<<ለቸርነቷ ልማድ ወሰን የለውም>>
መጽሐፍ ቅዱስ በቸርነቱ ወደር የሌለው እግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል÷ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ››፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ›› ‹‹በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት÷ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች!›› በማለት ያስነብባል (መዝሙር 23፡6፤ 25፡10፤ 31፡19)፡፡
ቸር የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹የሚሰጥ፣ ለጋስ፣ አባ መስጠት፣ እጀ ሰፊ›› የመኒል በመሆኑ ከሰዉ ልጆች መካከል በልዩ ልዩ ቸርነት ውስጥ ሊገለጡ የሚችሉ ሰዎች ሞለተዋል፡፡ ነገር ግን ደካማ የሰው ልጅ በመሆናቸው ቸርነታቸው ፍጹም አይደለም፡፡ በአንዱ ቸር ቢሆኑ በሌላው ንፉግ (ስስታም) ሆነው ይታያሉና፡፡ ለቸርነቱ ወሰን የሌለው እግዚእሔር አምላክ ብቻ ነው፡፡
የገድለ አርሴማ ጸሐፊ ግን ይህን የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለፍጡር ለመስጠት እጁ የታዘዘለት ሰው ነው፡፡ ሐሳንም ‹‹ቅዱሳን ሰማዐት በምድር እንደሚወርድ እንደ ዝናብ ነጠብጣብ ስለሆነው ስለ ሥቃይዋና ግፍዋ ብዛት ይደሰቱባታል፡፡ ለግፍዋ መጠን ቊጥር የለውም፡፡ ለቸርነቷ ልማድም ወሰን የለውም፡፡ የእግዚአብሔር ነገሩንማ ጥበቡ ዕፁብ ድንቅ ነውና›› በማለት አስፍሮታል፡፡
ጸሐፊው በዚህ ስፍራ ወደ ምድር በሚወርድ የዝናብ ነጠብጣብ የመሰለው ስቃይዋና የደረሰባት ግፍ ብሎ ያስቀመጠው ምን እንሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ መጽሐፉን ባነበብኩበት ወቅት በዚህ መጠን የሚገለጸ ሥቃይና ግፍ ቀርቶ ሰማዕትነትን ከመቀበሏ ውጪ የደረሰባት ነገር አላየሁም፡፡ ከዚህ ይልቅ ግን ምንም እንኳ ሥቃይና ግፍ ደረሰባት ቢባልም ሥቃይና ግፍ ስታደርስ የምትታየው እርሷ ናት፡፡ ለዚህም በገድሉ ላይ፤
ቡርክት አርሴማም መለሰችለት በጌታዬ ላይ የስድብ ቃል ከምሰማ፤ ልገድልህ በወደድሁ ነበር፡፡ ወይም ሞት በተሻለኝ ነበር፡፡
ድርጣድስም ልጇን ስታበረታታ በሰማ ጊዜ የእናትዋን የዐጋታንና የቀወድስት አርሴማን ጥርሶች ይሰበሩ ዘንድ አዘ፡፡ እግዚእሔር ግን በንጉሥ ድርጣድስ ላይ ኀይልንና ብርታትን ሰጣት፡፡ እርሱ በፀብ ኀይለኛና የታወቀ፣ ፈጽሞም የበረታ ሲሆን፣ ወደ ኋላው ጣለችውና በምድርም ጎተተችው፡፡ ያን ጊዜም ንጉሥ ድርጣድስ በወታደሮቹ ት በብፅዕት ቅድስት አርሴማ ስለተሸነፈ አፈረ፡፡
ቡርክት አርሴማም መለሰለችለት፡፡ እንዲህም አለች፤ ፊቷን በጥፊ ወደ መታት ወደዚህ ንጀለኛ ላይ፣ በእጇ ጣት በትእምርተ መስቀል እያማተበች፣ ፊቷን በጥፊ የመታት፣ ያ ወንጀለኛ ሕያው እንደሆነ ወደ ሲኦል ይወርድ ዘንድ፣ ምድርም አፏን ትከፍትና እንደ ዳታንና አንደ አቤሮን ትውጠው ዘንድ ወደ ፈጣሪዋ ለመነች፡፡ እንደ ብፅዕት አርሴማ ቃልም ሆነ፡፡ በሰጠመበትም ላይ ዘጋችው፡፡ ቅድስት አርሴማ ያደረገችውን ይህን ተኣምር ያዩ ከወታደሮች ብዙዎቹ ሸሹ፡፡ ንጉሡም ይሸሽ ዘንድ ከዙፋኑ ተነሣ፡፡ ያን ጊዜም ቡርክት አርሴማ ፈገግ አለች፡፡ ቅዱሳን ሰማዕትም ስለ እርስዋ ተደሰቱ፡፡ መላእክት በላይዋ ሲከቡአት አይተዋልና፡፡
ተብሎ ተጻፈውን መመልከት ይቻላል፡፡ በእነዚህ ምንባባት ውስጥ ‹‹ልገድልህ በወደድሁ›› በማለት እሷ እየተሰቃየች ሳይሆን ዛቻ እያቀረበች መሆኑን፣ ንጉሡን መሬት ላይ ጥላ እንጎተተችው እና የንጉሡን ወታደር ‹‹ሕያው እንደሆነ ወደ ሲኦል ይወርድ ዘንድ›› ቃል በማውጣት ‹‹ሕያው እንደ ሆነ›› ምድር እንድትውጠው በማድረግ ደስ እንደተሰኘች (‹‹ያን ጊዜም ቡርክት አርሴማ ፈገግ አለች›› ተብሎ ተጽፋልና) የተመለከተ ልባም አንባቢ እንደ ዝናብ ነጠብጣብ የሆነው መከራዋ የቱ ነው ደግሞ እንዲህ ብዙ የሆነ ሥቃይና ግፍ ሲያደርጉባት ወሰን የለውም የተባለው ቸርነቷ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል
@gedlatnadersanat