Friday 2 October 2020

 በእንተ ሰማንያ አሃዱ (ክፍል-፮)

[በዝምታው ዘመን(400 ilent Year) የተጻፉ ስለሆኑ አንቀበላቸውም የሚለው የፕሮቴስታንቶች ሙግት]
√ ባለፉት አምስት ክፍሎች ፕሮቴስታንቶች የማይቀበሏቸውን የዲዩትሮካኖኒካል (Deutrocanonical) መጻሕፍት እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቀኖና የተቀነኑትን የሐዲስ ኪዳን የሥርአት መጻሕፍት(Books of Church Order) ምንጮች ተመልክተናል። ከዚህ በኃላ ባሉት ተከታታይ ጽሁፎች ደግሞ መጻሕፍቱን ላለመቀበል በሚያነሷቸው ትችቶችና ጥያቄዎች ላይ ምላሽ እንሰጣለን።
√ የፕሮቴስታንቱ ዓለም የዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትን ላለመቀበል ከሚያቀርቧቸው መክንያቶች አንዱ "ትንቢተ ሚልኪያስ ከተጻፈ በኃላ እግዚአብሔር ለ 400 አመታት በዝምታ ውስጥ ነበር" የሚል ነው። ይህንን ይይዙና የዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት የተጻፉት በእነዚህ 400 የዝምታ አመታት ስለሆነ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት አልተጻፉም፣ ስለዚህ አንቀበላቸውም ብለው ይደመድማሉ። አንዳንዶች ደግሞ እንደ ሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ባንቀበላቸውም ለታሪክ ማጣቀሻነት ብቻ ልንጠቀምባቸው እንችላለን የሚል ሀሳብ ይሰነዝራሉ። ይህንን ዘመን የፕሮቴስታንቱ አለም Inter testamental period, Between the Testament, 400 silent year በማለት ይጠሩታል። ይህንን የፕሮቴስታንቶች ሙግት ስህተትነት ለማየት እንሞክር።
√ በመጀመሪያ ማወቅ ያለብን እግዚአብሔር ለ 400 ዓመት በዝምታ አሳልፏል የሚለው ሀሳብ አንድም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለውም። በመጽሐፍ ቅዱስ ከነቢዩ ሚልኪያስ በኃላ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ አላጸፈም፣ እግዚአብሔር ከእስራኤል ተለይቶ ዝም ብሏል የሚለው የፕሮቴስታንቶች ሙግት መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያላደረገ ነው። ይህ ሀሳብ የሚገኘው የሰባ ሊቃናትን (Septuagint) መጽሐፍ ቅዱን አንቀበልም ያሉት ፈሪሳውያን በጻፉት "The Babylonian Talmud" በተባለው የትውፊት መጽሐፋቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (Sola Scriptura) የሚል አስተሳሰብ ያላቸው ፕሮቴስታንቶች ይህንን ሀሳብ ከየት አምጥተው ነው የሚናገሩት? መልሱን ለእነሱ ትቼዋለው።
√ ፕሮቴስታንቶች ይህንን ሀሳብ እንደ መክንያት ቢያቀርቡትም እነርሱ ከሚሉት ከዝመታው ዘመን በፊት የተጻፉትን እንደ ተረፈ ኤርሚያስ ያሉትን መጻሕፍት ለምን አይቀበሉም? በእርግጥም ላለመቀበል የፈጠሩት ሰበብ እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል።
√ መጽሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር ለ 400 አመታት ዝም ብሏል፣ ነቢያትን አላስነሳም፣ መንፈስ ቅዱስ ከእስራኤል ተለይቶ ነበር የሚለውን ሀሳብ አይደግፈውም። ይልቁንም በተቃራኒው ይቃወመዋል። ከዚህ በታች ያሉት ሶስት ጥቅሶች ይህንን ያረጋግጣሉ።
1. " ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ፤"
ማቴ11:13
√ በዚህ ጥቅስ ላይ በግልጽ እንደ ተቀመጠው እግዚአብሔር ትንቢት ያናገረው እስከ ነቢዩ ሚልኪያስ ሳይሆን እስከ ዮሐንስ ድረስ ነው። እግዚአብሔር እስከ ዮሐንስ ድረስ የመሲሁን መምጣት በትንቢት ሲያናግር ነበር።
2. " እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፥ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት ይጠባበቅ ነበር፤ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፥ መንፈስ ቅዱስም በእርሱም ላይ ነበረ።" ሉቃ2:25
√ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ለ 400 አመታት እግዚአብሔር አልተናገረም፣ መንፈስ ቅዱስ ርቋል የሚለውን ሀሳብ የሚያፈርስ ነው። " ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤"
(የሉቃስ ወንጌል 2:29) ብሎ መናገሩ አስቀድሞ እግዚአብሔር የገለጠለት ምሥጢር እንደነበረ ያሳያል፣ በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ነበረ የሚለው ቃል መንፈስ ቅዱስ ተለይቷቸዋል የሚለውን ሀሳብ ከንቱ የሚያደርግ ነው።
3. " ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤" ሉቃ2:36
√ እግዚአብሔር ለ 400 አመታት በዝምታ ውስጥ ነበር፣ ነቢያትን አላስነሳም ቢሉም ቅዱስ ሉቃስ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱጨበፊቴ ነቢይት ሐና የመሲሁን መምጣት እንደ ሰበከች ይነግረናል።
=>>>በአጠቃላይ 400 የዝምታ አመታት የሚለው የስህተት ሀሳብ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው፣ የዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትን ላለመቀበል የተፈጠረ ሀሳብ ነው።
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር!
©ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
Image may contain: text
11
26 Comments
14 Shares
Like
Comment
Share

No comments:

Post a Comment