Thursday, 5 May 2016
( ትምህርት ስምንት ) የትምህርት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር የሚያውቀው ነገር ሲኖር በመከራ ውስጥ ያሳልፈናል (የትምህ..የትምህርቱ ዋና ዋና ነጥቦች የትምህርት ርዕስ ፦ እግዚአብሔር የሚያውቀው ነገር ሲኖር በመከራ ውስጥ ያሳልፈናል ጌታ እግዚአብሔር የሚያውቀው ነገር ሲኖር ሕይወታችንን በተለያዩ መከራዎች ያሳልፈዋል ከእኛ ይልቅ የእኛን ነገር እግዚአብሔር በትክክል ያውቃል ጌታ እግዚአብሔር መልካም ነገራችንንም ሆነ መልካም ያልሆኑ ነገሮቻችንን በእርግጠኝነት ያውቃል በራዕይ መጽሐፍ ጌታ እግዚአብሔር ለኤፌሶን ቤተክርስቲያን እንዲህ ሲል ይናገራታል ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትሕንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንዳትችል፥ እንዲሁም ሳይሆኑ፦ ሐዋርያት ነን የሚሉቱን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ ይለናል ራዕይ 2 ፥ 2 እና 3 ይህ ብቻ አይደለም መዝሙረኛው ዳዊት ወደተናገረው ሃሳብ ስንመጣም ጌታ እግዚአብሔር መቀመጣችንና መነሳታችንን ሃሳባችንን ሁሉ ሳይቀር ከሩቅ ያውቃል ሌላው ቀርቶ እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሠወሩም ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችሕ አዩኝ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ ይለናል መዝሙር (139) ፥ 15 እና 16 ስለዚህ በእግዚአብሔር የማይታወቅ የሕይወት ክፍል የለንም ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ይልቅ እርሱ ሕይወታችንን ከመጀመርያው አንስቶ እስከ መጨረሻው ያውቀዋል ማለትም ከዚህ በፊት የነበረውን አሁን ላይ ያለውን ወደፊትም የሚሆነውን ሕይወታችንን አምላካችን እግዚአብሔር በሚገባ ጠንቅቆ ያውቃል ያልተሠሩ አካሎቻችንን ዓይኖቹ ያዩ እግዚአብሔር ይሄ ትላንት የነበረና አሁን ላይ ያለ ወደፊትም እንደ እርሱ ፈቃድ በፊቱ የሚኖር ሕይወታችን ከእርሱ የተሠወረ ይሆናል ወይም ይጠፋበታል ለማለት አንችልም ከዚህም የተነሣ ጌታ እግዚአብሔር በሕይወታችን የሚያውቀው ነገር ሲኖር በመከራ ውስጥ ያሳልፈናል ታድያ ሕይወታቸውን በመከራ ውስጥ ካሳለፈው ሰዎች መካከል በምሳሌነት የምንመለከታቸው ሰዎች እንዳሉ መጽሐፍቅዱሳችን ይጠቁመናል ፦ 1ኛ ) ኢዮብ ነው ( መጽሐፈ ኢዮብ 16 ፥ 7 _ 16 ) 2ኛ ) ዳዊት ነው ( መዝሙር 42 ፥ 7 ፤ መዝሙር 66 ፥ 12 ) 3ኛ ) ነቢዩ ዮናስ ነው( ትንቢተ ዮናስ 2 ፥ 3 ) 4ኛ ) ከታላቁ መከራ የመጡና ልብሳቸውን በበጉ ደም አጥበው ያነጹ ናቸው ( ራዕይ 7 ፥ 14 ) ጌታ እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ የሚያሳልፈን እኛ ያልተመለከትነው ጌታ እግዚአብሔር ግን በሕይወታችን የተመለከተውና የሚያውቀው ነገር ስላለ ነው ስለዚህም አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ አለን መዝሙር ( 32 )፥ 8 ወገኖቼ ከማንም ይልቅ ለሕይወታችን ጌታ እግዚአብሔር መልካም መምህር ነው ለዚህም ነው ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችሕ ግን አስተማሪህን ያያሉ ያለን ትንቢተ ኢሳይያስ 30 ፥ 20_ 21 ከዚህ የተነሣ ጌታ እግዚአብሔር ሕይወታችንን በልዩ ልዩ መንገድ እያሳለፈ ያስተምረዋል ያሰለጥነዋል ያን ጊዜ የሕይወት ልከኝነት ይኖረናል እኛ በተጽናናንበት መጽናናትም ብዙዎችን የምናጽናና ፣ ከሚያለቅሱት ጋር የምናለቅስ ደስ ከሚላቸውም ጋር ደስ የምንሰኝ እንሆናለን እንደገናም የማያሳፍር ሠራተኞች መሆንም በሕይወታችን በብዙ ይመጣል ከሁሉ በላይ ደግሞ እግዚአብሔርን የመምሰል ባሕርይን በሕይወታችን እናጎለብታለን እናሳድጋለን የተወደዳችሁ ወገኖች ትምህርቱ በእነዚህና በመሳሰሉት ነገሮች ላይ ያጠነጠነ ነው ታድያ ይህንኑ ትምህርት በይበልጥ የሚያብራራ በቪዲዮ የተለቀቀ ተከታታይነት የለው ትምህርት ስለሆነ ትምህርቱ ሳያመልጣችሁ እንድትከታተሉትና ለሌሎችም ትምህርቱን ላላዳመጡ ሁሉ ሼር በማድረግ እንድታስደምጧቸው ይሁን በማለት በታላቅ ትሕትናና አክብሮት እጠይቃለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ .
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment