Tuesday 12 September 2017

ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለተኛው አዳም ነው ( ክፍል አስራ አምስት ቊጥር 5 ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለተኛው አዳም ነው ( ክፍል አስራ አምስት ቊጥር 5 ) ሰላም ለእናንተ ይሁን ወገኖች በዚህ ትምህርት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ የአዳም ልጅ የተባለበትን እውነት እንመለከታለን 1ኛ ) የሰው ልጅ ትርጉሙ የአዳም ልጅ ማለት ነው በዘፍጥረት 1 ፥ 26 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ እንደሆነ ሁሉ በሂብሩ የትርጉም አፈታት ወይም አነጋገር ደግሞ የአዳም ልጅ ነው ምንጩ ያልተደባለቀውንና ዋነኛውን ለአዳም የተሰጠውን ተስፋ የወረስነው በአዲስ ፍጥረትነት ባለ የበላይነት ግዛት ነው ምክንያቱም አዳም በኃጢአት ስለወደቀ በካሳ ወይም በቅጣት መልክ የሚከፈል የሕይወት ክፍያ ነበር ከዚህ በመቀጠል ይህንን እውነት የሚጠቁሙ ጥቅሶች እንደሚከተለው አስቀምጣለሁ ፦ ( ሮሜ 5 ፥ 12 _ 21 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፥ 45 ፤ ዕብራውያን 2 ፥ 6 _ 9 ፤ መዝሙር 8 ፥ 4 _ 6 እንመልከት ) 2ኛ ) የሰው ልጅ ማለት በአማካኝ ምን እንደሆነ ትምህርቱ ይጠቁመናል ( ዘኁልቊ 23 ፥ 19 ፤ ኢዮብ 25 ፥ 6 ፤ ኢዮብ 35 ፥ 8 ፤ መዝሙር 8 ፥ 4 ፤ መዝሙር 79 ( 80 ) ፥ 17 ፤ መዝሙር 144 ፥ 3 ) 3ኛ ) ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔራዊ መልክና መጠን ሲኖር ሳለ በምድር ላይ ራሱንና የኑሮ ደረጃውን የገለጠባቸው መንገዶች ምክንያታዊ መሆናቸው የማቴዎስ ወንጌል 8 ፥ 20 ፤ የሉቃስ ወንጌል 9 ፥ 58 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 11 ፥ 19 ፤ የሉቃስ ወንጌል 7 ፥ 34 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 16 ፥ 13 ፣ 15 ፤ የሉቃስ ወንጌል 6 ፥ 22 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 9 ፥ 35 የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ትምህርቶቹ በእነዚህ ሃሳቦች ዙርያ የተጠቃለሉ ናቸው ተከታተሉት አጥኑት ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment