Monday 14 August 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ አንድ ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ አንድ ) ኢየሱስ ምሳሌና አርአያ የሆነበትን ሕይወት ነው እየተመለከትን ያለነው በዛሬው ዕለት እንደ መነሻ አድርገን የወሰድነው ጥቅስ 1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 21 _ 25 የተጻፈውን ቃል ነው ክርስቶስ ፍለጋውን እንድንከተል ምሳሌ ትቶልናል እርሱ ኃጢአትን አላደረገም ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ የሚለውን ሃሳብ ነው የተመለከትነው በሚቀጥለው ክፍለ ጊዜያችን ቀጣዩን የትምህርት ሃሳብ እንመለከታለን ታድያ ጴጥሮስ ክርስቶስ ምሳሌ የሆነበትን ሕይወት በእንዲህ መልኩ ሲዘረዝረው ኢሳይያስ በትንቢቱ ደግሞ _ _ _ ተጨነቀ ተሰቃየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም _ _ _ _ ከባለጠጐችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር በማለት ነገረን ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 በሙሉ ቁጥር 7 _ 12 መመልከት እንችላለን ማርቆስ በወንጌሉ ደግሞ ይህንንኑ ሃሳብ በማጠናከር የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር እርሱ ግን ምንም አልመለሰም ጲላጦስም ደግሞ አንዳች አትመልስምን ? እነሆ በስንት ነገር ያሳጡሃል ? ብሎ ጠየቀው ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም ይለናል ( የማርቆስ ወንጌል 15 ፥ 3 _ 5 ) ይህ እንግዲህ በማንም ዘንድ የማንመለከተው ፣ በየትኞቻችንም ውስጥ የሌለ እና ብሎም እንዲኖርም ጭምር የምንፍጨረጨርለት አስደናቂው የኢየሱስ የሕይወት አርአያነትና ተምሳሊትነት ነው ታድያ ይሄ ኢየሱስ ወደ መስቀል በሄደበት ጊዜም ሆነ ከመስቀሉ ጉዞ በፊት ኃጢአትን ያላደረገ ፣ ተንኮልም በአፉ ያልተገኘበት ፣ ሲሰድቡት መልሶ ያልተሳደበ ፣ መከራንም ሲቀበል ያልዛተና በጽድቅ ለሚፈርደው ዳኛ ራሱን አሳልፎ የሰጠ ቢሆንም በምድር በተመላለሰበት ጊዜና በመዋዕለ ትምህርቱ ግን የሕግ መምህራን አለቆችንና በዓመጻ የታሰሩ ሰዎችን እንደገናም ትምህርቱን ሊካፈሉ የመጡ ሰዎችን ፣ ደቀመዛሙርቱንና የቅርብ ተከታዮችን ሳይቀር ጥፋትን አይቶ ባለማለፍ ይስተካከሉ ዘንድ እንደ አስፈላጊነቱ የገሰጸበት ፣ የዘለፈበት ፣ የነቀፈበት ፣ ያስጠነቀቀበት ፣ የመከረበት ፣ እንዲሁም መጽናናትና መበረታታት በሚያስፈልጋቸው ጊዜ መጽናናት መበረታታ ያስፈለጋቸውን ሰዎች ሁሉ ደግሞ ያጽናናበትና ያበረታታበት ጊዜ ነበር ታድያ የክርስቶስ ትምህርት በእነዚህ እውነቶች ሁሉ የተቃኘ በመሆኑ በእውነተኛ ልብ የሰሙትን ሰዎች ሁሉ ሙሉ የሚያደርግ ነው ውድ ወገኖቼ ሆይ እንግዲህ የክርስቶስ ትምህርት የክርስቶስ ብቻ ሆኖ ሊቀር አይገባም የክርስቶስ ትምህርት የቤተክርስቲያን ትምህርት ሊሆን ይገባል ፤ የክርስቶስ ትምህርት የቅዱሳን ሁሉ ትምህርት ሊሆን ይገባል ፤ ያኔ ነው እንግዲህ የቤተክርስቲያን ሰማያዊ ቃልዋና ሥልጣንዋ ወጥቶ ፣ ተገልጦም በትንቢተ ኢሳይያስ 2 ፥ 1 _ 5 በተጻፈው ሃሳብ መሠረት የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉበአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ ተብሎ በተነገረው ቃል መሠረት ሲነገር ለውጥን የሚያመጣ ነውና ከዚህ የተነሳ ዛሬ ላይ ያለን በክርስቶስ ስም የተጠራን የክርስቶስ አብያተክርስቲያናት በሙሉ በዚህ የእውነት ልክ ልንመላለስ ግድ ሊለን ይገባል የክፍል አስራ አንድ አጠቃላይ መልዕክት እንግዲህ ይህንን ይመስላል በተጨማሪ የተለቀቀውን ቪዲዮ ስትሠሙት የበለጠ ትባረኩበታላችሁና ቪዲዮውን እንድትሠሙና እንድታዳምጡ ላበረታታችሁ እወዳለሁ ስለዚህ ይህንን ቪዲዮ ጊዜ ወስዳችሁ ስሙት አዳምጡት ተከታተሉት ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ የክፍል አስራ ሁለት ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩ ፣ ሰላም ሁኑ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment