Wednesday 30 August 2017

ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ክፍል አስራ አምስት ( ቊጥር 1 ) ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ክፍል አስራ አምስት ( ቊጥር 1 ) የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን የዛሬውን ትምህርት ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው በሚል አርዕስት ጀምረናል ኢየሱስ ሰባ ስምንት ጊዜ ያህል ራሱን የሰው ልጅ በሚል ታይትል ጠርቷል በዚህ ውስጥ ደቀመዛሙርቱን የእርሱን አይደንቲቲ ጠየቀ የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 13 ኢየሱስ የሰው ልጅ የሆነበትን ጉዳይ ስንመለከት ኢየሱስ ፍጹም ሰው መሆኑን እንመለከታለን ኢየሱስ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ፍጹም ሰው ሆኖ የኖረበትን ሕይወት እናያለን ኢየሱስ የሰው ልጅ የሆነበት ትልቁ ምክንያት የሙሴን ሕግ ለመፈጸምና ለመጠበቅ ነው ለምን ስንል የአዳም ዘር የሆነ ሁሉ የሙሴን ሕግ መጠበቅ ስለማይችል ነው የሰው ልጅ የሚለው ታይትሉ ወይንም የተሰጠው ስያሜ ከምድራዊ ሕይወቱ ጋር የተያያዘ ነው የማርቆስ ወንጌል 2 ፥ 10 ከዚህ የተነሣ ለሰንበት እንኳ ሳይቀር ጌታዋ ነው የማርቆስ ወንጌል 2 ፥ 28 እንደገናም ኢየሱስ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይ ወፎችም መሣፈርያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው ይለናል የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 20 የትምህርቱ ጠቅላላ ሃሳብ ይህ ነው ቪዲዮውን ስትሰሙት ደግሞ በተብራራ መልኩ የቀረበ ስለሆነ በብዙ ትጠቀማላችሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Friday 25 August 2017

ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አራት ) ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አራት ) የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ኢየሱስ የዳዊት ልጅ ነው የሚለውን የክፍል አስራ አራት ትምህርታችንን ዛሬ ጀምረናል የዳዊት ልጅ የሚለው መሲሃዊ የማዕረግ ስም ነው የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 27 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 1 እንዴት የማዕረግ ስም ሊሆ ቻለ ? ስንል ለእስራኤል ሕጋዊ ንጉሥ ለሆነው ለዳዊት እግዚአብሔር ዙፋኑን ለዘላለም ሊያደርግ ቃልኪዳን ገብቷል 2ኛ ሳሙኤል 7 ፥ 12 _ 17 ሕጋዊ የማዕረግ ስም የሆነበትም ከዚህ የተነሳ ነው ስለሆነም የዳዊት ልጅ ሊመጣ ላለው ለመሲሁ የታወቀ መጠርያ ነበረ ይሁን እንጂ በማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 20 ላይ የተመለከተው ቃል ግን መሲሃዊ የማዕረግ ስም አይደለም ወንጌሉን የጻፈው ማቴዎስ ለአይሁድ ስለነበረ የጻፈው የኢየሱስን የትውልድ ሐረግ በዚህ መንገድ መግለጹ ተገቢ ነበረ ይሁን እንጂ የትውልድ ሐረጉንና ከየት መጣውን በዝርዝር አወቁ ብለን ባንገምትም የዳዊት ቤት ተስፋን ሰምተዋልና በዳዊት ቤትና በዳዊት ቤት ተስፋ ውስጥ የመጣውን መሲሃዊ ማዕረግ በእስራኤል ምድር ያሉትና ከእስራኤል ቤት ውጪ ያሉ ዕውሮች አንካሶች ለምፃሞችና የመሣሠሉት ሁሉ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን ብለዋል በማቴዎስ ወንጌል 12 ፥ 22 _ 32 መሠረት ደግሞ ዕውርና ዲዳ የነበረው ሰው እስኪናገርና እስኪያይ ድረስ በመፈወሱ ምክንያት የዳዊት ልጅ ይሆንን ? ቢሉም ፈሪሳውያን ግን ሰምተው ይህ በቡዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ አጋንንት አያወጣም አሉ ኢየሱስም ሃሳባቸውን አውቆ እርስ በእርስዋ የምትለያይ መንግሥት እንደምትጠፋ ከነገራቸው በኋላ እኔስ በቡዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንኩ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል ? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል አላቸው አያይዞም እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንት የማወጣ ከሆንሁ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች ሲላቸው እንመለከታለን ታድያ እነዚያ ፈውሱንና ተአምራቱን የተመለከቱ ሰዎች የዳዊት ልጅ ይሆንን ያሉ አንደኛ በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን ያወጣ መሆኑን የተመለከቱ ፣ ሌላኛውና ሁለተኛው ሃሳብ ደግሞ የዳዊት ልጅ የሆነበትን መሲሃዊ ማዕረግ የተገነዘቡ ይመስላሉ መሲሁን የተቃወሙት ፈሪሳውያን ግን ይህንን ሁሉ እውነት ያልተቀበሉ ናቸው እንደገናም በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ ሕዝቦች ኢየሱስን የዳዊት ልጅ እንደሆነ አድሬስ አድርገዋል ሕጻናቱም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ ዘምረዋል የማቴዎስ ወንጌል 21 ፥ 5 ፣ 9 ን ይመልከቱ መሲሁ ኢየሱስም የተወለደው በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ነው የማቴዎስ ወንጌል 2 ፥ 1 እና 2 ከዚህም ሌላ ኢየሱስ መሲሃኒክ ታይትል ነበረው Primarily, the title “Son of David” is more than a statement of physical genealogy. It is a Messianic title ከዚህ የተነሳም የሃይማኖትን ሕግ ለሚያስጠብቁ የሕግ መምሕራን ትኩረታቸው ሆኖ ነበር መዝሙር 110 ፥ 1 ፣ የማቴዎስ ወንጌል 22 ፥ 42 _ 46 በዚህ ጉዳይ ከአይሁድ ጋር የማትተባበረዋ ሳምራዊቷ ሴት ሳትቀር ክርስቶስ የሚባል መሲህ እንዲመጣ አውቃለሁ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል ስትል ለኢየሱስ መልስ የሰጠችበት ቃል እጅግ የሚደንቅና በመሲሁ ላይ የተደረገ የትኩረት አቅጣጫን የሚያሳይና ለሳምራውያን ሕዝቦች በሙሉ መታምንንም ጭምር ያመጣ አመላካች ቃል መሆኑን ይጠቁማል የዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 25 ኢየሱስ የዳዊት ልጅ በመባሉ ምክንያት ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው ፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ተብሏል ወደ ሮሜ ሰዎች 1 : 3 እና 4 በጢሞቴዎስ መጽሐፍ ላይም በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ ተብሎም ተነግሯል 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2 : 8 ከዚህም ሌላ የዳዊት ሥርና ዘር ነው የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነው ራዕይ 22 ፥ 16 የዳዊት ቊጥቋጥም ነው ስለዚህም እንደ ንጉሥ ይነግሳል ይከናወንለትማል በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል የሚጠራበትም ስም እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው ትንቢተ አርምያስ 23 ፥ 5 _ 7 ወገኖቼ የትምህርቱ ጥቅል ሃሳብ በአጭሩ እንግዲህ ይህንን የሚመስል ነው ይበልጥ ለመረዳት ደግሞ ቪዲዮውን ያዳምጡት ከዚህ በተረፈ የምለው ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ነው በክፍል አስራ አምስት ትምህርት እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Tuesday 22 August 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሦስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አስራ ሦስት ) ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሔር ሕዝቦች በክፍል አስራ ሦስት የምንመለከተው እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል በሚለው በ1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 25 ላይ የተመሠረተን ትምህርት ነው መጽሐፉን አስተውለን ስንመለከት ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ሲል ይንገረን እንጂ የተመለስነው እኛ አይደለንም በመጀመርያ የመለሰን እርሱ ራሱ ነው እንዴት መለሰን ? ስንል በትንቢተ ኢሳይያስ 53 ፥ 6 ላይ ኲልነ ከመ አባግዕ ተገደፍነ ብእሲኒ ዘዘዚአሁ ሆረ በፍኖቱ ወስሕተ ወመጠዎ እግዚአብሔር በእንተ ኃጣወኢነ ትርጉም እኛ ሁላችን እንደ በጐች ተቅበዘበዝን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ ይለናል ስለዚህ እረኛችን ኢየሱስ የመለሰን በደላችንን ተሸክሞ ፣ ስለ እኛ ኃጢአት ሆኖ ፣ የደኅንነታችንን ተግሣጽ ተቀብሎ ፣ በቁስልና በደዌ በሕማም ውስጥ ሆኖ ፣ በመቃብር ውስጥ አድሮና ሲኦል ድረስ ሄዶ ነው የመለሰን ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 ን ብናነብ ሙሉ የሆነን መልስ እናገኛለን ለዚህም ነው እንግዲህ የማቴዎስ ወንጌል ጸሐፊ የኢሳይያስን ትንቢት በመጥቀስ በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ወደ እርሱ አመጡ በነቢዩ በኢሳይያስ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ መናፍስትን በቃሉ አወጣ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ በማለት የነገረን የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 16 እና 17 ን ይመልከቱ ከዚህ የተነሳ ኢየሱስ ለእነዚህ ሁሉ ሕሙማንና ደካሞች እንዲሁም በአጋንንት አሠራር ለተጠቁ ሁሉ ቦታ ስለነበረው በሰዓታት ሳይገደብ ጊዜያቶችን ሁሉ በጎ ለማድረግ ተጠቀመ ከዚህም ሌላ ይሄ ምሽት በሰዓት መፈራረቅ የመጣ የተፈጥሮ ምሽት ብቻ ሳይሆን በደዌ በታሰሩና በታመሙም ሰዎች ሕይወት ላይ አጥልቶ ያለ ምሽት ነበር ስለዚህ ኢየሱስ በእነዚህ ሰዎች ሕይወት ላይ ያጠላውን ድቅድቁን ምሽት ሳይቀር ሊያነጋው መናፍስትን በቃሉ አወጣ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ ይለናል በመሆኑም ሳይፈወስም ሆነ ነጻ ሳይወጣ ወደ ቤቱ የተመለሰ አንድም ሰው አልነበረም እንደገናም በዚህ ጉዳይ ላይ ኢየሱስ ሲሪየስ አቋም ስለነበረው ነጻ የማውጣቱንም ሆነ የመፈወሱን አገልግሎት እርሱ ብቻ ፈጽሞት ያለፈ ብቻ ሳይሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ለደቀመዛሙርቱ መከሩስ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት ሲላቸው እንመለከታለን ኢየሱስ የመጣበት ዋነኛው አጀንዳና አንገብጋቢው ጉዳይ ይሄ ነበር ታድያ የኢየሱስ ዋንኛው አጃንዳ የእኛ የአገልጋዮች ዋነኛ አጅንዳ ሆኖና እኛ ብቻ ከሚለው ወጥተን የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ልንለምን ይገባል የማቴዎስ ወንጌል 9 ፥ 35 _ 38 በዚህ ትምህርት ውስጥ ሰዎችና በዘመኑ የነበሩ የምኩራብ አለቆች ቦታ ያልሰጧቸውን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት አድርጎ ቦታ እንደሰጣቸውና እንደፈወሳቸው ተመልክተናል ዝርዝር ሃሳቡ በቪዲዮ ስለቀረበ የተለቀቀውን ቪዲዮ ይመልከቱ ለዚህም ነው እንግዲህ መጽሐፍቅዱሳችን ሁላችን እንሞታለን በምድርም ላይ እንደፈሰሰና እንደማይመለስ ውሃ ነን እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድም ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል ሲል የነገረን 2ኛ ሳሙኤል 14 ፥ 14 ኢየሱስ የናዝሬቱ ሰው ለተባልን ለማንኛችንም ሰዎች ሁሉ የሚሆን ቦታ ስላለው በእኛ በሰዎች ነገር give up ( ጊቭ አፕ ) አያደርግም ከዚህ የተነሳ የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል እንደገናም አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ የሆነና ለሚጠሩትም ባለጸጋ ስለሆነ በሰዎች መካከል ልዩነት አያደርግም ሮሜ 10 ፥ 12 ስለዚህ እኛም በክብር ጌታ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን እምነት ለሰው ፊት በማድላት መያዝ የለብንም የያዕቆብ መልዕክት ምዕራፍ 2 ፥ 1 _ 7 የእስራኤል ነቢይ ሙሴም እንደተናገረው በፍርድም አድልዎ ባለማድረግ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት ሳንፈራ ፣ ታላቁን እንደምንሰማ ታናሹንም እንዲሁ ልንሰማ ይገባል ይለናል ዘዳግም 1 ፥ 17 ፣ ቆላስያስ 3 ፥ 25 በመጨረሻም ልለው የምፈልገው መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ሕይወቱን ስለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣል ስለሚል ዮሐንስ ወንጌል 10 ፥ 11 ሕይወቱን ለመከራና ለሞት አሳልፎ የሰጠን ኢየሱስ ዛሬም ከእኛ ጋራ ነው እርሱ ለዓለምና ለዘላለም የመራናል የመልዕክቱ ፍሬ ሃሳብ እንግዲህ ይህንን ይመስላል ተባረኩ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Friday 18 August 2017

ወቅታዊና አስፈላጊ የጊዜው መልዕክት





የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ




የስድባችንን ፍርድ የሚፈርድልን ክፋቱንም በራሱ ላይ የሚመልስልን ስላለ በሰነፎች በባለጌዎችና በተሳዳቢዎች የምትበሳጩ የምትናደዱ አትበሳጩ አትናደዱ ( 1 ሳሙኤል 25 39 ሮሜ 12 19 )

Image result for nabal







ወቅታዊና አስፈላጊ የጊዜው መልዕክት















የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ





የስድባችንን ፍርድ የሚፈርድልን ክፋቱንም በራሱ ላይ የሚመልስልን ስላለ በሰነፎች በባለጌዎችና በተሳዳቢዎች 

የምትበሳጩ የምትናደዱ አትበሳጩ አትናደዱ ( 1 ሳሙኤል 25 39 ሮሜ 12 19 )


ተሰምቶ የማይጠገብ ድንቅ መዝሙር ስሙትና ተባረኩበት

ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ ዝማሬ መላዕክት ያሰማህ ዘመንህን 

እግዚአብሔር ይባርከው 








አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፤ በስንፍናውም ብዛት ይስታል ( መጽሐፈ ምሳሌ 5 23 )

ብልህ ሁሉ በእውቀት ይሠራል፤ ሰነፍ ግን ስንፍናውን ይገልጣል ( መጽሐፈ ምሳሌ 13 16 )

ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፤ ቍጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል ( መጽሐፈ ምሳሌ 14 : 29 )

ሰነፍን በስንፍናው ከመገናኘት ልጆችዋ የተነጠቁባትን ድብ መገናኘት ይሻላል ( መጽሐፈ ምሳሌ 17 : 12 )

አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት ( መጽሐፈ ምሳሌ 26 : 4 )

ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሰነፍ እንደ ስንፍናው መልስለት ( መጽሐፈ ምሳሌ 26 : 5 )

ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ውሻ ስንፍናውን የሚደግም ሰው እንዲሁ ነው ( መጽሐፈ ምሳሌ 26 : 11 )

ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም ( መጽሐፈ ምሳሌ 27 : 22

Related image

         




 የተወደዳችሁ ወገኖች ዛሬ በዚህ ሃሳብ ላይ ጥቂት የጻፍኩት ነገር አለና ተከታተሉኝ ሰነፎች ስንሆን 

ባለጌዎች እንሆናለን ባለጌዎች ስንሆን ደግሞ ተሳዳቢዎች እንሆናለን እነዚህ ነገሮች ተያያዥነት ስላላቸው 

በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ ሲገለጡ ተያይዘውና ተከታትለው ነው የሚገለጡት ስንፍናም ሆነ ባለጌነት ደግሞ 

ሰው አይመርጥም በዕድሜ ለጋ ሕጻን ወጣት ጎልማሳ በመካከለኛ የዕድሜ ክልል ያለ ሙሉ ሰው ሽማግሌ አሮጊት 

አይልም እንደገናም ሃብታም ደሃ የተማረ ያልተማረ ሥልጣን ያለው ሥልጣን የሌለው ጥቁር ቀይ ነጭ ጠይም 

መልከ መልካም መልኩ የማያምር ረጅም አጭር ቀጭን ወፍራምና የመሳሰሉትን አይልም እነደየ ሰዉ ያለማደግ 

ሕይወትና የአስተሳሰብ ዝቅጠት ልክ ከፍ ብሎ ይታያል ተጎልጉሎም ይወጣል ይገለጣል ስንፍናም ሆነ ብልግና 

ከሰዎች ሕይወት ውስጥ ሊወገድ የሚችለው ሰዎች ከላይ እንደዘረዘርኩት ሃብታም ደሃ የተማሩ ያልተማሩ 


ሥልጣን ያላቸው ሥልጣን የሌላቸው እና የመሳሰሉትን ሲሆኑ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ ሲለወጡና ከፍ ብለው 


ሲገኙ ነው መጽሐፍ እንደሚነግረን ሰዎች ማለት አስተሳሰባቸው ማለት ናቸውና ምሳሌ 23 7 አስተሳሰባቸው 


ሲለወጥ ስንፍናቸውና ብልግናቸውም ያኔ ከእነርሱ ይሄዳል በሕይወታቸውም ሆነ በአመለካከታቸው ከፍ ብለው 


ይገኛሉ በሰዎች ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ የሚያመጣው ደግሞ የተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው 


ትንቢተ ኢሳይያስ 55 6 _ 12 የሉቃስ ወንጌል 7 29 _ 35 ከዚያ ውጪ እንደተባለውና በእግዚአብሔርም ቃል 


እንደተጻፈው ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም ይላልና 


መጽሐፈ ምሳሌ 27 22 ስንፍናው በማይለቀው በሰነፍ ሰው ባሕርይ መናደድም ሆነ መበሳጨት ፍጹም ሞኝነት 


ነው ለዚህም ነው እንግዲህ አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት ሲል በዚሁ



በምሳሌ መጽሐፍ ላይ የእግዚአብሔር ቃል የነገረን ምሳሌ 26 4 ዳዊት ለናባል የነበረው ግምት የተለየ ስለነበረ 


ከባለሟሎቹ ጋር ሆኖ መንጋው በናባል እረኞች ሲጠበቅ ዳዊትና ባለሟሎቹ በቀንና በሌሊት አጥር ሆነውላቸው 


እንደነበር የእግዚአብሔር ቃል በግልጥነት ይነግረናል የናባል የመንጋው እረኞችም ከነዳዊት ጋር በነበሩበት ጊዜ 


ሁሉ አልተበደሉም ነበር በቀርሜሎስም በተቀመጡበት ዘመን ሁሉ ከመንጋው አንዳች አልጎደለባቸውም ነበር 


ነገር ግን ዳዊት ለናባል ያለው ይሄ ሁሉ ግምት የተበላሸው ናባል ያለውን ነገር ለዳዊት አላካፍልም ሲል 


የእምቢተኝነት አቋም በመያዙ ሳይሆን ከዚያ መልስ መጽሐፍ እንደሚነግረን እነሆ ዳዊት በምድረ በዳ ሳለ 


ጌታችንን ሊባርኩ መልዕክተኞችን ላከ እርሱ ግን ሰደባቸው ይለናል አያይዞም መጽሐፉ እነዚህ ሰዎች ግን በእኛ 


ዘንድ እጅግ መልካም ነበሩ አልበደሉንምም አለን 1 ሳሙኤል 25 በሙሉ ያንብቡት እንደገናም ቊጥር 14 _ 


17 የተጻፈውን ይመልከቱ ታድያ እጅግ መልካም ለነበሩና የስድብ ቃል ለማይገባቸው ለእነዚህ የተባረኩ ሰዎች 


የሀገር ሀብታም የሆነው አጅሬው ናባል ተራ የሆነ የስድብ ቃል ከአፉ አውጥቶ በመሳደብ ዳዊትን አሳዘነ 


የተወደዳችሁ ወገኖቼ መጽሐፉ ለምሳሌነትና እንድንማርበትም የባለጸጋውን ሰው የናባልን ቅሌት ይጠቁመን 


እንጂ ዛሬም በዘመናችን ናባልን የመሰሉ በሀብትና በባለጸግነት ብዛት በመንፈሳዊ የአገልግሎት ሥልጣንና 


ስምም ጭምር ተሸፍነው አንቱ የተባሉ ሰዎች ስማቸውም ሆነ ተግባራቸው እንዲሁም የሚያሳዩትና የሚያሰሙት 


ነገር በሙሉ ተዳምሮ ካሉበት ሁኔታ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ዛሬም ድረስ ባለጌ ናባሎች በከተማችንም ሆነ 


ባዓለማችን እንዲሁም በቤተክርስቲያን መድረክ ሳይቀር ያሉ ሁሉ ብዙዎች ናቸው ዳዊትን ያስቆጣውና ለበቀልም 


ያነሳሳው ነገር አንድና አንድ እንግዲህ ይሄ ነው የጠበቀው ቀርቶ ያልጠበቀውን መልስ ከናባል አንደበት ሰማ 


ዛሬም ታድያ በዓለማችንም ሆነ በምድራችን እንዲሁም በቤተክርስቲያን በሥልጣንና በገንዘብ በክብር በተሸፈነ 


ማንነት ውስጥ ሆነው ጤነኛና አዋቂ ከመሰሉ በሳሎችም ነን ሲሉ ራሳቸውን ካቀረቡ ናባሎች ዛሬም እንደዳዊት 


የጠበቅነው ቀርቶ ያልጠበቅነውን አሳፋሪ ነገር እንሰማለን እንደገናም ጆሮአችንን ሳይቀር እስኪሰቀጥጠን 


የሰማውንም ጆሮአችንን እስኪከብደውና የሰማው ጆሮዬ ነው ወይስ ሌላ ብለን እስክንጠራጠር ድረስ በጣም 


አሳፋሪ የሆነን ነገር ሰምተናል አይተናል ለወደፊቱም በብዙ እንሰማለን እናያለን ብዙ ናባሎች ከነብልግናቸውና 


ከነስድባቸውም ጭምር ከዚህም ሌላ ከሥልጣናቸውና ከሃብታቸው ከገንዘባቸውም ጋር አይነኬ ሆነው 


ተቀምጠዋል ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ ናባልን ሰውየው ግን ባለጌ ነበረ ግብሩም ክፉ ነበረ እንዳለው 


እነዚህም ሰዎች ሃብትና ንብረት ሥልጣንም ጭምር እላያቸው ላይ ያለ ቢሆንም እንኳ እንደዚሁ እንደናባል 


የፋነኑ ሆነው በመገኘታቸው ክፉ ነገር ከሰው ሳይሆን ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር እንዲመጣባቸው የተቆረጠ 


በመሆኑ ማንም ሊናገራቸው የማይችል ምናምንቴዎች ባለጌዎችና ክፉዎች ናቸው መጽሐፍቅዱስ 2 ነገሥት 


ምዕራፍ 5 1 ላይ ስለ ሶርያው ንጉሥ ስለ ንዕማን ሲናገር የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማን እግዚአብሔር 


በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል ነበረ ነገር ግን 


ለምጻም ነበረ ይለናል ታድያ የንዕማንን ይሄን የመሰለ የታላቅነት የክቡርነት የጀግንነት ጽናትና ኃያልነት 


ያጠፋው በላዩ ላይ እየታየ ያለው ለምጻምነት ነው መጽሐፍቅዱስ አሁንም ንዕማንን ለምጻም ነበረ ይለናል ታድያ 


ንዕማን ይህንን በላዩ ላይ የተጣበቀውን ጸያፉን ለምጽ አውቆ ነው ነቢዩ ኤልሳዕን ፍለጋ ዮርዳኖስ ድረስ 


የወረደው ወርዶም አልቀረ ለነቢዩ ቃል ታዞና እሺ ብሎ ወደ ወንዙ ውስጥ በገባ ጊዜ ገላው እንደ ሕጻን ልጅ ገላ 


ሆኖና ተመልሶ ተፈወሰ 2 ነገሥት ምዕራፍ 5 በሙሉ ይመልከቱ ይሄ ፈውስ ታድያ በንዕማን ሳያበቃ ዛሬም ላይ 


በሥልጣን በገንዘብና በክብር ተሸፍነን አንቱ ለተባልን ስንገለጥ ደግሞ ከስንፍናችን ጋር ናባሎች ሆነንና ፈጠን 


ለተገኘን ሁሉ የማያዳግም ፈውስ ሆኖ በሕይወታችን እንዲመጣ የሁልጊዘም ጸሎቴ ነው ባለሥልጣኑ ንዕማን 


ገንዘቡ ሳያኮራው ሥልጣኑም ልቡን ሳይደፍነው ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ እንደሄደና ከነቢዩ አፍ በወጣው ቃል ታዞ 


ብቅ ትልቅ በማለት እንደተፈወሰ ሁሉ እኛም በሥልጣንና በገንዘብ የተሸፈነውን ማንነታችንን እና ሰዎችም 


የማያውቁትን እኛነታችንን ይዘን ሰዎች እኔን የበተክርስቲያን መሪና መጋቢ ሐዋርያና ነቢይ ሽማግሌና 


የመሣሠሉትን ይሉኛል የሚለውን በይሉኝታ የተያዘ የማዕረግ ከበሬታና እንዲሁም የኑሮ ከፍታ ሁሉ ወደ ጐን 


በማድረግ ከዮርዳኖስ ውሃ በሚበልጠውና ውጪያዊ ለምጽን ብቻ ሳይሆን የውስጥን ለምጽ ጭምር በሚያነጻው 


በክርስቶስ ደም ለመታጠብ ራሳችንን ብንሰጥ መጥተንም በክርስቶስ ደም ብንታጠብ ከዚህ ሁሉ ችግር 


እንላቀቃለን እግዚአብሔርን የሚያከብረው ነገር ገንዘባችን ሥልጣናችንና የአገልግሎት ስማችን ስመ ጥር 


የሆነውም እኛነታችንና አንቱታችን ሳይሆን የተፈወሰው ሕይወታችን ነው ይህ የተፈወሰው ሕይወታችን ደግሞ 


ለእግዚአብሔር ክብር የሚውል ብቻ ሳይሆን ለሰዎች ጥቅምም የሚሆን ነው ከዚያ ውጪ ግን በሕይወት ፈውስ 


እግዚአብሔር እንደ ንዕማን ሳይገናኘን እንዲሁ ከሀብታችንና ከስልጣናችን እንዲሁም ከተሰጠን የአገልግሎት 


ስማችን ጋር ተጎዝጉዘንና ተነስንሰን አንቱ ብቻ ተብለንም የምንከርም ከሆነ ግን አንድ ቀን የናባል ዕጣ ፈንታ 


የእኛም ይሆናል እንደገናም በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የምያስፈራ ነውና ዕብራውያን 10 26 _ 31 


እኛም እንደ ናባል ከእግዚአብሔር በሆነው በድንገተኛው ሞት ልንወሰድ እንችላለን 1 ሳሙኤል 25 38  


መዝሙር 72 ( 73 ) በሙሉ ምሳሌ 29 1 ምሳሌ 28 13 1 ዮሐንስ 1 5 _ 10 እግዚአብሔር ከዚህ ዓይነቱ 


አስከፊ ሞት ይጠብቀን ለንስሐም ሕይወት ያብቃን
Related imageImage result for 2 king 5





ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

God bless u all





yonasasfaw8@gmail.com