የጸሐፊዎች ምስክርነት Part 4
6ኛ ) የጸሐፊዎች ምስክርነት
የመጽሐፍቅዱስ ጸሐፊዎች ለጻፉት የምስክርነት ሁኔታ ሁልጊዜ የአይን ምስክሮች ነበሩ በተመሣሣይ ምክንያትም ከእግዚአብሔር መገለጥን የተቀበሉ አይደሉም ወደ ወንጌል ስንመጣ ከሰው ያገኘነው እውቀት ወይም ወሬ የተዘጋጀው በአይን ምስክርነት ነው ከዮሐንስ በስተቀር የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የሞቱት በሰማእትነት ነው የክርስቶስን ሕይወት ሂሳብ ከመካከላቸው ፍጹም የለወጠ የለም
ሀ ) በዚህ ውስጥ ሉቃስ ያገኘው የራሱ ዘገባ ወይንም ኢንፎርሜሺን ምንድነው ስንል መልሱን ፡__ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 1 ፥ 1 እና 2 ላይ በግልጽ ተጽፎ እናገኘዋለን የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ
ይለናል
ለ ) በ2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 16 ላይ ደግሞ
ጴጥሮስም ስለ ኢየሱስ ያገኘው ዘገባ ምንድነው ብለን ስንል የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኃይልና መምጣት አስታወቅናችሁ በማለት ይናገረናል
ሐ ) እንደገናም ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ያገኘው ዘገባ ምንድነው ስንል አሁንም መልሱን በ1ኛ ዮሐንስ 1 ፥ 1 _ 3 ላይ እናገኘዋለን
በ1ኛ ዮሐንስ 1 ፥ 1 _ 3 ላይ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው ይለናል
No comments:
Post a Comment