Saturday 30 September 2017

መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉበት ምስጢር ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፩መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉበት ምስጢር ( ክፍል አስራ ስምንት ) ቊጥር ፩ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ አሁን በማቀርበው ትምህርት መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉበትን እውነት እንመለከታለንና ተከታተሉ መላዕክት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸው ታስቦአል ተመዛዝኖአል ዘፍጥረት 6 ፥ 2 ፣ ዘፍጥረት 6 ፥ 4 ፣ ኢዮብ 1 ፥ 6 ፤ 2 ፥ 1 እና ኢዮብ 38 ፥ 7 ፣ ዳንኤል 3 ፥ 25 ፣ መዝሙር 29 ፥ 1 ፣ መዝሙር 89 ፥ 7 ን ይመልከቱ የኢዮብ መጽሐፍ እንደሚያመለክተን መላዕክት በእግዚአብሔር የተፈጠሩ እንኳ ቢሆኑ የተገኙት ከዘላለም በፊት ነው ኢዮብ 1 ፥ 6 ፤ ኢዮብ 38 ፥ 7 እንደገናም ሰይጣን ዲያብሎስ ከእነርሱ ጋር ነበር ይህ ማለት ግን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለን የምናስበው አይደለም ሌላው የምንመለከተው በ King James Bible ( ኪንግ ጀምስ ባይብል ) በዘፍጥረት መጽሐፍ ምዕራፍ 6 ብዙ ሕዝቦች ሴቶችን አገቡ ልጆችን ወለዱ ( አፈሩ ) ማለትም ጃይንት የሆኑ ልጆችን አፈሩ ኃያል ጠንካራ የሆኑ ወንዶችን ዝነኞች የሆኑ ወንዶችን አፈሩ ይለናል መደበኛው መጽሐፍቅዱሳችንም በቃሉ እንዲህ ይላል እንዲህም ሆነ ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ እግዚአብሔርም ፦ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም እርሱ ሥጋ ነውና ዘመኖቹ መቶ ሃያ ዓመት ይሆናሉ አለ ይለናል ዘፍጥረት 6 ፥ 1 _ 3 እንመልከት ታድያ ይህ ዓረፍተ ነገር መላዕክትን አያመለክትም ማለትም ትክክለኛ የሆኑትን ቅዱሳን መላዕክትንም ይሁን ትክክለኛ ያልሆኑትን የሚያመለክት አይደለም ይህንንም ስናረጋግጥ መንፈስ የሆኑ መላዕክትና የሰው የሆኑ ሴቶች ልጆች ተጋብተው ዘር ማፍራት አይችሉም በሐዲስ ኪዳን መላዕክት ማግባትም ሆነ መጋባት እንደማይችሉ የእግዚአብሔር ቃል በግልጽ ይናገራል የማቴዎስ ወንጌል 22 ፥ 29 እና 30 መጋባት የሚችሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆች ናቸው ዘፍጥረት 1 ፥ 28 ፤ ዘፍጥረት 2 ፥ 18 ፣ 21 _ 24 ፤ ዘፍጥረት 3 ፥ 15 እና 16 ን ይመልከቱ ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ የሚለውን በዘፍጥረት 6 ፥ 1 _ 3 የተጻፈውን ቃል የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት መላዕክት ናቸው ብለን በመደምደም የሰውን ሴቶች ልጆች ያገቡት እነዚሁ የእግዚአብሔር ልጆች መላዕክት ናቸው ስንል ባልተገባ መልኩ ቃሉን ልንተረጒምና ለቃሉም ፍቺ ልንሰጥ መጽሐፉንም በዚህ መልኩ ልናብራራ አይገባም እንደገናም እውነተኛ ወንዶችና ሴቶች ልጆች የሚሆኑት ሰዎች ናቸው እንዴት ? ስንል ኃጢአታቸውን ሲናዘዙና ኢየሱስን ብቸኛ የሕይወታቸው አዳኝና ጌታ አድርገው ሲቀበሉ ፣ በመንፈስቅዱስም ሲጠመቁ ነው በአብዛኛው መጽሐፍቅዱስ የሚያስተላልፍልን የተለወጡ ሰዎች የእግዚአብሔር የቤተሰብ ክፍል መሆናቸውን ነው ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 12 ፤ ሮሜ 8 ፥ 12 _ 19 ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 18 ፤ ገላትያ 4 ፥ 4 _ 6 ፤ 1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 3 ፥ 1 እና 2 ፤ ኤፌሶን 2 ፥ 19 እውነተኞቹም መላዕክት የሚያስገነዝቡን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን ነው እነርሱ ከመጀመርያ ከመነሻቸው ሲፈጠሩ አንድ ዓይነትና ወጥ የሆነ መንፈሳዊነት ነው ያላቸው ፍጥረታቸውም መሠረት ያለው ነው ሰዎች ግን በሌላ መልኩ ከሥጋ ነው የተወለዱት ስለሆነም በመላዕክቱና በሰዎች መካከል የሥነ አፈጣጠር ልዩነት አለ ሰዎች በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠሩ ሲሆኑ ዘፍጥረት 1 ፥ 26 _ 28 ስለ መላእክትም፦ መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ ይላል ወደ ዕብራውያንየተላከ ምዕራፍ 1 ቊጥር 7 ከዚህም ሌላ በመካከላቸው በጣም ትልቅና የተራራቀ ክሂሎት ነው ያለው ይሁን እንጂ በጌታ ወንጌል የተለወጡ ቅዱሳን ሰዎች በእርግጠኝነት ለወደፊቱ ከሞት በሚነሡ ጊዜ የፈራጅነት ሃላፊነት ይሰጣቸዋል 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 2 እና 3 የዛሬው የትምህርት ፍሬ ሃሳብ ይህ ነው ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይከታተሉ በመጨረሻም ልገልጽ የምፈልገው በኮኔክሽን ችግር ምክንያት ቪዲዮው ለሁለተኛ ጊዜ ቀጥሎ ቀርቦላችኋል ስለሆነም ተከፋፍሎ የቀረበ እንኳ ቢሆንም ትምህርቱ አንድ ወጥና ተከታታይነት ያለው በመሆኑ የተለቀቁትን ሁለቱንም ቪዲዮዎች አድምጡአቸው ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment