብሔር አባት መባሉ 'አስገኚ' ወይም 'ፈጣሪ' በሚል ፍካሬአዊ እሳቤ 'ideological sense' መጥቷል" በማለት ጥቅሶችን ይደረድራል ከዛም በጥቅሶቹ 'አባት' የሚለው 'አስገኚ' ወይንም ' ፈጣሪ' በሚል ፍካሬያዊ ትርጉም ስለሚተረጎም ለኢየሱስም አባት ሲባል በዛው እሳቤ የሚሄድ ነው ይለናል።
የኡስታዙ አመክንዮን ለተረዳው ሙግቱ ከአለማዊ የፍልስፍና ትምህርት እንኳን የማያልፍ ነው። በነዚያ ጥቅስ ፈጣሪ የሚል ትርጉም ስላለው ኢየሱስም በዚሁ መፈታት አለበት ብሎ መሞገት weak analogy የሚባለውን የfallacy አይነት መፈፀም ነው።
የአመክንዮውን ገለባነት በመፅሀፍ ቅዱስ ለማስደገፍ ያህል " አባት" የሚለው አስገኚነትን በሚያሳይ መልኩ እንደተገለፀ ሁሉ የሁሉ ጠባቂ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ መገለፁን እንጥቀስ፦
“አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።”
— ኢሳይያስ 63፥16
በዚህም መሰረት ኡስታዙ ለእራሱ የሚመቸውን ጥቅስ ብቻ ጠቅሶ መፅሀፍን ለማንሸዋረር የተጠቀመበት ሂደት ስህተት መሆኑን እንረዳለን ማለት ነው።
⭕ ወሒድ፦ አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል?
#ምላሻችን፦ ወሒድ እዚህ ላይ እኛ የማንለውን ወይንም ይዘን የማንሞግትበትን ነጥብ ይዞ ለመሞገት እየሞከረ ነው። እንደርሱ አባባል ከሆነ አኛ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለን የምናምነው ከድንግል ማርያም ከተወለደ በኋላ ነው። ግን ይኼ ፈፅሞ ስህተት ነው። በባለፈው ክፍላችን እንደተመለከትነው የኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነት በቅድመ አለም በነበረው ልደቱ ጀምሮ እንጂ ከድህረ አለም ልደቱ ከድንግል በተወለደው አይደለም (የቀደመውን ክፍል ማየት ለወደደ https://t.me/ekbetemnet/215)። በድህረ አለም ልደቱ እኛ ልጅ በተባልነው አይነት በጸጋ ልጅ ተብሏል ይህ ግን ቀድሞ የነበረውን ልደቱን አይቀይረውም። ኡስታዙ ይህንን እሳቤውን በፅሁፉ በተደጋጋሚ አንፀባርቆታል ይህን የተንሸዋረረ ምልከታውን የፈፀመው እያወቀ ከሆነ የሚፅፈው ለፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን ለዘላለማዊ ህይወት ነውና ከዚህ ነገር ይታቀብ። ያለማወቅ ከሆነ ደግሞ " ከመጠምጠም መማር ይቅደም" በሚለው ብሂል መማሩን ያስቀድም ወንድማዊ ምክራችን ነው።
⭕
⭕ ኡስታዙ፦ አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል
#ምላሻችን፦ ይህ መዝ 2:7 እና ዕብ 1:5 የኢየሱስን ሁለት ልደታት ልናሳይበት የምንችልበት ጥቅስ ነው። ወልድ ቅድመ አለም ያለ እናት ከአብ ተወልዷልና " አንተ ልጄ ነህ" ሲለው ድህረ አለም ከድንግል የተወለደውን ሁለተኛውን ልደት ለማሳየት ደግሞ " እኔ ዛሬ ወለድሁህ" በማለት ይገልጸዋል።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ዕብራውያን መልእክትን በተረጎመበት ድርሷኑ ይኽንን ብሏል፦
Ver. 5. "For to which of the Angels said He at any time, Thou art My
Son, this day have I begotten Thee. And again, I will be to Him a
Father, and He shall be to Me a Son"? For these things indeed are
spoken with reference also to the flesh: "I will be to Him a Father,
and He shall be to Me a Son"--while this, "Thou art My Son, this day
have I begotten Thee," expresses nothing else than "from [the time]
that God is." For as He is said to be, from the time present (for this befits Him more than any other), so also the [word] "Today" seems
to me to be spoken here with reference to the flesh. For when He
hath taken hold of it, thenceforth he speaks out all boldly. For indeed
the flesh partakes of the high things, just as the Godhead of the
lowly.
ከዚህም በተጨማሪ ይህ የመዝሙር 2:7 ትንቢት የኢየሱስን ከሙታን መነሳት ጋር በተያያዘ በሐዋርያት ተገልጿል፦
“ኢየሱስንም ከሙታን በማስነሣቱ ለእነርሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል፤ ይኸውም በሁለተኛው መዝሙር እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።’”
— ሐዋርያት 13፥33
⭕ ኡስታዙ ከዚህ ቀጥሎ "ተራሮች ተወለዱ የሚለው መፈጠራቸውን የሚያመለክት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስም ወለድሁህ መባሉ መፈጠሩን የሚያመለክት ነው" በማለት ከላይ የተመለከትነውን አይነት አመክንዮአዊ ከረጅም ሀተታ ጋር ሲጠቀም እናገኘዋለን።
አሁንም ስሁት የሆነ አክንዮን እሰራ ስለሆነ እሱ የዘከዘከውን ያክል እኛም አንዘከዝክም ግን ያን ሁሉ ሀተታውን በአጭሩ ለመቋጨት ያህል ተራሮች ተወለዱ መባላቸው መፈጠራቸውን የሚያመለክት እንደሆነ እሙን ነው ማንም ተወለዱ ብሎ አይከራከርም ግን ለተራሮች የተነገረው ለኢየሱስ ይሆናል ወይ? የሚለው ነው ወሳኝ ጥያቄ ። መልሱም አይደለም የሚል ነው ምክንያቱም ተራሮች ሊወለዱ አይችሉም ኢየሱስ ግን ሊወለድ የሚችል ነው። የማይነፃፀር እያነፃፀሩ መሞገት በእውነት ቂልነት ነው።
ከላይኛው ሙግቱ በተጨማሪ፦
“የወለደህን አምላክ ተውህ፥ ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ።”
— ዘዳግም 32፥18
ይህንን ይጠቅስና እስራኤላውያን "የወለደህ" መባሉ መፈጠራቸውን ለማመልከት ከሆነ የኢየሱስንም በዚሁ ተረዱት በማለት በማያዋጣ ሙግት ወገቡን ገትሮ ይሟገታል።
አሁንም የወለደህ መባሉ "የፈጠረኽ" የሚል ፉካሬያዊ ትርጉም አለው የሚለውን ተቀብለን ብንመለከተው ለራሱ እዚህ ላይ የፈጠረኽ በሚል ስለመጣ ብቻ ለኢየሱስም የፈጠረኽ በሚል መተርጎም አለበት ማለት አይደለም።
⭕ ወሒዴ፦ መዝሙር 110፥3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማህጸን ወለድሁህ
የተወለደው በኃይሉ ቀን ነው፤ የቅዱሳን ብርሃን በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህ የግሪክ ሰፕቱጀንት እንጂ የማሶሬቲኩ ላይ ቃላቱ የለም። ከማርያም ማህጸን “ወለድሁህ” ማለት “ፈጠርኩ” ማለት ካልሆነ ችግር ይፈጠራል።
✟# መልሳችን፦ ኡስታዙ መፅሀፍን በገዛ ስልጣኑ እያጣመመ መተርጎሙን ተያይዞታል። አሁን በዚህ ጥቅስ "በቅዱሳን ብርሃን" የሚለውን መንፈስ ቅዱስ ብሎ እንዲተረጉም ምን አስቻለው? በራሱ የለመደውን በመፅሀፍም ለመድገም እየቃጣው ነው።
ከዚህ ባለፈ ጥቅሱን አባቶች ሲተነትኑት ከአጥቢያ ኮኩብ የሚለው እንደሚያሳየን ቀንና ሌሊትን የሚያለዩ ብርሃናት ከመፈጠራቸው በፊት ኢየሱስ ከአብ የተወለደውን ቅድመ አለም ልደቱም የሚያሳይ ነው። ኡስታዙ እራሱ ችግር ፈጣሪ ሆኖ " ከማርያም ማህፀን 'ወለድሁህ' ማለት 'ፈጠርኹህ' ካሌሆነ ችግር ይፈጥራል ይለናል። ሲጂመርስ " ከማርያም ማህፀን" የሚለውን ከየት አመጣው? በእውነቱ ጥቅሱ ይላልን? በፍፁም አይልም። ጥቅሱ የሚለው ከማህፀን ወለድሁህ ነው። ወላጁም አብ ነው። አንዳንድ የዋሆች አምላክ ማህፀን አለው እንዴ? ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ መልሱ ግን በሰዎኛ አገላለጽ እየገለጸው እንጂ አምላክ ዘር መቋጠሪያ ኑሮት አይደለም። በዮሀንስ 1:18 ወንጌላዊው ዮሀንስ "በአባቱ እቅፍ" ይላል እዚህ ላይ አምላክ ልጅ ማቀፊያ ጉያው ኑሮት አይደለም ግን በሰዎኛ አገላለጽ እየገለፀው ነው ያንንም በዚህ መልኩ መረዳት ይገባል።
⭕ ወሒድ ፦ ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*
ወሒድ አሁንም ፈጠራውን ቀጥላል። አሁን ደግሞ መፅሀፍን በራሱ ፍች አስቀምጦ ጨርሶ ወደ ሃይማኖተ አበው ተሸጋግሯል። ሃይማኖተ አበው ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ አባቶች ያስተማሩት ትምህርት ስብስብ ሆኖ ሳለ ከዛ የእርሱን ሃሳብ የሚደግፍለትን ለመፈለግ መግባቱ አስገራሚ ነው።
ወደጠቀሰው ስንመለስ ቅዱስ ባስልዮስ በምዕራፍ 32 ከቁጥር 18 ላይ እየተናገረ ያለው ስለ ምሳሌ 8:21-24 ያለውን አርዮስ ኢየሱስ ፍጡር በማለት የካደበትን ጥቅስ እንጂ መዝሙር 110:3 ላይ ያለውን አይደለም። ይህ እንዳለ ሆን ቅዱስ ባስልዮስ ኢየሱስ ፍጡር አይደለም እያሉ መሆኑን እንኳን ወሒድ ልብ አላለም። " ፈጠረኝ ማለትም ሰው ስለ መለሆኑ ይተረጎማል" የሚለው ኢየሱስ አምላክ ሲሆን ሰው ነውና እንደሰውነቱ " ፈጠረኝ" የሚለው ይስማማዋል እያሉን ነው። ወሒድ ሃይማኖተ አበው ጠቅሶ ክርስትናን ለመሞገት ባይሞክር እና ባይደክም ይሻለዋል።
⭕ ወሒድ፦ አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ።
ወሒድ አንድ ያልተረዳው ነገር አለ። ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጡ ናቸው ግን አወጣጣቸው አንድ አይደለም። ወልድ ከአብ በውልደት ሲወጣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በስርጸተ ይወጣል። ስለዚህ ወልድ ከአብ ወጣ ስንል መንፈስ ቅዱስ ከአብ ወጣ ከምንለው የተለየ ነው። ወሒድ ይህንን ቢረዳ ኑሮ እንዲህ ባልተቸገረ ነበር።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!
ይቆየን!
©✞ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
👍 Like our page & follow us
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
Image may contain: 1 person, text
የመማፀኛዬ ከተማ ኢየሱስ ነው and 18 others
7 Comments
13 Shares
Like
Comment
Share

No comments:

Post a Comment