ሴትነት በመጽሐፈ ሲራክ
‹‹ከልብስ ብል ይገኛል፣ ክፋትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል፡፡ ኀፍረትን እና ቅንአትን ከምታመጣ ሴት ደግነትን፤ የወንድ ክፋት ይሻላል›› (ሲራክ 42÷13-14 የ2000 ዕትም)፡፡
‹‹ከልብስ ብል ይገኛል ኀጢአትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል፡፡ ከሴት ቸርነት የወንድ ንፍገት ይሻላል፡፡ ውሸማዋንና ባሏን የምታቃና ሴት እፍረት ናት›› (ሲራክ 42÷13-14 የ1980 ዕትም)
‹‹ክፉ›› የሚለው ቃል ትርጕም ‹‹መጥፎ፣ ጨካኝ፡፡ ስስታም፣ ንፋግ፣ ኃይለኛ›› ማለት ነው፡፡ በዚህ ትርጕም መሠረት ክፋትን የወንድና የሴት በሚል ለመክፈል የሚያስችል ምንም ምክንያት የሌለ በመሆኑ የመጽሐፈ ሲራክ አዘጋጅ ከሴት ቸርነት ይልቅ የወንድ ክፋት ይሻላል ያለው በምን ይሆን?
ክፋት ከጾታ ጾታ የሚለያይ (የሴቲቱ ክፋት ክፉ የወንዱ ክፋት የተሻለ የሚባል) አይደለም፡፡ ጥያቄው መሆን ያለበት የታሰበው ሐሳብም ሆነ ድርጊቱ በማን ታሰበ ወይስ ተደረገ? የሚል ሳይሆን አሳቡ ክፉ ነው መልካም? የሚል ነው፡፡ ሴትም ትሁን ወንድ ያደረጉት ነገር ክፉ ከሆነ ክፉ ነውና፡፡
የመጽሐፈ ሲራክ አዘጋጅ ለሴቶች ያለው አመለካከት ምን ዓይነት እንደ ሆነ ይበልጥ ለማወቅ ቀጣዮቹን መመልከቱ ጠቃሚ ነው፤
1. ‹‹ኀይልህን እንዳታደክምብህ (‹‹ምሥጢርህን እንዳታወጣብህ›› የ1980 ዕትም)፤ ለሴት ልብህን አትስጣት›› (ምዕራፍ 9 ቊጥር 2)፡፡
2. ‹‹ከቁስል ሁሉ ይልቅ የልብ ቁስል ይከፋል፤ ከክፋትም ሁሉ የሴት ክፋት ትከፋለች›› (ምዕራፍ 25 ቊጥር 13)፡፡
3. ‹‹ለውሃ መፍሰሻ አታበጅለት ለሴትም የልብህን ምሥጢር አታውጣለት፡፡ እንደጠባይህ ከልሆነች ፍታት (‹‹ግብሯ እንደ ግብርህ ካልሆነች ፍታት ከሰውነትህም ለያት›› የ1980 ዕትም)›› (ምዕራፍ 25 ቊጥር 24-26)፡፡
ከሴቶች መካከል ክፉዎች እንዳሉ ሁሉ ከወንዶችም መካከል በክፋት የሰለጠኑ ሞልተዋል፤ የሴቶች ክፋት ከወንዶች ክፋት የተለየ ሆኖ የቀረበበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም፡፡ በመልካምነታቸው ብዙዎችን የጠቀሙ ሴቶች ቢኖሩም ከሴት ቸርነት የወንድ ክፋት ተመራጭ ማድረግ፣ ክፉ ሴቶችም ሰዎች በመሆናቸው ከክፋታቸው ሊርቁና በመልካም ስብዕና ሊገነቡ የሚችሉ ቢሆኑም ከእነርሱ ጋር ከመኖር ከምድር አውሬ ጋር መኖር ይሻላል ማለት (ሲራክ 25÷16)፣ ሴቶችን መጨበጥ ጊንጥ እንደ መጨበጥ ነው ማለት (ሲራክ 25÷24-26) ከጥላቻ የተነሣ ካልሆነ ምን ምክንያት ሊሰጠው ይችላል? ደግሞስ ሴቲቱ ምን ክፉ ብትሆን ፍታት ብሎ መምከሩ ‹‹መፋታትን እጠላለሁ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዝአብሔር›› የሚለውን አላነበበው ይሆን (ሚልክያስ 2÷16)?
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚመሰክረው በሰይጣን የተታለለችው ሔዋን ናት (ዘፍጥረት 3÷6፡፡ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2÷14)፡፡ ከዚህ ጥፋት በኋላ እግዚአብሔር ይህን ስላደረግህ ብሎ እንደየጥፋታቸው የተናገራቸው ሦስቱንም (አዳምን፣ ሔዋንንና አሳቹን እባብን) ነው እንጂ ሴቲቱን ብቻ አይደለም፡፡ ሌላው ይቅርና ለሴቱቱ ‹ቀድመሽ ስለበላሽና ምንም የማያውቀውን ሰው እንዲበላ ስላደረግሽው› አላላትም፡፡ ምንም እንኳ እሷ ቀድማ ጥፋቱን ብትሠራም ዘግይቶ ከሠራው ከአዳም የበለጠ ጥፋተኛ አልሆነችም፡፡
መጽሐፈ ሲራክ በተደጋጋሚ ስለ ክፉ ሴት ሲያስነብብ ክፉ የሚለውን ወንድ ግን አንድም ጊዜ ቢሆን ሊያቀርብ አልቻለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ከሴት ደግነት ይልቅ የወንድን ክፋት የተሻለ እንደ ሆነ ሊያስተምር ነው የሞከረው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ፤ ‹‹አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ከአገርህ ደጆች በማንኛይቱም ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ.... ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋልህ›› በማለት ሴትን ከወንድ ሳይለይ ሁለቱንም እኩል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ነው የሚያስተምረው (ዘዳግም 17÷2)፡፡
@gedlatnadersanat