Friday 7 July 2017

የሥዕል መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት በእናት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ዘጠኝየሥዕል መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት በእናት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ዘጠኝ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በማለት የከበረ ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ በመቀጠልም በክፍል ዘጠኝ ትምህርታችን ላይ ከላይ በተመለከታችሁት አርዕስት በቪዲዮ የተላለፈ ትምህርት አዘጋጅቼ ለቅቄያለሁ የትምህርቱን ጭብጥ ሃሳብ በአጭሩ ለማስቀመጥ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥዕልን በተመለከተ ሦስት ዓይነት መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ታቀርባለች እነርሱም ፦ 1ኛ ) ቅዱሳት ሥዕላት 2ኛ ) ርኩሳን ሥዕላት ( ጣዖታት ) 3ኛ ) ዓለማውያን ሥዕላት የተወደዳችሁ ወገኖች በሦስት ደረጃ ተከፍለውና ተመድበው የተቀመጡትን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ሰጥታ ያስቀመጠቻቸውን ትምህርቱ በጥልቀት በመዳሰስና ትክክለኛ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ የትምህርት እውነታን በማስያዝ ለሕዝባችን ተገቢውን ምላሽ ያቀርባል ለዛሬ የተመለከትናቸው ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ መጽሐፍቅዱሳችን ትክክለኛ ትርጉም ሰጥቶ ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው ስለዚህ ስግደት ፣ አምልኮ ፣ ውዳሴ ይገባቸዋልና ሥለን ልናመልካቸው ፣ ልናስመልካቸው ይገባል ብለን ስንጠይቅ መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ለዚህ የሚሰጠን መልስ የለም ቅዱሳት ሥዕላትን ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው ስንል የጠራናቸው እኛ እንጂ መጽሐፍቅዱሳችን አይደለም በሙሴ አማካኝነት በታቦቱም ላይ ሆነ በመጋረጃው ላይ የተሠሩት ኪሩብ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት እንዲሰራው የተደረጉ ኪሩቦች ናቸው እነዚህን ኪሩብ በመስራት ታድያ የታዘዘው ሙሴ እንጂ እኛ አይደለንም እንደገናም ሙሴን እግዚአብሔር ሲያዘው ማደርያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም ነው ያለው ዘጸአት 26 ፥ 30 በመሆኑም ሙሴ እግዚአብሔር ያላሳየውን አላቆመም የእግዚአብሔር ነቢይ ሙሴ ይህንንም ያደረገው በዓላማ ነው በሰማይ የነበረው የእግዚአብሔር አምልኮ በምድርም እንዲቀጥል እግዚአብሔር ስለፈቀደ በሙሴ አማካኝነት ይህንን አደረገ ምስጢሩ እንግዲህ ይሄ ነው ርኩሳን ሥዕላት የተባሉትም በተለያዩ መልኮች የሚሳሉ ሆነው የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚቃወሙና የሚሳሉ በተቃራኒው ደግሞ የሰይጣንን ክፉ ተግባራት የሚያወድሱት በሙሉ ናቸው በዚህ ዘመንም የጣኦት አምላኪዎች የሚጠቀሙባቸው ሥዕሎች የአምልኮ ምልክቶችና ጽሑፎች ወዘተርፈ ከዚህ ይመደባሉ ይሉናል ኦርቶዶክሳውያኑ የሥዕል ስነ አፈታት ባለቤቶች አያይዘውም በመጽሐፍቅዱስ ከሚገኙ ርኩሳን ሥዕሎች መካከል ፦ 1ኛ ) እስራኤላውያን በጥጃና በተለያዩ እንስሳት ምስል ሰርተው ያመልኳቸው የነበሩት ዘጸአት 32 ፥ 1 _ 10 2ኛ ) በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ንጉሡ አቁሞት የነበረው ከወርቅ የተሠራ ምስል ትንቢተ ዳንኤል 3 ፥ 1 _ ፍጻሜ 3ኛ ) ከነአናውያን ያመልኳት የነበረችው አስታሮት የተባለችው የሴት ምስል ወዘተ የመሣሠሉት ርኩሳን ሥዕላት ተብለው ይጠራሉ ሲሉ አሁንም ኦርቶዶክሳውያኑ መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ይሰጣሉ መሣፍንት 2 ፥ 13 ፤ መሣፍንት 3 ፥ 7 ፤ መሣፍንት 10 ፥ 6 እና የመሣሠሉትን ብዙ የብዙ ብዙ ጥቅሶች መመልከት እንችላለን ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ ርኩሳን ሥዕላት ፣ ርኩሳን ሥዕላት ተብለው ለመጠራታቸው የማጠናከርያ ጥቅሶች ናቸው ሲሉ እነዚህን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች በአስረጂነት ያቀርቧቸዋል ዘዳግም 7 ፥ 25 ፤ 1ኛ ነገሥት 12 ፥ 28 _ 30 ፤ ትንቢተ ዳንኤል 11 ፥ 31 ፤ 12 ፥ 11 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 15 _ 18 መመልከት ይቻላል ይሁን እንጂ ወገኖቼ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱሳት ሥዕላትና ርኩሳን ሥዕላት ሲል ለይቶ የሚጠራቸው ሥዕሎች የሉትም ለእግዚአብሔር ሁሉም ሥዕሎች አንድ ዓይነትና እኩል ናቸው ለምን ስንል በዘጸአት 20 ፥ 1_ 6 ላይ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ ተብሎ ተጽፎልናል በዘዳግም 4 ፥ 15 ጀምሮ የተጻፈውን ስንመለከት ደግሞ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ ተብሎ ነው የተጻፈልን ወደ ሐዲስኪዳን ስንመጣም እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ እግዚአብሔርን የምናመልከው በእውነትና በመንፈስ ነው የዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 23 እና 24 እንመልከት በመሆኑም ለርኩሳን ሥዕሎች የተሰጡ ጥቅሶች በሙሉ ቅዱሳን የተባሉ ሥዕሎችንም የሚመለከቱ በመሆናቸው አንዱ ከሌላው የተለየ ወይም የተሻለ የምንለው ነገር አይደለም በክፍል አስር ትምህርታችን ዓለማውያን ሥዕላት የሚለውን ተመልክተን የዚህን አርዕስት ማጠቃለያ ሃሳብ በመስጠት የክፍሉን ትምህርት በዚሁ እንቋጫለን አያይዘንም ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል እናልፋለን እስከዚያው ተባረኩ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment