Tuesday 26 September 2017

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበት ምስጢር ( ክፍል አስራ ሰባት ) አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበት ምስጢር ( ክፍል አስራ ሰባት ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዛሬው ዕለት የምንማማረው አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን ምስጢር ነው ኢየሱስ ክርስቶስ የአባት የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን ከድንግል ማርያም በመወለዱ ምክንያት ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ተባለ በ2ኛ ዮሐንስ መልዕክት ቊጥር 3 ን እና በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቊጥር 35 የተጻፈውን የእግዚአብሔር ቃል እንመልከት በሉቃስ ወንጌል 20 ፥ 36 ላይ ደግሞ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል በምን ምክንያት እኛ የእግዚአብሔር ልጆች ሆንን ስንል ደግሞ ትልቊ የእግዚአብሔር ልጅ ያሰኘን የትንሣኤ ልጆች ስለሆንን ነው ከዚህ በመቀጠል ግን አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን እውነት እንመለከታለን አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው በምን ዓይነት መንገድ ነው ? ስንል አዳምን ስናየው በግልጽነት የእግዚአብሔር ልጅ አይደለም አዳም በምድር ላይ አባት እና እናት አልነበረውም ነገር ግን በእግዚአብሔር ተፈጥሮአል ስለዚህ አዳም በመመሣሠል ላይ የተመሠረተ ልጅነት አለው ወይ ? ስንል መልሱ ፦ በመጀመርያው ሴንቸሪ የልጅ ሃሳብ ክርስቲያኖች በጻፉት መሠረት ከዛሬው የተለየ ነው በአንድ ወቅት በነበረው ክንዋኔ ወይንም ድርጊት ልጅ ሲተረጎም ከእግዚአብሔር የመጣ እና በእርሱ መልክ የተፈጠረ ማለት ነው ዘፍጥረት 1 ፥ 26 እና 27 ን ይመልከቱ ሌላኛው ተጨማሪ መልስ ደግሞ ዘፍጥረት 5 ፥ 1 _ 3 ላይ የተጻፈ ነው ይህ የአዳም የዘር ግንድ ነው መጽሐፍም የአዳም የትውልድ መጽሐፍ ይህ ነው ይለናልና የአዳም የዘር ግንድ ነው ያልነው ከዚህ የተነሳ ነው ዘፍጥረት 5 ፥ 1 This is the book of the genealogy of Adam . In the day that God created man , he med him in the likeness of God ( English Bible Benson Commentary ) በዚያ ቀን እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ባረካቸው በፈጠራቸውም ቀን የሰው ልጅ ብሎ ጠራቸው አዳም 130 ዓመት ኖረ በእርሱ አምሳል የተፈጠረ የእርሱ ልጅ እየሆነ ሄደ ይለናል በዚሁ በዘፍጥረት 5 ፥ 1 _ 32 መሠረት እንግዲህ አዳም የዘር ግንድ አባት ወይም መሪ ዓይነት ነው Ge 5:1-32. Genealogy of the Patriarchs ይህ ማለት አዳም የሰው ዘር መጀመርያ ወይም የሰው ዘር ማለትም የሕዝብ መጀመርያ ነው ማለታችን ነው ሌላው በዘፍጥረት 11 ፥ 4 ላይ የተጠቀሰውን ሃሳብ በማገናዘብ ይኸው ቃል የትውልድ መጽሐፍን የሚያመለክት ነው book of the generations—(See Ge 11:4). Adam:- used here either as the name of the first man or the human race generally ( English Bible Benson Commentary ) በዘፍጥረት 5 ፥ 2 ላይ ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው ይለናል ለሁለቱም አንድ ዓይነት ስም ነው የሰጣቸው አንደኛው በስነ ፍጥረት ሲሆን ከዚያ በኋላ ደግሞ በጋብቻ ነው Genesis 5:2. He called their name Adam — He gave this name both to the man and the woman. Being at first one by nature, and afterward one by marriage, it was fit they should both have the same name in token of their union.( English Bible Benson Commentary ) By giving them both one name he notes the inseparable conjunction of Man and Wife . ሌላኛው ትርጉም ደግሞ በዘፍጥረት 5 ፥ 2 መሠረት ስማቸውን በፈጠረበት አዳም ብሎ ጠራቸው ማለት ሰው ብሎ ጠራቸው ማለት ነው እግዚአብሔር የሰጣቸው ስም ሰው ወይንም የሰው ልጅ የሚል ነው ይህ የትውልድ መጽሐፍ መቅዘፍያው ወይንም መሽከርከርያው አዳም ነው ዘፍጥረት 5 ፥ 1 መቅዘፍያ ወይንም መሽከርከርያን በተመለከተ ዘፍጥረት 2 ፥ 4 ን ከዘፍጥረት 5 ፥ 1 ጋራ በንጽጽር መመልከቱ ጠቃሚነት አለው የትውልድ መጽሐፉ በተጠናቀቀ ሁኔታ የተሠራው የነበረውና የተገኘው ከአንድ ይዞታ ወይንም ከብዙ ነው ለምሳሌ ዘዳግም 24 ፥ 1 ፣ 3 የፍቺ ደረሰኝን ያሳያል ይህ ነገር ታድያ የፍቺ ደረሰኝን አሰጣጥ ጉዳይን የሚመለከት ቢሆንም የአንድ ቤተሰብን የመሠረት ሁኔታና የመነሻ ሃሳብንም ጭምር የሚያመለክት ነው The heading in Genesis 5:1 runs thus: "This is the book (sepher) of the generations (tholedoth) of Adam." On tholedoth, see Genesis 2:4. Sepher is a writing complete in itself, whether it consist of one sheet or several, as for instance the "bill of divorcement" in Deuteronomy 24:1, Deuteronomy 24:3. The addition of the clause, "in the day that God created man," etc., is analogous to Genesis 2:4; the creation being mentioned again as the starting point, because all the development and history of humanity was rooted there (English Bible Benson Commentary ) ሌላው በዘፍጥረት 5 ፥ 2 መሠረት ስማቸውን በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው ማለት አዳም ከእግዚአብሔር የወጣ ነው እንደገናም ስሙ በእግዚአብሔር የወጣለት ነው እርሱ ቀዳሚና መጀመርያም ነው ሔዋን የመጣችው ከእርሱ በኋላ ነው ጋብቻውም የመጣው ከእርሱና ለእርሱ ነው ዘፍጥረት 2 ፥ 18 _ 25 ስለዚህ ሔዋንም በጋብቻ አንድ የምትሆነው ከእርሱ ከአዳም ጋር ነው ይህ ማለት አዳም የሚለው ስም Man and Wife ሲሆን ይህ ስም የተሰጠው በፍቅር አንድ ለመሆንና ለመገናኘት ነው ይህ ስም የተገኘው ወይም የተወረሰው ከአረብ ቃል ነው Signifying " to Join "መገናኘት ማለት ተካፋይ መሆን ማለት ነው ውድ ወገኖቼ አሁንም በዘፍጥረት 1 ፥ 26 እና 27 የተጻፈውን ሃሳብ መሠረት አድርገን ስናብራራ በአንድ ወቅት በነበረው ክንዋኔ አዳም ከእግዚአብሔር የመጣና በእርሱ መልክ የተፈጠረ ሆኖ በቀላሉ ሲተረጎም ልጅ የሚለውን ስያሜ ያሰጠው ቢሆንም በግሪኩ ትርጉም ግን ልጅ ብሎ አልተጠቀመም ሁሉም የዘር ግንድ የሚሄደው ወደ ተመሠረተበት ነውና በዚያን ጊዜ ልጅ የሚለው ቃል በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ቊጥር 23 ላይ ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው 30 ዓመት ያህል ነበር ሕዝቡ እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ ስለሚለን ቃሉ ኢየሱስ በትክክለኛ የዘር ግንድ ወይንም በትውልድ መጽሐፍ የተቆጠረ የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን ለምናልባቱ ማለትም በአይሁድ ልማድ ያለወንድ ዘር ጸንሳ የተገኘች አመንዝራ ተብላ ትወገራለችና ማርያምን ከአይሁድ የድንጋይ መወገር ለመጠበቅ ሲባል የዮሴፍ ልጅ ነው ተባለ ኢየሱስ ግን ያለወንድ ዘር ከመንፈስቅዱስ የተጸነሰ በመሆኑ በሥጋ ከድንግል ማርያም የተወለደ ቢሆንም የዮሴፍ ልጅ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው ድንግል ማርያምንም መልአኩ መልዕክትን ይዞላት ሲመጣ የተናገረው መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል የሚል በመሆኑ ድንግል ማርያም የወለደችልን የዮሴፍን ልጅ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ ነው አይሁድ ግን በልማዳቸው መሠረት ሕዝቡ እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ ተብሎም በቃሉ ስለተጻፈ እስከ ዛሬ ድረስ ሞትን ድል ነስቶና ሥራችንን ሁሉ ሰርቶ በአብ ቀኝ የተቀመጠልንን የናዝሬቱ ኢየሱስን የዚያ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው ይሉታል እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናቸውን ያብራላቸው የማርቆስ ወንጌል 6 ፥ 1 _ 6 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 27 ፥ 62 _ 66 ፤ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28 የኢየሱስን መነሣትና የመነሳቱንም ውጤት የሚናገር በመሆኑ ምዕራፉን በሙሉ አንብቡት በመሆኑም ኢየሱስ ለምናልባቱ የዮሴፍ ልጅ ነው የተባለ እንኳ ቢሆንም በሉቃስ ወንጌል 3 ፥ 22 ላይ በተጻፈው የእግዚአብሔር ሃሳብ መሠረት ግን መንፈስቅዱስ በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ እግዚአብሔር አብ ደግሞ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽ ከሰማይ አምጥቷል ክብር ለእርሱ ለአምላካችን ይሁንለት ከዚህ የተነሣ በሉቃስ ወንጌል 3 ፥ 23 _ 28 ያለው የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ግንድ የሚያልቀው በኢየሱስ ነው የሚጀምረው በአዳም የእግዚአብሔር ልጅነት ነው ኢየሱስ ለእኛ ራሱን ሲያረጋግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ትርጉሙም በቀላሉ እርሱ ጻድቅ እንደነበረ በእርሱ ያመኑና ጻድቃን የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከአዳም ፍጥረት ጀምሮ ያሉት ናቸው አለበለዚያ ሉቃስ አዳም የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ አያረጋግጥልንም ነበር ሕጉም ዳዊት የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብሎ አያረጋግጥልንም ነበር ኢየሱስ የተወደደና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ አስደሳች ልጅ እንደ መሆኑ መጠን በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ የዳነው ፣ የእግዚአብሔር ልጅም የሆነው አዳምና የአዳም ዘር በሙሉ እንዲሁ እንዲሆን ይፈለጋል እንደገናም የሉቃስ የዘር ግንድ አሁንም በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ ስለዳነው ስለ አዳምና ስለ ዘሩ ሲናገር በመለኮታዊ የመፍጠር መፍለቅያ ሃሳብ የሚመራው ወደ ኢየሱስ ነው የሉቃስ ወንጌል 3 ፥ 38 ጌታ እግዚአብሔር የምናነበውን ይህንን ቃል ይባርክልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment