Friday 10 March 2017

የትምህርት ርዕስ ፦ የሰው ልጅ በመባሉ ምክንያት በሰውነቱም ጭምር የሠራው የማዳን ሥራና አማላጅነቱ( ክፍል አንድ )የትምህርት ርዕስ ፦ የሰው ልጅ በመባሉ ምክንያት በሰውነቱም ጭምር የሠራው ሥራና አማላጅነቱ ሃሌሉያ ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሰብሑ ወዘምሩ ሎቱ ወንግሩ ኩሎ መንክሮ ወትከብሩ በስሙ ቅዱስ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ ተቀኙለት ዘምሩለት ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ ( መዝሙር 104 ( 105 ) ፥ 1 _ 3 ) ክፍል አንድ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አባቶች ፣ እናቶች ፣ እህቶችና ወንድሞች ፣ ሊቃውንተ እግዚአብሔር መምሕራን ፣ አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናት እና ዲያቆናት ፣ ሕዝበ እግዚአብሔር ምዕመናን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በማለት በዛሬው ዕለት እንደ ጌታ ፈቃድ ለእናንተ ለወገኖቼ የሚጠቅም ተከታታይ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት አንድ ብዬ ዛሬ ጀምሬያለሁ ይህቺ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ቅድመ ዓለም ከአብ የተወለደ መጀመርያና መጨረሻ የሌለው አልፋና ኦሜጋ የሆነ ከአብ ጋር በቅድምና የነበረ ቀዳማዊ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ሲሆን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ከሴት በመወለዱ ደግሞ የለበሰው ከአዳም የተገኘ መዋቲ ወይንም ሟች የሆነውን ሥጋ ነውና የሰው ልጅም መሆኑን ጠንቅቃ የምታውቅ በመሆንዋ ሳታዛባ የሰው ልጅ የሆነበትንና የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን ምስጢር ለሰዎች ታስተምራለች በመሆኑም ስለነዚህ ስለያዘቻቸው ትላልቅ መንፈሳዊ እውነቶችና መረዳቶችዋ እግዚአብሔርን ከፍ ባለ ድምጽ እናከብራለን እናመሰግናለን ከዚህም ሌላ ይህቺ ቤተክርስቲያን ለእኛም ጭምር እናት እና አንጋፋም የሆነች ቤተክርስቲያን ስለሆነች በብዙ እንባርካታለን ለዘለዓለሙም እግዚአብሔር ይባርካት ነገር ግን ከዚህ በመቀጠል አንድ እውነት መናገር የምፈልገው ይህቺ ቤተክርስቲያን የሰው ልጅ የሆነበትንና የእግዚአብሔር ልጅ የተባለበትን ምስጢር ለሰዎች ታስተምር እንጂ የሰው ልጅ በመባሉ ምክንያት በሰውነቱ የሠራውን የማዳን ሥራውንና ከሞት ከተነሣም በኋላ ሰው ሆኖ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠ በመሆኑ አማላጅነቱም ጭምር በመጽሐፍዎችዋ ውስጥ እንደሚገባ ተዘርዝረውና ተጽፈው የተገኙ ቢሆኑም እንኳ በማመን ያልተቀበለቻቸው በመሆንዋ ዛሬ ላይ ባለ እምነትዋ ፈጽሞ የረሳችና የዘነጋች ተጽፎ የተገኘውንም እውነት ፍጹም የማታምንም ሆናለች ስለዚህ ይሄ ትምህርት ደዋል ሆኖ ሊቀሰቅሳትና ከእንቅልፏም ሊያነቃት በዚህ መልኩ በቪዲዮ ዛሬ ተዘጋጅቷል የሰው ልጅ በመባሉ ምክንያት በሰውነቱ የሠራልን ሥራ የእኔና የእናንተ ሥራ በመሆኑ ወደ አብ መንግሥት ሊያስገባን ብቃትን የሰጠን ሕይወትም የሆነልን በመሆኑ እኛም ፍጹም የምንረሳውና በቀላሉም የምንመለከተው አይደለም ከዚህ የተነሳ የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ አማላጅነቱም ጭምር ለእኛ ለአማኞች ዓመት ጠብቀን የምናከብረው ታሪካዊ ክብረ በዓላችን ወይም ጥሩ የሆነው የእንኳን አደረሳችሁ ሰላምታችን አይደለም የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ለእኛ ለምናምን ከዘላለም ሞት የዳንበት ሕይወታችን ነው ይሄ ጌታ ሞትን አሸንፎ በአብ ቀኝ የተቀመጠም በመሆኑ መቀመጡ ለፈራጅነት ሳይሆን ለአማላጅነት ነውና ዕለት ዕለት በድካማችን የሚያግዘን አማላጃችን ነው የዛሬው ትምህርት የሚያሳየን እውነት እንግዲህ ይህንን ነው ለበለጠ መረጃ ይህንን የተለቀቀውን ቪዲዮው ይከታተሉ የክፍል ሁለት ትምህርት ይቀጥላል ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment