Thursday 29 June 2017

የሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስምንትየሃይማኖታዊ ሥዕላት አሣሣል በጥንታዊትና ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ስምንት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ናችሁ በክፍል ስምንት ትምህርታችን የምንመለከተው የመምህራንና የሊቃውንትን አሳሳልና የሥዕሉን ትርጉም ነው ሃሳቡን እንዲህ በማለት ያስቀምጡታል መምህራንና ሊቃውንት ካባ ለብሰው ወንጌል ይዘው ይሣላሉ ይህም ክብራቸውን ለማሳየት ነው በዚህ ዓለም ዞረው ወንጌል ለማስተማራቸው ፣ መናፍቃንን ተከራክረው ስለመርታታቸው እውነተኛዋን እምነት ስለማስተማራቸው ነው ይላሉ በመሠረቱ ለሥዕል መስገድ እንደሌለና የተቀረጸ ምስልንም ማምለክ እንደማይገባን መጽሐፍቅዱሳችንን መሠረት አድርገን በተደጋጋሚ መነጋገራችን ይታወሳል ዘጸአት 20 ፥ 3 _ 6 ፤ ዘዳግም 4 ፥ 15 ፤ ዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 24 ን እንመልከት ይሁን እንጂ ከዚህ ከማብራርያው ሃሳብ በመነሳት ሰዎች በሞያቸው ምክንያት ካባ ፣ ቀሚስ ፈርጅያ ፣ ጃኖ ፣ ጥንግ ድርብ በወንጌላውያንም አብያተክርስቲያናት ደረጃ ሱፍ ክራቫትና የመሳሰሉትን ቢያደርጉ የለበሱት የማዕረግ ልብስ ከወዴት እንደሆኑ የሚያሳይ ባሕላዊ አለባበስንም የሚጠቁም በመሆኑ ያን ያህል ችግር የሚያመጣ ነው ብዬ አላስብም ሰዎችም ከአንድ የትምህርት ተቋም ተምረው ሲጨርሱ የመመረቅያ ገዋን ይለብሳሉ ይህ ለሰዎቹ የሞያቸውን ምንነትና ማንነት የሚያሳይ በመሆኑ የሚያስመሰግንና እጅግም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው ነገር ግን ልብሱ እንዲህ ሊሆን ሲገባው ትርጉሙን ቀይሮና በምትኩ ሌላ ትርጉም ይዞ ሲመጣ ግን እጅግ ይከብዳል ይህንንም በትረካው እንደተመለከትነው መምህራንና ሊቃውንት ካባ ለብሰው ወንጌል ይዘው ይሳላሉ ይህም ክብራቸውን ለማሳየት ነው የሚለው አባባል ፍጹም ከወንጌል እውነት የወጣና ስሕተት የሆነ ነገር ነው ካባ ፣ ቀሚስ ፣ ፈርጅያ ፣ ጃኖም ሆነ ሱቶችንና ክራቫቶችን ለክብራችን የምንለብስ ከሆነ የጌታ አገልጋዮችና ወንጌል ሰባኪዎች መሆናችን ቀርቶ በሉቃስ ወንጌል 20 ፥ 45 _ 47 በተጻፈው ቃል መሠረት ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ በገበያም ሰላምታ በምኩራብም የከበሬታ ወንበር በምሳም የከበሬታ ሥፍራ ከሚወዱ ጻፎች ተጠበቁ ይለናልና እኛም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እየሆንን ስለሆነ በዚህ በእኛም ዘመን ሰዎች ከእኛም ሊጠበቁ ይገባል እያልናቸው መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይሁን እንጂ በዚህ ጉዳይ ኢየሱስም ሆነ ሐዋርያቱ የኖሩት ኑሮ ምን እንደሚመስል ለእኛ ምሳሌ እንዲሆነንና እኛም እንድንማርበት ትምህርቱ በሰፊው ይተነትናል አያይዞም ተከራክሮ መርታትን አስመልክቶ ኦርቶዶክሳውያኑ ሊቃውንት ከአዋቂነታቸው ጋር አያይዘው ስለሆነ የሚተረጎሙት መጽሐፍቅዱሳችን እውቀትን የማይጠላና የሚያበረታታ ፣ ካህን መሆን የሚፈልግ ሰውም እውቀት ሊኖረው እንደሚገባ ቢያስተምረንም ትንቢተ ሆሴዕ 4 ፥ 6 እኔ አዋቂ ነኝ ፣ ከኔ ወዲያ ለአሳር የሚለውንና ተከራክሬም ረታለሁ ፣ አሸንፋለሁ ፣ ማን ይችለኛል ? ሲሉ ለራስ የከፍታ ሥፍራንና የሊቅነትን ቦታ ሰጥቶ ሌላውን መናፍቅ ፣ አላዊና ከሐዲ ነህ ሲሉ በድፍኑ ማንጓጠጥን ፣ ማቃለልን ግን እጅግ ጸያፍ ፣ በልግና የኃጢአትም ሥራ መሆኑን እያስገነዘበን እንደገናም የሌላውን ሳይሆን የራስን አላዋቂነትና ኋላቀርነትንም ጭምር የሚያሳይ ሽፍን አስተሳሰብ መሆኑንም ትምህርቱ ሰፊ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ ማስረጃና ማብራርያር በመስጠት ከዚህ ዓይነቱ ደካማና የተናቀ አስተሳሰብም ሆነ አመለካከት እንድንወጣ ግልጽ አድርጎ በመናገር በጉልህ ያስተምረናል ይመክረናል ለበለጠ ግንዛቤ ቪዲዮውን ተመልከቱ ጌታም በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment