በመንፈስቅዱስ እንዴት መሞላት እንደሚቻል
Lesson 3 Part 1
ዓላማ ፦ የዚህ ትምህርት ዓላማ እንደ የፈቃዳችን መግለጫ በእምነት እንዴት በመንፈስቅዱስ መሞላት እንደሚቻል እንድንማር ነው
የትምህርት ግቦች ፦ ይህ ትምህርት ፦
1) መንፈስቅዱስ ማን እንደሆነና ለምን እንደመጣ እንድንገነዘብ
2) በመንፈስቅዱስ መሞላት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እንድንችል
3) በፈቃደኝነት በእምነት እንዴት ወደ ውስጥ መተንፈስ ............በመንፈስቅዱስ መሞላት እንደሚቻል እንድንረዳ
4) በመንፈስቅዱስ መሞላት ጋር የተያያዘ ሁለት ጥቅሶችን መጥቀስ እንድንችል
5) ከመንፈስቅዱስ ሙላት ጋር የተያያዙት የሁለት ጥቅሶች የማጠቃለያ ሃሳብ ቁልፍ የሆነውን ቃል ማውጣት እንድንችል ይረዳናል
መግቢያ ፦
ሀ| በመንፈስቅዱስ እንዴት መሞላት |በቁጥጥር ስር መሆንና ኃይል ማግኘት|እንደሚቻል መማር የክርስትና ሕይወት እጅግ ጠቃሚ የሆነው ክፍል ነው
ለ| ደቀመዛሙርት በምድር ላይ በነበረው አገልግሎት ለሦስት ዓመታት ከጌታ ጋር ቢኖሩም ቅሉ በመንፈስቅዱስ እስኪሞሉ ድረስ የጌታን ታላቁ ተልእኮ ለማካሄድ አልተዘጋጁም ነበር (የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 8 )
ሐ) እርሱ ካደረገው የሚበልጥ ሥራ እንደምንሰራ ኢየሱስ ተስፋ ሰጥቶናል ዮሐንስ ወንጌል 14 ፥ 12 _ 14
መ| የሚያሳዝነው ብዙ ክርስቲያኖች በመንፈስቅዱስ እንዴት መሞላት እንደሚችሉ አያውቁም
1) መንፈስቅዱስ ማነው ?
ሀ - ( የሐዋርያት ሥራ 5 ፥ 3 _ 4 )
ለ - ማንነት የሌለው እንዲሁ ኃይል ብቻ ሳይሆን የራሱ አካል ያለው ነው
1ኛ ቆሮንቶስ 2 ፥ 11 ፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5 ፥ 19 ፤ ኤፌሶን 4 ፥ 30
ሐ) ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል የሆነ የሥላሴ ሦስተኛው አካል ነው
ማቴዎስ 28 ፥ 19 ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 13 ፥ 14
2ኛ ) መንፈስቅዱስ የመጣው ለምንድነው ?
ሀ) ክርስቶስን ለማክበር ነው የመጣው
(ዮሐንስ 16 ፥ 7 ፤ 13 ፥ 14 )
ለ) የመጣው ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን ነው
( ዮሐንስ 16 ፥ 13 )
ሐ) የመጣው ክርስቶስን ለማሳወቅና በእርሱ እንድንኖር ኃይል ሊሰጠን ነው
1) የተትረፈረፈውን ሕይወት እንድንኖር ለማድረግ (ዮሐንስ 7 ፥ 37 _ 39 )
2) ለመመስከር (የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 8)
3) ውጤት ያለው ጸሎት እንድንጸልይ
3) በመንፈስቅዱስ መሞላት ምን ማለት ነው ?
ሀ) መሞላትና ኃይል ማግኘት ማለት ነው
በመንፈስቅዱስ መሞላት ከሞት በተነሳው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ መሞላትና በእርሱ መኖር ነው
መሞላት ማለት በመንፈስቅዱስ መመራት መገዛትና ኃይል ማግኘት ማለት ነው በመንፈስቅዱስ ስንመራና ኃይል ስናገኝ በመላ አካል ውስጥ በመመላለስ ክርስቶስ በእኛ በእኛና በእያንዳንዳችን ውስጥ በእኛ በኩል የትንሣኤውን ሕይወት ይገልጻል
ለ) የፈቃድ መግለጫንም ይጨምራል
መንፈሳዊ እስትንፋስ ወደ ውጪ መተንፈስ ኃጢአትን መናዘዝ ሲሆን ወደ ውስጥ መተንፈስ ደግሞ በመንፈስ መሞላት ነው ወደ ውስጥ መተንፈስ የመንፈሳዊ እስትንፋስ ሁለተኛው ክፍል ነው በ1ኛ ዮሐንስ 1 ፥ 9 መሠረት ወደ ውጪ መተንፈስ ኃጢአትን መናዘዝ መሆኑን እናስታውስ
ክርስቲያኖች ሁሉ መንፈስቅዱስ ቢኖርባቸውም በመንፈስ መሞላት ደግሞ ፈቃደኛ የመሆን ምርጫን ይጨምራል ስለዚህ ክርስቲያኖች በሙሉ በመንፈስ ተሞልተዋል ማለት አይደለም
ሐ) በመንፈስ መሞላት በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ የሚከተሉትን አራት ነገሮችን ለማድረግ ያስችላል
1) መንፈስቅዱስ ቅድስና የተሞላበት ሕይወት እንድንኖር ያስችለናል 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 14 _ 16
2) መንፈስቅዱስ መንፈሳዊ ፍሬዎችን እንድናፈራ ያስችለናል ዮሐንስ ወንጌል 15 ፥ 8
3) መንፈስቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንድንረዳና ተግባራዊ ማድረግ እንድንችል ያስችለናል ዮሐንስ ወንጌል 16 ፥ 13
4) መንፈስቅዱስ በየዕለቱ በሚያጋጥመን ችግር ላይ በድል እንድንመላለስ ያስችለናል ሮሜ 8 ፥ 26
4) ለብ ያለው ክርስቲያን በመንፈስቅዱስ የማይሞላው ለምንድነው
ሀ) እውቀት ማጣት
ለብ ያለው ክርስቲያን እውቀት በማጣቱ ምክንያት በመንፈሳዊ ሕይወት በመሸነፍ ይኖራል በመንፈስቅዱስም የተሞላ አይደለም ውጤቱም እምነት ማጣት ይሆናል
ለ) በአለማመን ምክንያት
ለብ ያለው መካከለኛ ሕይወት ያለው ክርስቲያን
በአለማመን ምክንያት በመንፈስቅዱስ አይሞላም
1) ብዙ ሰዎች እግዚአብሔርን ይፈሩታል አይታመኑበትምም
2) ብዙዎች የማይችሉትን ነገር እግዚአብሔር ከእነርሱ የሚጠብቅ ይመስላቸዋል ፤ በሁኔታዎች የማይወሰነውን የእግዚአብሔርን የፍቅር መጠን ይጠራጠራሉ
3) ብዙዎች የሚያስደስታቸውን ነገር እግዚአብሔር የሚወስድባቸው ይመስላቸዋል ፤ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን የሚያስደንቅ ዕቅድ አልተገነዘቡም (ማቴዎስ ወንጌል 6 ፥ 33 )
No comments:
Post a Comment