Thursday 1 March 2018

በአንገታችን ላይ ስለምናስረው ማህተብ ታሪካዊ አመጣጥ ፣ ድንግል ማርያም ጌታ እየሱስ ክርስቶስን የወለደችው በሥጋ ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ በተለቀቀው ትምህርት በብዙ እንደ ተባረካችሁ እናምናለን:: ከትምህርቱ እንደተገነዘባችሁት ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ ነው የወለደችው አንጂ በመለኮቱ አልወለደችውም :: አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ ወለደችው የምንል ከሆነ በሥጋ የመጣበትን ዓላማ ፣ ሰው የሆነበትንም ምስጢር ፣ እኛን የሰው ዘር የሆነውን ሁላችንንም ያዳነበትን እውነት በብዙ የምንዘነጋ ስለምንሆን ትልቅ ስሕተት ውስጥ እንወድቃለን :: መጽሐፍቅዱሳችንም ሲናገር እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን ነው የሚለን ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 ን እንመልከት :: ስለዚህ ከአባቶቻችን በሥጋ የመጣው ክርስቶስ ፣ ከድንግል ማርያምም በሥጋ የተወለደው ክርስቶስ ፣ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው :: እንደገናም ድንግል ኢየሱስን ልትወልድ መልአኩ ሲያበስራት መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ነው ያላት የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 35 :: ታድያ ይሄ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም ሲወለድ የተወለደው በሥጋ ነው :: ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔርን ልጅ የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮት አይደለም :: ከዚህም ባሻገር ክርስቶስ የእኛን የማዳን ሥራ ሲያከናውን ኃጢአታችንን የተሸከመው በሥጋው ነው :: ሐዋርያው ጴጥሮስ በምዕራፍ 2 ቊጥር 24 ላይ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ይለናል :: ከዚህ ምንባብ ተነስተን እንግዲህ ድንግል ማርያም አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ አትወልደውም አምላክን የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮቱ ግን አይደለም ብለን ባንናገር ጴጥሮስ የተናገረውና ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋው የፈጸመው ይሄ ሁሉ እውነት የሚቀርብን ስለሚሆን : —— 1ኛ ) ክርስቶስ የመጣበትን የማዳን ዓላማ በብዙ እንስታለን 2ኛ ) ክርስቶስ በሥጋው የፈጸመልንን ይህንን እውነት ስለምንስት መዳናችን ሳይቀር አጠራጣሪ ይሆን ነበር :: ነገር ግን እኛ ከዚህ በተለየ መልኩ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በሥጋ ነው የተወለደው ብለን ስላመንን ለማዳን የመጣበትን ዓላማ አልሳትንም :: በክርስቶስ የሆነልንና የተፈጸመው ፣ እኛም አምነንበት በተቀበልነው የመዳናችን እውነት እርግጠኞች ነን ከዚህ የተነሳም ኢየሱስ አዳኝ ማርያምንም የኢየሱስ እናት መሆኗን እንናገራለን የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 ፣ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 3 ን ይመልክቱ :: አባቶቻችንም በዚህ ጉዳይ የመጽሐፍቅዱሱን ቃል በመከተል በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይና በሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸው ሳይቀር ይህንኑ እውነት ተናገሩ ትምህርቱን በዚሁ ቪዲዮ የለቀቅነው በመሆኑ ሁሉንም አሁን ማብራራት አልችልምና የተለቀቀውን ትምህርት ስሙ :: በጥቂቱ ዋናውን ሃሳብ መጥቀስ ቢያስፈልግ ግን በዚሁ በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ አንድምታ ላይ ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብዕሲ ወአድሃነነ የሚለውን ሊተረጉሙልን ፈቀደ ብሎ ነበርና ወዶም አልቀረ ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ :: ተወልዶም አዳነን :: << በሥጋ አለ በመለኮቱ አትወልደውምና አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብዕቱ እንዲል >> ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጽ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተወለደ ያጠይቃልና :: ልደት ቀዳማዊ ተአውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል :: ዳግመኛ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ ዕሩቅ ብዕሲ ባሉት ነበርና :: ሶበሰ ተወልደ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተኃዘብዎ ወእምረሰይዎ ሐሰተ ሲሉ ገልጸውታል :: በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ቅዱስ ሳዊርያኖስ ኤጲስቆጶስ ዘሀገረ ገብሎን እንዲህ ሲል ያስተማረውን እንጠቅሳለን በማለት ተናገሩ :: በማይመረመር ልደት በተወለደው በአካላዊ ቃል እናምናለን :: ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር ቀዳማዊ ደኃራዊ እርሱ ነው :: ዳግመኛ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በምድር ላይ ከቅድስት ድንግል ማርያም እርሱ በሥጋ ተወለደ :: በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል :: ይኸውም እግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ተናገረ ( ሃይማኖተ አበው ገጽ 105 ቊጥር 2 እና 3 ይመልከቱ ) :: ታድያ ከዚህ ከሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንዳየነው ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ማርያም ባይወለድ ኖሮ በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል ተብሎ አይጻፍልንም ነበር :: እኛም ከዳግማዊው አዳም በዳግመኛ ልደት አንወለድም ነበር :: ሃሳቡ ይህን ይመስላል ወገኖች ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com
የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ በተለቀቀው ትምህርት በብዙ እንደ ተባረካችሁ እናምናለን:: ከትምህርቱ እንደተገነዘባችሁት ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ ነው የወለደችው አንጂ በመለኮቱ አልወለደችውም :: አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ ወለደችው የምንል ከሆነ በሥጋ የመጣበትን ዓላማ ፣ ሰው የሆነበትንም ምስጢር ፣ እኛን የሰው ዘር የሆነውን ሁላችንንም ያዳነበትን እውነት በብዙ የምንዘነጋ ስለምንሆን ትልቅ ስሕተት ውስጥ እንወድቃለን :: መጽሐፍቅዱሳችንም ሲናገር እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን ነው የሚለን ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 ን እንመልከት :: ስለዚህ ከአባቶቻችን በሥጋ የመጣው ክርስቶስ ፣ ከድንግል ማርያምም በሥጋ የተወለደው ክርስቶስ ፣ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው :: እንደገናም ድንግል ኢየሱስን ልትወልድ መልአኩ ሲያበስራት መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ነው ያላት የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 35 :: ታድያ ይሄ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም ሲወለድ የተወለደው በሥጋ ነው :: ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔርን ልጅ የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮት አይደለም :: ከዚህም ባሻገር ክርስቶስ የእኛን የማዳን ሥራ ሲያከናውን ኃጢአታችንን የተሸከመው በሥጋው ነው :: ሐዋርያው ጴጥሮስ በምዕራፍ 2 ቊጥር 24 ላይ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ይለናል :: ከዚህ ምንባብ ተነስተን እንግዲህ ድንግል ማርያም አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ አትወልደውም አምላክን የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮቱ ግን አይደለም ብለን ባንናገር ጴጥሮስ የተናገረውና ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋው የፈጸመው ይሄ ሁሉ እውነት የሚቀርብን ስለሚሆን : —— 1ኛ ) ክርስቶስ የመጣበትን የማዳን ዓላማ በብዙ እንስታለን 2ኛ ) ክርስቶስ በሥጋው የፈጸመልንን ይህንን እውነት ስለምንስት መዳናችን ሳይቀር አጠራጣሪ ይሆን ነበር :: ነገር ግን እኛ ከዚህ በተለየ መልኩ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በሥጋ ነው የተወለደው ብለን ስላመንን ለማዳን የመጣበትን ዓላማ አልሳትንም :: በክርስቶስ የሆነልንና የተፈጸመው ፣ እኛም አምነንበት በተቀበልነው የመዳናችን እውነት እርግጠኞች ነን ከዚህ የተነሳም ኢየሱስ አዳኝ ማርያምንም የኢየሱስ እናት መሆኗን እንናገራለን የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 ፣ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 3 ን ይመልክቱ :: አባቶቻችንም በዚህ ጉዳይ የመጽሐፍቅዱሱን ቃል በመከተል በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይና በሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸው ሳይቀር ይህንኑ እውነት ተናገሩ ትምህርቱን በዚሁ ቪዲዮ የለቀቅነው በመሆኑ ሁሉንም አሁን ማብራራት አልችልምና የተለቀቀውን ትምህርት ስሙ :: በጥቂቱ ዋናውን ሃሳብ መጥቀስ ቢያስፈልግ ግን በዚሁ በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ አንድምታ ላይ ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብዕሲ ወአድሃነነ የሚለውን ሊተረጉሙልን ፈቀደ ብሎ ነበርና ወዶም አልቀረ ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ :: ተወልዶም አዳነን :: << በሥጋ አለ በመለኮቱ አትወልደውምና አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብዕቱ እንዲል >> ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጽ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተወለደ ያጠይቃልና :: ልደት ቀዳማዊ ተአውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል :: ዳግመኛ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ ዕሩቅ ብዕሲ ባሉት ነበርና :: ሶበሰ ተወልደ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተኃዘብዎ ወእምረሰይዎ ሐሰተ ሲሉ ገልጸውታል :: በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ቅዱስ ሳዊርያኖስ ኤጲስቆጶስ ዘሀገረ ገብሎን እንዲህ ሲል ያስተማረውን እንጠቅሳለን በማለት ተናገሩ :: በማይመረመር ልደት በተወለደው በአካላዊ ቃል እናምናለን :: ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር ቀዳማዊ ደኃራዊ እርሱ ነው :: ዳግመኛ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በምድር ላይ ከቅድስት ድንግል ማርያም እርሱ በሥጋ ተወለደ :: በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል :: ይኸውም እግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ተናገረ ( ሃይማኖተ አበው ገጽ 105 ቊጥር 2 እና 3 ይመልከቱ ) :: ታድያ ከዚህ ከሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንዳየነው ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ማርያም ባይወለድ ኖሮ በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል ተብሎ አይጻፍልንም ነበር :: እኛም ከዳግማዊው አዳም በዳግመኛ ልደት አንወለድም ነበር :: ሃሳቡ ይህን ይመስላል ወገኖች ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com


No comments:

Post a Comment