Thursday 17 August 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሁለት )የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሁለት ) የተወደዳችሁ ቅዱሳን ወገኖች በሙሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን የክርስቶስን አርአያነትና ምሳሌነትን አስመልክቶ አሁንም በ1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 24 ላይ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ይለናልና በዚሁ ቃል መሠረት ኃጢአትን አለማድረግም ሆነ ለኃጢአት መሞት የምንችለው ኢየሱስ ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ እንደተሸከመ ስናምንና በመገረፉ ቁስል እንደተፈወስን ወይም መፈወሳችንን ስናረጋግጥ ብቻ ነው ታድያ ሰዎች ከዚህ ቃል በተለየ መልኩ ኃጢአትን አድርጎ ላለመሳሳትና ለኃጢአትም ለመሞት ሲሉ የማይፈጽሙት ሃይማኖታዊ ስነ ምግባር የለም ይህ ብቻ አይደለም ኃጢአትን ላለማድረግና ለኃጢአትም ለመሞት ሲሉ በገዛ ሰውነታቸው ላይ ሳይቀር ስለት ማለትም ካራና ቢላዋ ይመዛሉ አካላቸውንም በዚሁ ቢላዋ ይቆራርጣሉ በአጠቃላይ በአለንበት በዓለማችን የማይደረግ ምንም ነገር የለም ሰዎች ሁሉ ግን ይሄንን አድርገው ኃጢአትን ላለመስራት ጨክነውና ወስነው ኃጢአትን ከዚህ በኋላ በቀላሉ እገላገለዋለሁ ሲሉ በወሰዱት ሥጋዊ የሆነ የኃይል እርምጃ በዋዛና በቀላሉም የሚገላገሉት አይሆኑም እንደውም ነገሩ እየባሰ መጥቶ እየጨመረ ይሄዳል እንጂ የሚቀንስ አይሆንም በሰውነቶቻችን ላይ የሚያርፉት ካራዎችም ሆኑ ሃይማኖታዊ ስነምግባራት እኛን ከኃጢአትም ሆነ ከሞት ሊታደጉንና በጽድቅ ለእግዚአብሔር ሊያኖሩን አይችሉም ይልቁንም የሚጨምሩብን ከፍተኛ የሆነ ስቃይ የበዛበት የአካል መጉደልንና ጠባሳን እየከፋ መጥቶ ከሆነ ደግሞ ከንቱ የሆነ ልፋትንና ሞትንም ጭምር የሚያተርፍልን ነው በመሆኑም ወደ መጽሐፍቅዱሳችን እውነት ስንመለስ ፣ መጽሐፍቅዱሳችንንም ብቻ ለመከተል ስንወስን ፣ መጽሐፍቅዱስ የሚነግረን አንድ እውነት አለ ለኃጢአት የሞትነው ገዳም ገብተን ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር ተሰቅለን ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ 2 ፥ 20 ላይ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ይለናል በዚህ የትምህርት ማብራርያዬ ላይ የገዳምን ሕይወት አንስቼ ከራሴና ከግል ሕይወቴም በመነሳት እኔም ገዳማዊ ሕይወት የነበረኝና ከምንኩስናም አልፎ እስከ ቊምስና ማዕረግ ደርሼ የገዳምን ሕይወትና ኑሮውንም ጭምር ጠንቅቄ የማውቅ በመሆኔ እኔም ሆንኩ እኔን የመሰሉ ሌሎች ሰዎች ገዳም የገባነው ፣ የመነኮስነውም ኃጢአት ላለማድረግ ፣ ለኃጢአትም ለመሞት ከዚያም መልስ ደግሞ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ ለመኖር ነበር እኔ ጌታን ባላወኩበት ዘመን ያለኝ አስተሳሰብና የነበረኝም ሃይማኖታዊ መረዳት ይሄ ስለነበረ መንኮሰ ማለት ሞተ ማለት ነውና የመነኮስኩት ለኃጢአት ሞቼ ለጽድቅ ለመኖር ነበር ነገር ግን በገዳም ባለ የምንኩስና ሥርዓት መንገድ መንኮሰ ሞተ ማለት ሆኖ ጨርሰን ተገንዘንና የሞትን ሆነን በመመንኮስ እኔም ሆንኩ እኔን የመሰሉ ሰዎች ሞተናል ብንልም በመመንኮስም ሆነ መንኩሶ ሰውነትን በማጐሳቆል ለኃጢአት መሞት አይቻልም ለምን ብንል እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ ወበዐመፃ ወለደተኒ እምየ ይለናል ወደ አማርኛ ሲተረጎም እነሆ በዓመፃ ተፀነስኩ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነው መዝሙር 50 ( 51 ) ፥ 5 ከዚህ የተነሳ ከአዳም ጀምሮ ያለ የውርስ ኃጢአት ስላለ ምን ሰውነታችንን ብናጎሳቁል ፣ ገዳምም ገብተን ብንመነኩስና የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ብንፈጽም ውስጣችን ያለ የኃጢአት ባሕርይ ስላለ ኃጢአት መስራታችን የማይቀር ጉዳይ ነው ስለዚህ በምንኩስናም ሆነ ሰውነትን በማጎሳቆል ለኃጢአት መሞትም ሆነ ለጽድቅ መኖር አይቻልም ለዚህ ነው ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ያለን ታድያ እኛም ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ ለመኖር ስንል ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ አሁን ሕያው ሆኔ አልኖርም ማለት አለብን ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲሉ ከክርስቶስ ጋር ለመሞት ደግሞ ክርስቶስን የሕይወታችን ጌታና አዳኝ አድርገን መቀበል አለብን የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቊጥር 12 ይመልከቱ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ማለት የሚችል የዳነና ክርስቶስን የሕይወቱ ጌታ አዳኝም አድርጎ የተቀበለ ሊሆን ይገባል ከዚህ ውጪ ግን በክርስቶስ አምነን ሳንድን ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ማለት አንችልም ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ በምንልበት ወቅት ግን ያን ጊዜ ነው ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ መኖር የምንችለው መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ተሰቅያለሁ እንድንል ብቻ ሳይሆን ሞቻለሁም እንድል ስለሚፈልግ በተለያዩ ክፍሎች ላይ ሞታችኋል ይለናል ይሁን እንጂ መሰቀላችንም ሆነ መሞታችን እንደገናም በምንኩስና ሥርዓትና ደንብ መንኮሰ ሞተ ተብለንና ለብቻችንም በሆነ ሞት ሞተን ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር ሆነን እና ሞተን ነው ከክርስቶስ ጋር የተሰቀለና የሞተ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር የተነሣ ነው በዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ በቆላስያስ 3 ፥ 1 _ 4 ላይ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ በማለት የነገረን ክብር ሁሉ ለወደደን ጌታ ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን ለኢየሱስ ይሁንለት በምንኩስና ሥርዓት ባለ የመሞትና የመጐሳቆል ሕይወት ግን ትንሣኤ የሌለበት ሕይወት ነውና ቀቢጸ ተስፋ ስለሆነ በላይ ያለውን አስቦ ሕይወቴ ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአል ሕይወቴ የሆነው ክርስቶስ ሲገለጥ ከእርሱ ጋር አብሬ እገለጣለሁ ሲሉ መናገርም ሆነ ማመን የለም ስለዚህ ገዳም ገብቶና ተገንዞ ያለ የምንኩስናው ሞት ከክርስቶስ ጋር የሆነ ሞት ስላልሆነ ትንሣኤ የሌለበት ዘላለማዊ ሞት ነው የእኛ ጽድቅ ግን የተረጋገጠው በክርስቶስ ትንሣኤ በመሆኑ ሕያውነትን የሚያበስር ነው ይሁን እንጂ ታድያ በምንኩስና ሞት ግን ትንሣኤም ሆነ የሚረጋገጥ ዘላለማዊ ጽድቅ የለም በመሆኑም ሰዎች ገዳም ገብተው መንኩሰውና ሞተው እንዳይቀሩ ስለ እነርሱ የሞተውንና እነርሱን ስለማጽደቅ ደግሞ ከሞት የተነሳውን ኢየሱስን አበክረን ልንነግራቸው ልንሰብካቸውም ይገባል በምንኩስናና ገዳማዊ ኑሮ ሰበብ ሞትን ያወጀባቸውም ማን እንደሆነ በጽኑ ልናስረዳቸውና ልናማክራቸውም ያስፈልጋል ሰይጣን የመጀመርያዎቹን ሰዎች አዳምንና ሔዋንን አትሞቱም ብሎ ዋሽቶም እንደገደላቸው ሁሉ ዛሬም ላይ ያሉ ሰዎችን ደግሞ ገዳም እንዲመሠርቱ እያደረገና ወደገዳምም እየላከ ምንኩስና የጽድቅ ሕይወት ነውና መንኩሱ እያለ ብዙዎችንም በገዳም እያጐሳቆለ ተስፋ አሳጥቶ ይገላል በዚህም ምክንያት ነው እንግዲህ ከመጀመርያ ነፍሰ ገዳይ ነው እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል ሐሰተኛ የሐሰት አባት ነውና ተብሎ በቃሉ የተጻፈልን የዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 44 መልዕክቴን ስጠቀልለው እኛ ግን ከዚህ ሁሉ ስላመለጥን ለሞተውና ለተነሳው ለክርስቶስ ኖረን ሌላውን ለማኖር ለራሳችን መኖርን ማቆምና ለክርስቶስና የክርስቶስ ብቻ ሆነን ልንቀር ፣ በክርስቶስም ፍቅር ግድ ልንሰኝ መነሳት አለብን ለዚህ አባባል አስረጂ የሚሆነን 2ኛ ቆሮንቶስ 5 ፥ 14 እና 15 ነውና መጽሐፍቅዱስዎን ገልጠው ያንብቡ ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ጽሑፍም ሆነ በተለቀቀው የቪዲዮ ትምህርት ፈጽሞ ይባርከን ያሳድገን ደግሞም ይለውጠን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment