Thursday 14 September 2017

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ( ክፍል አስራ ስድስት ) ቊጥር ፩ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ( ክፍል አስራ ስድስት ) ቊጥር ፩ የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በክፍል አስራ ስድስት ትምህርት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በተከታታይ ከዚህ ክፍል ጀምሮ የምንማማረው ጉዳይ ይሆናል የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ነውና የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የእግዚአብሔር ባሕርይ ዓይነት መሆን ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ባሕርይ አለኝ ማለት እግዚአብሔርን በመሆኑ ለአይሁድ መሪዎች ስድብ ነው ስለሆነም የኢየሱስን ሞት ጠየቀ ይህንንም ለመረዳት የማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 65 እና 66 ን ከዘሌዋውያን 24 ፥ 15 ጋር ተያይዞ የቀረበውን ሃሳብ መመልከቱ በቂ ግንዛቤን እንድናገኝ ያደርገናል ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔር አብ የባሕርዩ ምሳሌና የክብሩ መንጸባረቅ ነው ዕብራውያን 1 ፥ 3 እንደገናም የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ስለሆነ ኢየሱስ የተገለጠ እግዚአብሔር ነው ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 1 ፣ 14 ) ትምህርቱ እንግዲህ ይህ ብቻ አይደለም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን የሚገልጹ ብዙ የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች ተጠቅሰው ተብራርተውበታል ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ

No comments:

Post a Comment