Monday 5 March 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 3 ) ክፍል አራት የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን :: ቤተክርስቲያናችን ከአዳኟ ከኢየሱስ ተለይታ ቁልቁለቱን መንገድ የመረጠችበትን የቊጥር 3 ሃሳብ እንመለከታለን :: የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የዚቅ መጽሐፍ ገጽ 174 ላይ << ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ አማን ተወልደት ………………. ማርያም >> አለን :: ወደ አማርኛው ስተረጉመው << ነቢያትንና ጻድቃንን ትዋጅ ዘንድ ………….. ማርያም በእውነት ተወለደች>> የሚል ትርጉም የሚሰጠን ነው :: መጽሐፍ ቅዱስ ግን እስመ ኩሎሙ አበሱ ወጌገዩ ወሐደጉ ስብሐተ እግዚአብሔር በማለት ይናገራል :: ወደ አማርኛው ስተረጉመው ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል ሮሜ 3 ፥ 23 ን እንመልከት:: ታድያ ድንግል ማርያምም የሰው ዘር ሆና ለዮሴፍ የታጨች በመሆንዋ የአዳም በደል በእርሱዋም አለና ከዚህ በደል ነጻ ናት ልንል አንችልም :: የአዳም በደል ስንል ደግሞ ጥንተ አብሶ ማለታችን እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ይገባል የሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 22 _ 32 እንመልከት:: ከዚህ አውነት የተነሳ ድንግል ማርያምም የኢየሱስን መድኃኒትነት ተቀብላ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሃሴት ታደርጋለች ያለች በመሆንዋ የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 47 ለበደለው ዓለምና በኃጢአቱም ምክንያት ሞት ለተፈረደበት ዓለም አዳኙ ኢየሱስ ብቻ ነው:: አዳኝነቱም እንዴት እንደሆነ ሐዋርያው ሊገልጽልን ነገር ግን በክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸጸድቃሉ አለን ::( ሮሜ 3 ፥ 24 ) ሐዋርያው ጴጥሮስ ደግሞ በክቡር በክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ በማለት የተዋጀንበትን እውነት ነገረን ( 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 19 ) የተዋጀ ሰው ማለት ደግሞ በዋጋ የተገዛ ማለት ነውና ለራሱ አይደለም ( 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 20 ) ከእነዚህ የመጽሐፍቅዱስ እውነቶች አኳያ እንግዲህ ራስዋ ሳትቀር በክርስቶስ ደም የተዋጀችውን ድንግል ማርያምን ነቢያትንና ጻድቃንን ትዋጅ ዘንድ …….. ማርያም በእውነት ተወለደች ማለቱ ፍጹም መሳሳትና የመጽሐፍቅዱሱንም መሠረታዊ እውነት መካድ ይሆንብናልና ከዚህ ዓይነቱ ስሕተት ፈጥነን ልንመለስ ይገባል እላለሁኝ ሙሉውን ሃሳብ ለመከታተል በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ስሙት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com


No comments:

Post a Comment