Friday 25 August 2017

ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አራት ) ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አራት ) የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው የሚለውን የክፍል አስራ አራት ትምህርታችንን ዛሬ ጀምረናል የዳዊት ልጅ የሚለው መሲሃዊ የማዕረግ ስም ነው የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 27 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 1 እንዴት የማዕረግ ስም ሊሆ ቻለ ? ስንል ለእስራኤል ሕጋዊ ንጉሥ ለሆነው ለዳዊት እግዚአብሔር ዙፋኑን ለዘላለም ሊያደርግ ቃልኪዳን ገብቷል 2ኛ ሳሙኤል 7 ፥ 12 _ 17 ሕጋዊ የማዕረግ ስም የሆነበትም ከዚህ የተነሳ ነው ስለሆነም የዳዊት ልጅ ሊመጣ ላለው ለመሲሁ የታወቀ መጠርያ ነበረ ይሁን እንጂ በማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 20 ላይ የተመለከተው ቃል ግን መሲሃዊ የማዕረግ ስም አይደለም ወንጌሉን የጻፈው ማቴዎስ ለአይሁድ ስለነበረ የጻፈው የኢየሱስን የትውልድ ሐረግ በዚህ መንገድ መግለጹ ተገቢ ነበረ ይሁን እንጂ የትውልድ ሐረጉንና ከየት መጣውን በዝርዝር አወቁ ብለን ባንገምትም የዳዊት ቤት ተስፋን ሰምተዋልና በዳዊት ቤትና በዳዊት ቤት ተስፋ ውስጥ የመጣውን መሲሃዊ ማዕረግ በእስራኤል ምድር ያሉትና ከእስራኤል ቤት ውጪ ያሉ ዕውሮች አንካሶች ለምፃሞችና የመሣሠሉት ሁሉ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን ብለዋል በማቴዎስ ወንጌል 12 ፥ 22 _ 32 መሠረት ደግሞ ዕውርና ዲዳ የነበረው ሰው እስኪናገርና እስኪያይ ድረስ በመፈወሱ ምክንያት የዳዊት ልጅ ይሆንን ? ቢሉም ፈሪሳውያን ግን ሰምተው ይህ በቡዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ አጋንንት አያወጣም አሉ ኢየሱስም ሃሳባቸውን አውቆ እርስ በእርስዋ የምትለያይ መንግሥት እንደምትጠፋ ከነገራቸው በኋላ እኔስ በቡዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል ? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል አላቸው አያይዞም እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንት የማወጣ ከሆንሁ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች ሲላቸው እንመለከታለን ታድያ እነዚያ ፈውሱንና ተአምራቱን የተመለከቱ ሰዎች የዳዊት ልጅ ይሆንን ያሉ አንደኛ በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን ያወጣ መሆኑን የተመለከቱ ፣ ሌላኛውና ሁለተኛው ሃሳብ ደግሞ የዳዊት ልጅ የሆነበትን መሲሃዊ ማዕረግ የተገነዘቡ ይመስላሉ መሲሁን የተቃወሙት ፈሪሳውያን ግን ይህንን ሁሉ እውነት ያልተቀበሉ ናቸው እንደገናም በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ ሕዝቦች ኢየሱስን የዳዊት ልጅ እንደሆነ አድሬስ አድርገዋል ሕጻናቱም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ ዘምረዋል የማቴዎስ ወንጌል 21 ፥ 5 ፣ 9 ን ይመልከቱ መሲሁ ኢየሱስም የተወለደው በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ነው የማቴዎስ ወንጌል 2 ፥ 1 እና 2 ከዚህም ሌላ ኢየሱስ መሲሃኒክ ታይትል ነበረው Primarily, the title “Son of David” is more than a statement of physical genealogy. It is a Messianic title ከዚህ የተነሳም የሃይማኖትን ሕግ ለሚያስጠብቁ የሕግ መምሕራን ትኩረታቸው ሆኖ ነበር መዝሙር 110 ፥ 1 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 22 ፥ 42 _ 46 በዚህ ጉዳይ ከአይሁድ ጋር የማትተባበረዋ ሳምራዊቷ ሴት ሳትቀር ክርስቶስ የሚባል መሲህ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል ስትል ለኢየሱስ መልስ የሰጠችበት ቃል እጅግ የሚደንቅና በመሲሁ ላይ የተደረገ የትኩረት አቅጣጫን የሚያሳይና ለሳምራውያን ሕዝቦች በሙሉ መታምንንም ጭምር ያመጣ አመላካች ቃል መሆኑን ይጠቁማል የዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 25 ኢየሱስ የዳዊት ልጅ በመባሉ ምክንያት ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው ፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ተብሏል ወደ ሮሜ ሰዎች 1 : 3 እና 4 በጢሞቴዎስ መጽሐፍ ላይም በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ ተብሎም ተነግሯል 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2 : 8 ከዚህም ሌላ የዳዊት ሥርና ዘር ነው የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነው ራዕይ 22 ፥ 16 የዳዊት ቊጥቋጥም ነው ስለዚህም እንደ ንጉሥ ይነግሳል ይከናወንለትማል በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል የሚጠራበትም ስም እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው ትንቢተ አርምያስ 23 ፥ 5 _ 7 ወገኖቼ የትምህርቱ ጥቅል ሃሳብ በአጭሩ እንግዲህ ይህንን የሚመስል ነው ይበልጥ ለመረዳት ደግሞ ቪዲዮውን ያዳምጡት ከዚህ በተረፈ የምለው ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ነው በክፍል አስራ አምስት ትምህርት እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment