Thursday 15 October 2020

በእርሱ ያመኑትን ሕሙማንን ታሞ ያድን ዘንድ እጆቹን ለሕማም ዘረጋ ( ምንጭ ቅዳሴ ሐዋርያት ) ሰፍሃ እደዊሁ ለሕማም ሐሚሞ ከመ ሕሙማነ ያድህን እለ ተወከሉ በላዕሌሁ በእርሱ ያመኑትን ሕሙማንን ታሞ ያድን ዘንድ እጆቹን ለሕማም ዘረጋ ( ምንጭ ቅዳሴ ሐዋርያት ) የመጀመርያይቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዛሬ ላይ ተሃድሶ የሚያስፈልጋት ቢሆንም ቀድሞ ወይንም ከዚህ በፊት የነበራት የደኅንነት እምነት አቋም ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ያመኑትን ሕሙማንን ያድን ዘንድ እጆቹን ለሕማም ዘርግቶና ሕማማችንን ፣ መርገማችንንም ጭምር ወስዶልን ሳለ ፣ የዛሬዋ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለበደልዋ ካሳ የሚሆንን ቅጣት እንዳልተቀጣላት አድርጋ በመቁጠር ፣ የኪዳኑን ደም አክፋፍታና ረግጣ ወደ ፍጡራን አምልኮና አዳኝነት ኮበለለች :: ለደኅንነታችንም የተዘረጋው የኢየሱስ እጆች ሳይሆኑ የመላዕክት ክንፎች ናቸው አለችን :: ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ? ብለን ስንጠይቃት ደግሞም ታሪኳን አያይዛና ቀጥላ መላዕክቱ ክንፎቻቸውን ወደ ሲኦል በመዘርጋት ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ነፍሳት አዳኑ ስትልም መጽሐፍቅዱስ ላይ ያልተጻፈ ታሪክና የአሮጊቶችን ተረት መተረት ጀመረች ፤ እንደገናም በመላዕክቱ ሳታበቃ የመንግሥተ ሰማያት የይለፍ ፈቃድ ለነተክለ ሃይማኖት እንደ ተሰጠ አድርጋ በመቁጠር ፣ የኃጥኡም ሆነ የጻድቁ ነፍስ ተክለሃይማኖት ጋር ሳይደርስ ወደ ሲኦል አይሄድም አለችን :: የመጀመርያዋ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ግን የሐዋርያት ቅዳሴ በተሰኘው መጽሐፍዋ ላይ በእርሱ ያመኑትን ሕሙማንን ታሞ ያድን ዘንድ እጆቹን ለሕማም ዘረጋ ብላ ጽፋና ከትባ ስለያዘች ለደኅንነትዋ ከተዘረጋላት ከጌታ እጅ ውጪ ሌላ ነገር ማለትም ሆነ መቀላወጥ አላማራትም ፣ ደስም አላሰኛትም :: በእርሱ ያመነውን ሕሙማንን ያድን ዘንድ እጆቹን ለሕማሜ የዘረጋልኝ የጌታዬ እጅ ለእኔ በቂዬ ነው ስለዚህ የነፍሴ አዳኝ ኢየሱስና ኢየሱስ ብቻ ነው ስትል የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 በእርሱ ላይ አርፋና ተደላድላ እኛንም አደላደለችን :: ለበለጠ መረጃ እንደገና የተለቀቀውን ቪዲዮ በማስተዋል ተከታተሉ ለሌሎች ወገኖችም ሼር አድርጉ ስል ለማበረታታት እወዳለሁ ጌታ ይባርካችሁ ወንድማችሁ ሐዋርያዊው አገልጋይ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment