Tuesday 22 August 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሦስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሦስት ) ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ሕዝቦች በክፍል አስራ ሦስት የምንመለከተው እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል በሚለው በ1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 25 ላይ የተመሠረተን ትምህርት ነው መጽሐፉን አስተውለን ስንመለከት ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ሲል ይንገረን እንጂ የተመለስነው እኛ አይደለንም በመጀመርያ የመለሰን እርሱ ራሱ ነው እንዴት መለሰን ? ስንል በትንቢተ ኢሳይያስ 53 ፥ 6 ላይ ኲልነ ከመ አባግዕ ተገደፍነ ብእሲኒ ዘዘዚአሁ ሆረ በፍኖቱ ወስሕተ ወመጠዎ እግዚአብሔር በእንተ ኃጣወኢነ ትርጉም እኛ ሁላችን እንደ በጐች ተቅበዘበዝን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ ይለናል ስለዚህ እረኛችን ኢየሱስ የመለሰን በደላችንን ተሸክሞ ፣ ስለ እኛ ኃጢአት ሆኖ ፣ የደኅንነታችንን ተግሣጽ ተቀብሎ ፣ በቁስልና በደዌ በሕማም ውስጥ ሆኖ ፣ በመቃብር ውስጥ አድሮና ሲኦል ድረስ ሄዶ ነው የመለሰን ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ን ብናነብ ሙሉ የሆነን መልስ እናገኛለን ለዚህም ነው እንግዲህ የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ የኢሳይያስን ትንቢት በመጥቀስ በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ወደ እርሱ አመጡ በነቢዩ በኢሳይያስ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃሉ አወጣ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ በማለት የነገረን የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 16 እና 17 ን ይመልከቱ ከዚህ የተነሳ ኢየሱስ ለእነዚህ ሁሉ ሕሙማንና ደካሞች እንዲሁም በአጋንንት አሠራር ለተጠቁ ሁሉ ቦታ ስለነበረው በሰዓታት ሳይገደብ ጊዜያቶችን ሁሉ በጎ ለማድረግ ተጠቀመ ከዚህም ሌላ ይሄ ምሽት በሰዓት መፈራረቅ የመጣ የተፈጥሮ ምሽት ብቻ ሳይሆን በደዌ በታሰሩና በታመሙም ሰዎች ሕይወት ላይ አጥልቶ ያለ ምሽት ነበር ስለዚህ ኢየሱስ በእነዚህ ሰዎች ሕይወት ላይ ያጠላውን ድቅድቁን ምሽት ሳይቀር ሊያነጋው መናፍስትን በቃሉ አወጣ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ ይለናል በመሆኑም ሳይፈወስም ሆነ ነጻ ሳይወጣ ወደ ቤቱ የተመለሰ አንድም ሰው አልነበረም እንደገናም በዚህ ጉዳይ ላይ ኢየሱስ ሲሪየስ አቋም ስለነበረው ነጻ የማውጣቱንም ሆነ የመፈወሱን አገልግሎት እርሱ ብቻ ፈጽሞት ያለፈ ብቻ ሳይሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ለደቀመዛሙርቱ መከሩስ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት ሲላቸው እንመለከታለን ኢየሱስ የመጣበት ዋነኛው አጀንዳና አንገብጋቢው ጉዳይ ይሄ ነበር ታድያ የኢየሱስ ዋንኛው አጃንዳ የእኛ የአገልጋዮች ዋነኛ አጅንዳ ሆኖና እኛ ብቻ ከሚለው ወጥተን የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ልንለምን ይገባል የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 35 _ 38 በዚህ ትምህርት ውስጥ ሰዎችና በዘመኑ የነበሩ የምኩራብ አለቆች ቦታ ያልሰጧቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት አድርጎ ቦታ እንደሰጣቸውና እንደፈወሳቸው ተመልክተናል ዝርዝር ሃሳቡ በቪዲዮ ስለቀረበ የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ ለዚህም ነው እንግዲህ መጽሐፍቅዱሳችን ሁላችን እንሞታለን በምድርም ላይ እንደፈሰሰና እንደማይመለስ ውሃ ነን እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድም ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል ሲል የነገረን 2ኛ ሳሙኤል 14 ፥ 14 ኢየሱስ የናዝሬቱ ሰው ለተባልን ለማንኛችንም ሰዎች ሁሉ የሚሆን ቦታ ስላለው በእኛ በሰዎች ነገር give up ( ጊቭ አፕ ) አያደርግም ከዚህ የተነሳ የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል እንደገናም አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ የሆነና ለሚጠሩትም ባለጸጋ ስለሆነ በሰዎች መካከል ልዩነት አያደርግም ሮሜ 10 ፥ 12 ስለዚህ እኛም በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት መያዝ የለብንም የያዕቆብ መልዕክት ምዕራፍ 2 ፥ 1 _ 7 የእስራኤል ነቢይ ሙሴም እንደተናገረው በፍርድም አድልዎ ባለማድረግ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት ሳንፈራ ፣ ታላቁን እንደምንሰማ ታናሹንም እንዲሁ ልንሰማ ይገባል ይለናል ዘዳግም 1 ፥ 17 ፣ ቆላስያስ 3 ፥ 25 በመጨረሻም ልለው የምፈልገው መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል ስለሚል ዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 11 ሕይወቱን ለመከራና ለሞት አሳልፎ የሰጠን ኢየሱስ ዛሬም ከእኛ ጋራ ነው እርሱ ለዓለምና ለዘላለም የመራናል የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ተባረኩ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment