‹‹የክርስቶስ መካከለኝነተ ካሣ ነው፤ ይህ ማለት እርሱ ስለ እኛ ኀጢአት ስርየት መካከለኛ ሆነ፤ በእኛ እግር ዕዳችንን የሚከፍል ዕዳ ከፋይ ሆነ (ኢሳያይስ 53÷6)፡፡ ስለዚህም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ቆመ ወይም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለ ብቸኛ ሆነ፡፡ ለሰዎች ሞቶ ካሣ በመሆን የኀጢአትን ስርየት የሰጠ፣ ለእግዚአብሔር ደግሞ በሰማያዊ ፍርድ መብቱን የሰጠ ሆነ ማለታችን ነው፡፡
‹‹ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊው ‹ልጆቼ ሆይ፥ ኀጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኀጢአትን ቢያደርግ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው› (1ኛ ዮሐንስ 2÷1) አለ፡፡ ይህ ማለት የተገለጸው መካከለኝነት ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ በካሣ መካከለኛ መሆን በጣም ግልጽ ነው፡፡ እርሱም ለኀጢአተኛ መካከለኛ መሆነ ማለት ነው፡፡ ማንም ኀጢአት ቢያደርግ ያ ኀጢአተኛ የሚክስለት ያስፈልገዋል፡፡ ካሣውን የከፈለ አንድ ጻድቅ ደግሞ ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እሱ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ባፈሰሰው ደሙ ስለ እኛ መካከለኛ ሆነ፡፡
‹‹ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል ስላለው ብቸኛ መካከለኝነት የቅዱስ ጳውሎስ አባባልም ተመሳሳይ ትርጕም ይሰጣል፡፡ ‹አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው› (1ኛ ጢሞቴዎስ 2÷5)፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ካሣ ከፋይ ራሱን መስዋዕት አድርጎና የኀጢአታችንን ዋጋ ከፍሎ መካከለኛ ሆነ››
ያየህራድ አስናቀ (ዲያቆን) (ትርጕም)፣ አንጻራዊ ትምህርተ መለኮት በአቡነ ሺኖዳ 3ኛ እንዳጻፉት (1989) ገጽ 52-53፡፡
@gedlatnadersanat

2.9K