Friday 1 September 2017

ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አምስት ቊጥር 2 ) ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው ( ክፍል አስራ አምስት ቊጥር 2 ) የተወደዳችሁ ወገኖችና የእግዚአብሔር ሕዝቦች ኢየሱስ የሰው ልጅ የሆነበትን ተከታታይና ቀጣይ ትምህርት በሰዓቱ በዚሁ የፌስቡክ ላይቭ እየገባችሁ ስለተከታተላችሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ በማለት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ በመቀጠልም ወደ ዛሬው ትምህርት ሳልፍ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበትን መሠረታዊ ምክንያት ተናግሯል አንዱና ዋነኛው ምክንያትም በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ፥ 10 ላይ በተጻፈው ሃሳብ መሠረት በግዕዙ ቃል እንዲህ ይላል ወይቤሎ ኢየሱስ ዮምሰ ሕይወት ኮነ ለዝንቱ ቤት እስመ አንተሂ ወልደ አብርሃም አንተ እስመ መጽአ ወልደ እጓለ እመሕያው ይኅሥሥ ወያድኅን ዘተሐጉለ ወደ አማርኛው ስተረጉመው ኢየሱስም እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና በማለት ይነግረናል ስለዚህ ኢየሱስ የጠፋነውን የፈለገንና ያዳነን በሰውነቱም ጭምር በመሆኑ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአል ተባለ እንደገናም ኢየሱስ የሰው ልጅ በመሆኑ በሰውነቱም የተሰቃየ ነበረ በማርቆስ ወንጌል 8 ፥ 31 ላይ የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር ይለናል ከዚህም ሌላ የሰው ልጅ እንደተጻፈለት እንደሚሄድ ተናግሯል በማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 24 እና 25 ላይ የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈ ይሄዳል ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አለ አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም መልሶ መምህር ሆይ እኔ እሆንን ? አለ አንተ አልህ አለው ይለናል ሌላው የሰው ልጅ የሚለው ታይትል በሰውነት ውስጥ ያለውን የሐሴት ሕግ የሚያመለክተን ነው በማቴዎስ ወንጌል 25 ፥ 31 _ 33 ላይ የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላዕክቱ ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ እረኛም በጐቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ እርስ በእርሳቸው ይለያቸዋል በጐችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል ይለናል የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ የሰው ልጅ የሚለውን ታይትል በመያዙ መሲሃኒክ ስያሜ ( ማሳያ )ነው It is a messianic designation የሰው ልጅ የሚለው ታይትል መሲሁን የሚያሳይ ነው ትንቢተ ዳንኤል 7 ፥ 13 እና 14 ከዚህ ሃሳብ እንደምንረዳው ኢየሱስ ክርስቶስ በሥልጣኑና በበላይነት ግዛቱም የሰው ልጅ ነው የሰው ልጅ የሚለው ታይትሉ ዋና አጉልቶ የሚያሳየው የእርሱን የበላይነት ፣ ግዛቱን ፣ ሥልጣኑን ሲሆን እንደገናም እርስ በእርሱ የተጋጨና የተጻረረ የሚመስለው ያ ክብር የሚገኘው በመስቀሉ ሥር ባለ ትሕትና ነው ይህንንም በመስቀሉ ሥር ያለን ትሕትና ኢየሱስ ራሱን ባዶ በማድረግና ራሱን በማዋረድ ለሞትም ይኸውም ለመስቀል ሞት ሳይቀር የታዘዘ ሆኖ ገልጾታል በዚህም ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ይለናል ፊልጵስዩስ 2 ፥ 1 _ 11 ታድያ እኛም ክርስቲያኖች ማለትም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአካሉ ብልትና አባላት የሆንን በሙሉ በዚህ ትሕትና ውስጥ ስንመጣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሆነው ሥልጣንና የበላይነት መግዛቱም ሳይቀር ይገለጥብናል በዚሁ በትንቢተ ዳንኤል 7 ፥ 13 እና 14 መሠረት ታይትሉ ወይም ርዕሱ የሚያጐላው ፣ በጣምም የሚያሳስበውና የሚያጋንነው እርሱ ሰው እንደሆነ ነው The title Emphasizes that He was Human ኢየሱስ የሰው ልጅ የተባለውን ታይትል ሲጠቀም አቅርቦ ሊያሳየን የፈለገው እውነት እርሱ ሙሉ ለሙሉ ሰው መሆኑን ነው ከዚህም ሌላ የእርሱን የበላይነት ፣ ግዛቱ ማለቅያ የሌለው ፣ የማያልፍና የዘላለም ግዛት ነው መንግሥቱም አንድና የማይጠፋ መንግሥት ነው His dominion is an everlasting dominion that will not pass away and his kingdom is one that will never be destroyed ትንቢተ ዳንኤል 2 ፥ 36 _ 45 ፣ መዝሙር ( 103 ) ፥ 19 ፣ የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 33 ስለዚህ ኢየሱስ የሰጠን አንዱ መንግሥት በክብሩና በመንግሥቱ የበላይ ነው ከዚህም ሌላ ሊቀካህናቱ ኢየሱስ መሲህ ለመሆኑ ባቀረበው የሙከራና የመፈተኛ ጥያቄ ይህንን ምላሽ ኢየሱስ በትንቢታዊ ቃል አስተላለፈ የማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 63 እና 64 ን ይመልከቱ በመሆኑም በዚህ የቃል ምላሽ መሠረት የሃይማኖት መምህሩ የተቆጣውና ልብሱንም እስከመቅደድ ድረስ ደርሶ ክርስቶስንም የከሰሰው ኢየሱስን የእግዚአብሔርን ስም በክፉ በማንሳት ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር የእኩልነት ሥልጣን መብት ጠይቋል በማለት ነው ታድያ ይህ ሊቀ ካህን ብቻ ሳይሆን እርሱን የመሠሉ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራኑም ጭምር ኢየሱስን የዛ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው ብለው ስለሚያስቡ ግምታቸው ከዚህ የዘለለ አልነበረም የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 1 _ 6 ፣ የዮሐንስ ወንጌል 5 ፥ 1 _ 18 ፣ የዮሐንስ ወንጌል 8 ፥ 48 _ 59 ውድ ወገኖቼ ትምህርቱ በእነዚህ ሃሳቦች የተጠቀለለ ነው ቪዲዮውንም ደግማችሁ ስሙት ትባረኩበታላችሁ በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment