Friday 9 March 2018

የጥምቀት ትምህርት የክፍል ሁለት ውይይት የጥምቀት ትምህርት የክፍል ሁለት ውይይት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን የጥምቀት ትምህርትን በክፍል ሁለት የውይይት ጊዜያችን አጠቃለነዋል በአጭሩ ትምህርቱን ለማስጨበጥ ያህል ጥቂት ማለት እፈልጋለሁ ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ዛሬ ላይ ለጥምቀት የተሳሳተ ትርጉም ሰጥታ ፣ በጥምቀት ዳግም መወለድና የጸጋ ልጅነት ይገኛል ስትል የጸጋ ልጅነትን ለማሰጠት ሕጻናትን ሳይቀር ማጥመቅ አስፈላጊ ነው ብላ በ አርባ ቀንና በ ሰማንያ ቀን የተወለዱ ሕጻናትን ብታጠምቅም ከዚህ በፊት በነበረው እምነትዋ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ የምትፈጸም ጥምቀት አንዲት ናት አንድ ጊዜ ከተፈጸመች ማለት ከተሰጠች በኋላ አትደገምም በካህን በኤጲስቆጶስ እጅ የምትፈጸመው ጥምቀት አንዲት ናት << ሊቀ ጳጳስ ወይም ጳጳስ ወይም ኤጲስቆጶስ ሳይመጣ አናጠምቅም አይበሉ ፤ የማጥመቅ ሥልጣን ያለው ያጥምቅ እንጂ የጥምቀት ሥልጣን አንዲት ናትና >> ተብሎ በሕገ ቀኖና ታዞአልና በማለት አስተምራለች ( አንቀጽ ሣልስ ፣ ቊጥር 29 ን ) ይመልከቱ ይህንን ማለትዋ እምነትዋ ከሐዋርያት እምነት ጋር ሲያያዝ የመጣ በመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 4 ፥ 4 እና 5 ላይ የጥምቀትን አንዲት መሆንዋን ጥቅሶ ያስተማረውን ትምህርት አብነት አድርጋ ነው ይህ ብቻ አይደለም ሠለስቱ ምዕት በደነገጉት ጸሎተ ሃይማኖት በተሰኘው የእምነት መግለጫዋ ላይም ወነአምን በአሃቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ስትል ተናግራለች ከእነዚህ እውነቶች የተነሳ ታድያ አማናዊትዋ ማለትም እውነተኛዋ ጥምቀት አንዲትና የማትደገም መሆንዋ የታወቀ መሆኑን ለሁሉም ሰው ለማስገንዘብ እንወዳለን ይህ እንግዲህ የቤተክርስቲያኒቱ መልካም ጐንዋና አስተምህሮዋ በመሆኑ በዚህ ቀጥተኛና ትክክለኛ አቋዋምዋም እኛ ልጆችዋ ቤተክርስቲያኒቱን ልናመሰግናት እንወዳለን ይህ ብቻ አይደለም በአንቀጽ ሣልስ ቊጥር 27 በሕገ ቀኖና በፍትሕ መንፈሳዊ በተባለው መጽሐፍዋ ላይ ወተጠምቆትነሰ በማይ ውእቱ ተሳትፎትነ በሞተ ክርስቶስ ወእርገትነሂ እምነ ማይ ውእቱ ካዕበ አምሣለ ተንሲኦትነ ምስሌሁ በማለት ተናግራለች ወደ አማርኛው ስተረጉመው በውሃ መጠመቃችን በክርስቶስ ሞት አንድ መሆናችን ከውሃ መውጣታችን ሁለተኛ ከእርሱ ጋር የመነሳታችን ምሳሌ ተብሎ በሕገ ቀኖና ወይም በፍትሕ መንፈሳዊ ተደንጓል ማለት ሲሆን እንዲህ ስትል ከዚህ በፊት በነበረው እምነትዋና መረዳትዋ በመጽሐፍዋ ላይ ጽፋ ፣ ተናግራና አስተምራ አሁን ላይ ምን ነክቶአት ሕጻናት በተወለዱ በ አርባና በ ሰማንያ ቀን ተጠምቀው መንፈሳዊ ልጅነትን ያገኛሉ ስትል እስካሁን እስከ እኛ ዘመን ድረስ እንዳመነችና እንዳስተማረች ለእኔም ሆነ ለማናችንም ግልጥ አይደለም አደራረጉንም በተመለከተ መጽሐፍቅዱሳዊ ባለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አይደግፈውም ከዚህ የተነሳ በቅድምና የመረዳት እውነትዋም ሆነ በቃሉ እውነት መሠረት ተሃድሶ አድርጋ ወደ መጀመርያ እምነትዋና የማጥመቅ ሥርዓቷ ትመለስ እላለሁ ለምን ስንል ጥምቀት የጸጋ ልጅነትን ማግኛና ዳግም መወለጃ ሳይሆን እርስዋ በቀደመው ትምህርትዋ እንደገለጸችው ጥምቀት በክርስቶስ ሞትና መነሳት ለመተባበር የምናደርገው የእምነት ሥርዓት ነው ከዚህም ባሻገር አምኖ የዳነውን ሰው ለማጥመቅ ሥርዓተ ጥምቀቱ እንዴት መፈጸም እንዳለበት በሮሜ 6 ፥ 3 _ 5 የተጠቀሰውን መነሻ አድርጋ እንደገናም በሕገ ቀኖና በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀስ ሳልስ ሕገ ቀኖና ዘሰባልዮስ 107 ን በመጥቀስ ተጠማቂውን ሰው በሚያጠልቅና በታቆረ ውሃ ውሃ መጠመቅ እንዳለበት አጥማቂው ካህንም ተጠማቂውን በውሃ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያደረገ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ሊያጠምቀው እንደሚገባ ተጠማቂው በውሃ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ መጠመቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ሞትን ሽሮ የመነሳቱ ምሳሌ ነው ስትል ጽፋልናለች ደግሞም አስተምራለች የእኛም ጥያቄ ታድያ ይሄ መጽሐፍቅዱሳዊ የሆነው እውነት ይውጣና ቤተክርስቲያኒቱ ወደ መጀመርያው የእምነት መሠረትዋ ትመለስ ነው የምንለው ወድ ወገኖቼ ሆይ በትምህርቱ ላይ በሰፊው የተወያየንበት ስለሆነ ለተጨማሪ መረጃ በቪዲዮ የተለቀቀውን ተከታታዩን ትምህርት ስሙ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com


No comments:

Post a Comment