Tuesday 28 March 2017



የምንባብ ኃይለ ቃል 






ኅዙነ ወትኲዘ ልብ……








ያዘነና የተከዘ ልብ ……..




Image result for Adam and hewan come out from heaven




ኅዙነ ወትኲዘ ልብ……









        በአብ በወልድና በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ    ስም ትምህርቴን እጀምራለሁ የተወደዳችሁ አባቶቼና እና እናቶቼ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም አባቶች ሊቃውንተ እግዚአብሔር መምህራን ሕዝበ እግዚአብሔር ምዕመናን በሙሉ በቅድሚያ በልዑል እግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ




ኅዙነ ወትኲዘ ልብ……







በጥንታዊት ሐዋርያዊት እና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ነገር ከሥሩ ውሃ ከጥሩ እንዲሉ ልብ ብለን እና አስተውለን መጻሕፍቶችዋን ከሥር ከመሠረቱ ከመረመርን ከእግዚአብሔር ቃል ጋራ የማይጋጩ የእግዚአብሔርንም ቃል መሠረት አድርገው የተነገሩ ብዙ የብዙ ብዙ የሆኑ የከበሩ እውነቶች ያሉባት ቤተክርስቲያን በመሆኗ እኛም ቤተክርስቲያናችን ብለን ስንጠራት አናፍርባትም እንደገናም በዚህች ቤተክርስቲያን እጅግ በጣም ደስ ይለናል ለምን ቢባል ይህቺ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን ለብዙ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሳይቀር በቀዳሚነት የምትጠቀስ ቀደምትና እናት የሆነች ቤተክርስቲያን ስለሆነች በብዙ እንኮራባታለን ጥያቄያችን ግን እነዚህ ሁሉ እንቊ የሆኑና ከአዕላፋት ወርቅና ብርም የሚበልጡ ሆነው በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰግስገው የእግዚአብሔርን ቃል በሚያውቁ መምህራኖችዋ ተጽፈውና ሠፍረው ያሉ የእግዚአብሔር የአፉ ሕጎች ፍንትው ብለው ወጥተው ለሕዝቡ ይነገሩ ሕዝባችንም ላሜ ቦራን ከሚመስሉ ተረቶች፣ የገድል የድርሳናትና የልዩ ልዩ ልብ ወለድ መጻሕፍት አስተምህሮቶች ሰለባ መሆኑ ቀርቶ በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ይመስረትና በእምነቱ ይራመድ ነው ይህንንም በተመለከተ እስቲ ለዛሬ ወዳዘጋጀሁላችሁ መለኮታዊ የእግዚአብሔር ሃሳብ ላምራ ውዳሴ ማርያም አንድምታ መጽሐፍ ይገርማችኋል ፣ በጣምም ትደነቃላችሁ ብዙ የከበሩ እውነቶችን ይዟል በመሠረቱ ውዳሴ ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠና የሚገባ መሆኑን ብናምንም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ግን ውዳሴ ማርያም የሚባል የጸሎት መጽሐፍ አለና አንድምታ ተዘጋጅቶለታል አንድምታ ማለት ደግሞ ትርጓሜ ወይም ትርጉም ማለት ነው በእንግሊዘኛው ኮመንታሪ ልንለው እንችላለን ታድያ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከሰኞ እስከ እስከ እሁድ በቀናት ተወስነው የተደረሱ ጽሑፎች አሉ እኛ ለዛሬ የምንመለከተው ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ( የሰኞ ውዳሴ ማርያም ) ላይ የተዘገበውን ቃል ነው ቃሉም እንዲህ ይላል ፈቀደ እግዚእ ያግዕዞ ለአዳም ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ወደ አማርኛው ስተረጉመው ያዘነ የተከዘ አዳምን ጌታ ሊያድነው ነጻ ሊያወጣው ወደደ የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል አንድምታው ወይም ትርጓሜውም እንዲህ ሲል ያብራራዋል 

Jesus in the Gardan of Gethsemane and the chief priests , the officers of the temple police,and the elders who had come for him

ኅዙነ ወትኲዘ ልብ…… ያዘነና የተከዘ ልብ ……..

Image result for jesus in the garden of gethsemane picture
Image result for Jesus died in across and resurrected


አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ወደደ ኅዙነ ልብ ትኩዘ ልብ ሲል ነው ይለናል ወገኖቼ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን የሚለው የቁጥር ጉዳይ ስለሆነ ብዙም ውዝግብ ውስጥ የሚከተን አይሆንም በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ማለቱ ደግሞ ግብርናት ማለት ባርነት ማለት ነውና በዲያብሎስ ባርነት ሥር የነበረ አዳም ማለትን የሚያመለክተን ነው ኅዙነ ልብ ትኩዘ ልብ ማለት ደግሞ ያዘነ ልብ የተከዘ ልብ ማለትን የሚያመለክት ነውና ያዘነ ልብ የተከዘ ልብ ያለው ደግሞ አዳም ብቻ ሳይሆን የአዳም ዘርን በሙሉ የሚያካትት በመሆኑ ኅዙነ ልብ ትኩዘ ልብ የሆነውን አዳምና ዘሩን በጠቅላላው ሊያድን ወደደ የሚለውን ሃሳብ ይይዝልናል የመጽሐፉ አንድምታ ሲቀጥል እንዲህ ይላል አንድም ያዘነ የተከዘ አዳምን ሊያድነው ወደደ ይልና ትርጉሙን እያያዘ እንዲህ በማለት ይናገራል አዳምን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ቤተ ፈት በዚህ ጊዜ እበላ እጠጣ ነበር ፣ በዚህ ጊዜ ተድላ ደስታ አደርግ ነበር እያለ ያዝናል እርሱ ግን አትብላ ያለኝን እፀ በለስ በልቼ ፣ ከፈጣሪዬ ትእዛዝ ወጣሁ ብሎአልና እያለ ይናገራል የቤተ ፈት ልማድ ማለት ቤተ ፈት የሚለውን ስንተረጉመው ቤቱን ፣ ኑሮውን ትዳሩን ፣ የፈታ ወይም ቤት አልባ ፣ ቤት የሌለው ፣ የትም አዳሪ የሚለውን ትርጉም ልንሰጠው እንችላለንና እንዲህ ዓይነቱ ሰው ደግሞ ተርጓሚው እንዳለው የቤተ ፈት ልማድ አለውና ምንም እንኳ ቤቱን የፈታ ቤቱም የተፈታበት ቢሆንም የቤቱን ልማድ ፣ ቤቱም ያፈራለትንና በቤቱ ያለውን የኑሮ ሁኔታ መብል መጠጡንና በጠቅላላው የቤቱን ምቾት በዚህ ጊዜና በእነዚያ ጊዜያት እያለ ማስታወሱ አይቀርም ነው የሚለን አያይዞም አዳም ግን እንደዚህ አይደለም አትብላ ያለኝን እፀ በለስ በልቼ ከፈጣሪዬ ወጣሁ ብሎ ነውና በማለት የአዳም ትካዜውና ሃዘኑ ከእግዚአብሔር በመለየቱ ምክንያት የመጣ በመሆኑ መንፈሳዊ እና ሃዘኑም ሆነ ትካዜው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን መሆኑን ይጠቁመናል መጽሐፋችንን በዚህ ጉዳይ ላይ ስንመለከት ደግሞ የዓለም ሐዘን ሞትን ያመጣል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ደግሞ ጸጸት የሌለበት ወደ መዳን የሚያደርስ ንስሐን ያደርጋል ይለናል 2ኛ ቆሮንቶስ 7 ፥ 8 _ 11 በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ፥ ቊጥር 11 _32 ላይ የጠፋው ልጅም መጥፋቱ ሲገባውና ወደ ልቡም ሲመለስ ያደረገው ነገር ይሄነኑ ነው ታድያ የጠፋው ልጅ በምሳሌነት ለእኛ ለአማኞች የተጻፈልን ስለሆነ ቤተ ፈትነቱ ለእግዚአብሔር ቤት በመሆኑ የአባቱን ቤት ክብር አይገባኝም በማለት ጠግበው የሚተርፋቸው የአባቱ ሞያተኞች ሁሉ ናቸውና ከእነርሱ እንደ አንዱ ሊሆን እንደናፈቀ ቃሉ ያስተምረናል ይህ እንግዲህ መዳንን የሚያመጣ የጤነኞች ሰዎች ሕይወትና የንስሐ ፍሬ ነው የጥንቷ ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ታድያ ይህንን እውነት አመስጥራና አራቃ በእንዲህ መልኩ አስተምራለችና ይህንን ጤናማ የሆነ እውነትዋን ከተደቀበው ጓዳዋ በማውጣት ግልጥልጥ አድርገን እና አፍረጥርጠን እኛ ልጆችዋ ለሕዝብዋ ማስተማር አለብን በመቀጠልም ወደዚሁ ወደተነሳሁበት ሃሳብ ስመጣ የውዳሴ ማርያም አንድምታ ተርጓሚው የነገሩን ውልና ፍቺ አብራርቶና ተርጉሞ ያልጨረሰ በመሆኑ አሁንም አንድም እያለ ይቀጥላልና እኛም ለዛሬ ታድያ አንድም እያልን እርሱን ተከትለን እንሂድ አንድም ጌታ ያዘነ የተከዘ ሆኖ አዳምን ነጻ ሊያወጣ ወደደ ተከዘት ነፍስየ እስከ ለሞት እንዲል ይለናል ወገኖቼ አባቶች አመስጣሪ ፣ መጽሐፍ አዋቂ ወይም ባለቅኔ መጥቶ ብሉዩን ከሐዲስ ለይቶና አስለይቶ ፣ አመስጥሮና አራቆ ፣ አደላድሎም ሲናገር ሲሰሙ ይበል እንደሚሉት እኔም ይህን ተርጓሚ ይበል ብየዋለሁ ለምን ስንል ተከዘት ነፍስየ እስከ ለሞት እንዲል ጌታ ያዘነ የተከዘ ሆኖ አዳምን ነጻ ሊያወጣው ወደደ በማለት ተርጉሞታልና ነው ተከዘት ነፍስየ እስከ ለሞት ማለት የግዕዝ ቃልና መጽሐፍቅዱሳዊ ቃል ሲሆን ትርጉሙም በማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 38 እና በማርቆስ ወንጌል 14 ፥ 34 ላይ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቆዩ ከእኔም ጋር ትጉ አላቸው የሚለውን መጽሐፍቅዱሳዊ እንድምታ የሚሰጠን ነው ውድ ወገኖቼ የዚሁ መልዕክትና የትምህርት ጽሑፍ አንባቢዎቼ በሙሉ ቊልፉ ሃሳብና የምስጢሩም ፍቺ ያለው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው ጌታችን ኢየሱስ በጌቴሴማኒ ከደቀመዛሙርቱ ተለይቶ ከዚያን ሰዓት ጀምሮ የደም ላብ እስኪያልበው ድረስ በጸሎት እንደገናም በጸዋትወ መከራው ማለትም በስቃዩ ፣ በግርፋቱ ፣ ምራቅ እየተተፋበት ፣ በጅራፍ እየተገረፈ ፣ ፊቱን ሸፍነው እየመቱትና ማነው የመታህ ? እያሉ ያሾፉበት ፣ የሾህ አክሊል ደፍተውበትና ከለሜዳ አልብሰውት ፣ በመስቀል ላይ ቸንክረውት ፣ ተጠማሁ እያለ ፣ በጦርም ወግተውት ደምና ውሃ ከጎኑ የፈሰሰው አረ ስንቱን ዘርዝሬ ልጨርሰው የጌታዬን ነገር ነፍሱ እስከ ሞት ድረስ ያዘነው የተከዘውም ኢየሱስ በእነዚህ ውስጥ ሁሉ በማለፍ ነውና ያዘነውና የተከዘው እንዲሁ ያዘነና የተከዘ አልነበረም ይልቁንም በኃጢአት መተላለፍ ምክንያት ሞት ተፈርዶበት በዲያብሎስ ባርነት ሥር ተግዞ እየተከዘና እያዘነ ያለውን የአዳም ዘር በሙሉ ማለትም ሁላችንንም ከዚህ ከከፋ ሃዘንና ትካዜ ፣ የባርነት ቀንበርና ሞት ጭምር እኛን ለማውጣት ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ተከዘ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ስለሁላችን የተከዘውና ያዘነው ፣ እንወደውም ዘንድ ደም ግባት እስኪያጣ ድረስ ደርሶ የሞተልን ኢየሱስ በዚያው ሳይቀር እኛን ስለማጽደቅ ተነስቶአል ታድያ ዛሬ የዚህ የኢየሱስ አድራሻው ያለው በሰማይ እንጂ እስከ ሞት ድረስ በተከዘበት ጌቴሴማኒ የትካዜ ስፍራ ወይም ደም ግባት ባጣበት የመስቀል ላይ ጣርና ሞት አይደለም ያለው ስለዚህ ላመንበት ለእኛ ሃዘናችንና ትካዜያችንን ለውጦታል ፣ አድራሻችንንም ቀይሮታል ዛሬ ይህ ኢየሱስ መዳናችንን ፈጽሞልን የዘላለምንም መዳን ሰጥቶን በሰማይ ነው ያለው የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ ዕብራውያን 5 ፥ 10 ን ይመልከቱ ስለዚህ ያዳነን ጌታ እና ሐገራችንንም በሰማይ ያደረገልን ጌታ እያለን ዛሬ ላይ እንደገና ወደኋላ ተመልሰን አንድ ብለን ልናዝንና ልንተክዝ አንጀምርም ያልዳንንም ሰዎች ብንኖር በዚህ ጌታ አምነን ድነንና የዘላለምም ሕይወት አግኝተን ከዚህ አግኝቶ እያሰቃየን ነው ከምንለው ትካዜና ሃዘናችን ለአንዴና ለዘለዓለሙ መላቀቅ አለብን የመዳንም ቀን አሁን ስለሆነ ለዚህ ሁኔታችን ማለትም ተይዘን ላለንበት ትካዜያችንና ሃዘናችን ቦታ ልንሰጠው አይገባም ስለዚህ ፈጥነን አሁኑኑ ወደዚህ ጌታ መምጣት ይሁንልን ነገር ግን ከዚህ ሃሳቤ ጋር አያይዤ ልገልጽላችሁ የምፈልገው አንድ እውነት የውዳሴ ማርያም ተርጓሚ ተከዘት ነፍስየ እስከለሞት ባለው ሃሳቡ ነፍሴ እስከሞት ድረስ ተከዘች ብሎአልና ያዘነ የተከዘ ሆኖ አዳምን ነጻ ሊያወጣ ወደደ ካለ ዛሬ ለምን ይሆን ሰዎች ወደ ገዳም በመግባት ዋሻ ፈልፍሎና ከሰው ተለይቶ ፣ የጣፈጠ ፣ የጣመ ምግብ ሳይበሉ ፣ ሰውነታቸውን በማክሳትና በማድረቅ ማዘን መተከዛቸው ? ለምንስ ይሆን ሰሌን ላይ መተኛታቸው ? ሰንሰለት ሳይቀር በውስጥ ሰውነታቸው ታጥቀው መተከዝ ማዘናቸው ? በቪዲዮ ምስሉን እንዳያችሁት ደብረ ዳሞ ወደተባለ አቡነ አረጋዊ ገዳም ለመሄድና እዚያ ለመድረስ ያለውን አበሳ ተመልከቱት ሕዝቡ ተራራውን ወጥቶ ገዳሙ ያለበት ለመድረስ በገመድ ተንጠላጥሎ አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦና ተጎትቶ ነው የሚደርሰው ይሄ ሁሉ ስቃይ ታድያ ለምን ይሆን ? ወገኖቼ እስቲ በዚህና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከዚህ ጽሑፍ አንጻር አንድ ስትሉ ተወያዩ ሲያስፈልግም ልትጽፉ ብዕሮቻችሁን አንሱ በዚህ ጉዳይ እስከ ሞት ድረስ ያዘነልንና የተከዘልን ጌታ እያለ ጌታ ምንም እንዳላደረገልን ቆጥረንና ከሰው ተለይተን በረሃ በመግባት ፣ የሴትን ፊቷን ላናይ ፣ ድምጽዋን ላንሰማ ፣ የሰራችውን ላንበላ ፣ ላናገባ ፣ ላንዳር ፣ ላንኳል ምለን ፣ ተገዝተን እያዘንና እየተከዝን ልንኖር በውኑ የጌታ ፈቃድ ነውን ? ይህንንስ ፍልስፍና ከየት አመጣነው ? እንደገናም በዚህ ሁኔታችንስ የጸጋውን መንፈስ ማክፋፋት ፣ የኪዳኑንም ደም መርገጥ አይሆንብንምን ? ዕብራውያን 10 ፥ 29 _ 31 መልሱንም ሆነ ውይይቱን ለእናንተ ለፌስቡክ አንባቢዎቼ የምተወው ይሆናል ቅዱሳን ወገኖች ስለዚህ ተወያዩበት ተነጋገሩበት ተማማሩበትና ሌሎችንም አስተምሩበት እላችኋለሁ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰማችሁንም ሁሉ እንደ ቃሉ እውነት ጻፉ በማለት ትምህርቴን በዚሁ አጠቃልላለሁ ተባረኩ ሰላም ሁኑ

Related image


በእርሱ ሆነው ላንቀላፉት ሁሉ ኢየሱስ 
በኩራት ሆኖ ተነስቷል 
Image result for the resurrection of jesus christ

እኛም በማመናችን ምክንያት ከእርሱ ጋር ተነስተን በሰማያዊ ሥፍራ ተቀምጠናል 

                                አሜን


ወይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ 
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ 




ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry

No comments:

Post a Comment