Thursday, 26 May 2016

የመጽሐፍቅዱስ አንድነትና ኅብረት Part 5

የመጽሐፍቅዱስ አንድነትና ኅብረት Part 5



Related image

7ኛ ) የመጽሐፍቅዱስ አንድነትና ኅብረት


Related image

መጽሐፍቅዱስ የ66ቱ ቤተ መጻሕፍት መጽሐፍ ነው መጽሐፍቅዱስ የተጻፈው ከ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አመት በፊት ነበር ወደ 40 የሚደርሱ ጸሐፊዎች ነበሩ ወደ ሦስት ለሚደርሱ አህጉራት ተጽፈዋል ኢሲያ አፍሪካና ኤሮፕ ለተባሉ ሀገሮች የተጻፉ ናቸው መጽሐፍቅዱስ ብዙ ከማይስማሙና ከሚያከራክሩ ባለቤቶች ጋር  በጥልቀት ይወያያል ያወራል እስካሁን ግን አስደናቂ የሆነ የአንድነት ንግጝር አለው መጽሐፍቅዱስ ለእኛ ሲነበብልን በአንድ ሰው እንደተጻፈ ሆኖ ነው ተአምረኛው የመጽሐፍቅዱስ አንድነት የቀረበው በመለኮታዊ ተነሳሽነት ነው ማለትም በመለኮታዊ ኢንስፓይሬሽን ነው ልዩ ልዩ አይነት ጸሐፊዎች ሁሉም ተነሳሽነት ያገኙት ወይም ኢንስፓየርድ የሆኑት በአንዱ አይነት መንፈስ መንፈስቅዱስ ነው ሌሎች መጻሕፍቶች አይነጻጸሩትም ወይም አይወዳደሩትም በሀሳብ የተገናኙትም 40 ልዩ ልዩ ሰዎች እየኖሩ የነበሩት በልዩ ልዩ የአለም ክፍሎች ነው እንደገናም ልዩ ልዩ የታሪክ ጊዜያቶች ፣ ለመጻፍም ብዙ የሆኑ  የማይስማሙ የሚያከራክሩ ባለቤቶች  የሚመሳሰሉና አንድ አይነት ንጝግር ያላቸውን መጻሕፍት ከአንድ ጸሐፊ ማግኘት ያለ ነው መጽሐፍቅዱስ የተለየና ልዩ ጠባይም ያለው ነው


 

Related image



 Related image

8ኛ ) የኢየሱስ አቁዋም በብሉይና በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት

 Related image

ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ነበሩ እርሱም በተከታታይ የሚጠቅሳቸውና ሥልጣን ያላቸው ፣ እምነትም የሚጣልባቸው ነበሩ ወንጌልን ስናነብ ኢየሱስ የብሉይኪዳን መጻሕፍት ሁኔታዎች ፍጹም የሆነ ታሪካዊነት ያላቸው መሆናቸውን ለእኛ ግልጽ አድርጎ አሳይቶአል ኢየሱስ የፍጥረትን የመምጣታቸውን ሂሳብ ማለትም በኖህ ዘመን የነበረውን የጥፋት ውሃ ቀን እና ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ የመኖሩን ትርጉዋሜ ያለውና ፍጹም ስሕተት የሌለበት ሁኔታ መሆኑን በሃላፊ ታሪክ ውስጥ ወስዶ አገናዝቦአል  ኢየሱስ እግዚአብሔር የሆነና የእኛንም ሥጋ ጨምሮ የያዘ ነው እግዚአብሔር በእኛ ሰብአዊ ሰውነት መጽሐፍቅዱስን  ማለትም የብሉይኪዳን መጻሕፍት በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እንደነበሩ ያመነ ነው እኛም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ  አንድ አይነት እይታ መያዝ አስፈልጎናል እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነበረውና ሃሳባችንን ስናጠቃልል መጽሐፍቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ሆኖ  ተነሳሽነት ያለውና ሃሳብ የሰጠ ወይንም ኢንስፓየርድ እንደሆነ ማስረጃ አለ ስለዚህ ልናነበውና ልንታዘዘው ያስፈልጋል መጽሐፍቅዱስን ለሕይወታችን ታማኝ አድርገን  ( እምነት የምንጥልበት አድርገን ) መያዝ ፣ በሕይወታችንም ላይ የመጨረሻ ሥልጣን ያለው መሆኑን መረዳት እና  ማስተዋል አለብን መጽሐፍቅዱሳችን በበለጠ፣ በተሻለና በተለየ ሁኔታ እምነት የምንጥልበት ፣  እግዚአብሔርንም  በእርግጠኝነት ምን እንደሚመስልና እኛም እንዴት መኖር እንዳለብን እንደሚፈልግ አበክረን የምንመለከትበት ፣ የዘገባችን ፣ የኢንፎርሜሺናችንም ምንጭ ነው



No comments:

Post a Comment