Tuesday 21 March 2017

ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ወደ 

ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል 

እውነት እንድትመለስ የሚረዳ ተከታታይ 


ትምህርት 

Related image


የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ይህ  Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry  ነው ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ የሚረዳ ትምህርት  ለተከታታይ ሳምንታት ማቅረቤ ይታወሳል ለትምህርቴ እንደ መነሻ ሃሳብ አድርጌ የወሰድኩት ቤተክርስቲያኒቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅና የሰው ልጅ የሆነበትን ምስጢር አስተባብራ የያዘች ብትሆንም የእግዚአብሔር ልጅም ሆነ የሰው ልጅ የሆነበትን ምስጢር ግን ተንትናና ከአባቶችም መጽሐፍ ጋር በማያያዝ ትክክለኛ የሆነውን መጽሐፍቅዱሳዊ ማብራርያ ሰጥታ ለሕዝባችን በተገቢው መንገድ እውነቱን እንዲያውቅ ያላደረገችና ያላስያዘች ያላስጨበጠችም በመሆንዋ  የሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ከገላትያ 4 4 ጋር በማስተባበር እንደገናም ወበከመ ደክመ ከማሁ ነአምር ከመ ውእቱ አዕረፈ የሚለውን የሃይማኖተ አበው ቃል ወደ አማርኛው ሲተረጎም እንደ ደከመ እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን ይለናልና ሃይማኖተ አበው ዘሄሬኔዎስ ምዕራፍ 7 ቁጥር 23 ከዮሐንስ ወንጌል 4 6 ጋር በማያያዝ ፦……………





1ኛ ) የሰው ልጅ በመባሉ ምክንያት በሰውነቱም ጭምር የሠራው ሥራና አማላጅነቱ ( ክፍል   አንድ )

2ኛ ) የእግዚአብሔር ልጅ በመባሉ በእግዚአብሔር ልጅነቱ የሠራው ሥራ  ( ክፍል ሁለት)

3ኛ ) የሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንደ ደከመ እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለን ይለናልና በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀካህናት የለንም የሚለውን ዕብራውያን 4 15 በማያያዝ የሚያብራራ ( ክፍል ሦስት)

4ኛ ) ወባሕቱ ሑር ወአፍትን ርዕሰከ ለካህን ሄደህ ራስሕን ለካህን አሳይ


የሚሉትን ሃሳቦች መጽሐፍቅዱሳዊ ማብራርያ በመስጠት በፌስቡክ ላይቭና በዩቲውብ ጭምር ተሠራጭቶ የቀረበ በመሆኑ ትምህርቱን በድጋሜ መከታተል የምትፈልጉ ሰዎች ብትኖሩ በነዚሁ አድራሻዎችም ሆነ በጐግልና በብሎግ አድራሻዎቼም ጭምር ማግኘት የምትችሉ መሆናችሁን ለእናንተ ለወገኖቼ ማሳሰብ እወዳለሁ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው 


ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን 




ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ 

No comments:

Post a Comment