Wednesday 8 March 2017

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅና የሰው ልጅ የሆነበትን ምስጢር የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ቅዱሳን ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን ይህ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ነው ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንድትመለስ የሚረዳ ትምህርት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሳምንት የሚቀርብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅና የሰው ልጅ የሆነበትን ምስጢር አስተባብራ የያዘችበትን እውነት የሚያብራራ ሃይማኖተ አበው ዘእልመስጦአግያ ምዕራፍ 3 ን ከገላትያ 4 ፥ 4 ጋር በማስተባበር ፣ እንደገናም ወበከመ ደክመ ከማሁ ነአምር ከመ ውእቱ አዕረፈ የሚለውን የሃይማኖተ አበው ቃል ወደ አማርኛው ሲተረጎም እንደ ደከመ እንዲሁ የደከሙትን የኃጢአት ሸክም የከበደባቸውን እንዳሳረፈ እናውቃለንና ሃይማኖተ አበው ዘሄሬኔዎስ ምዕራፍ 7 ቁጥር 23 ን ከዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 6 ጋር በማስተባበር የምንማማረው ይሆናል ትምህርቱ March 10 2017 10 : 00 In the Morning ይጀምራል ሳያመልጣች እንድትከታተሉ በጌታ ፍቅር እጋብዛለሁ ወይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment