Monday 6 March 2017



እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ የቀረበ 

ተከታታይ ትምህርት ለተከታታይ ወራት የተሰጠ 


















የተወደዳችሁ ቅዱሳን ሰላም ለእናንተ ይሁን እግዚአብሔርን መከተል በሚል ርዕስ 1ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 15 10 እና 11 መሠረት ያደረገ ተከታታይ ትምህርት ለተከታታይ ወራት መማማራችን ይታወሳል በመሆኑም በዚህ ዋና አርዕስት ስር ከክፍል አንድ እስከ ክፍል አስራ ሰባት በሚደርሱ ተከታታይ ንዑሳን አርዕስቶች ትምህርቱ እንደሚገባ ተዘጋጅቶ በፊስቡክ አድራሻዬም ሆነ በዩቲዩብ ቀርቦአል እናንተም አብዛኞቻችሁ በተለይ በፌስቡክ ላይቭ እየተገኛችሁ ተከታትላችኋል በዩቲዩብም እንዲሁ የተከታተላችሁ ትኖራላችሁ ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል የመማር ጥማትና መልካም ትጋታችሁ ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ ልላችሁ እወዳለሁ ከዚህ በመቀጠልም በእነዚህ ንዑሳን አርዕስቶች ዙርያ ለተከታታይ ጊዜ የቀረቡትን ክፍሎች ለመከታተል እንዲያመቻችሁ እንደሚከተለው በተራ ቁጥር ለእናንተ ለወገኖቼ  ለማቅረብ እወዳለሁ 


እግዚአብሔርን መከተል በሚል ዋና አርዕስት ሥር 


1ኛ ) እግዚአብሔርን መከተል ( ክፍል አንድ )

2ኛ ) የተከተሉ የመሰሉ ነገር ግን ባለመከተል የሚያታልሉ ( ክፍል ሁለት )

3ኛ ) የሳሙኤል ሳኦልን መለየት ( ክፍል ሦስት )

4ኛ ) የሳኦል ንጉሥነት ተናቀ ( ክፍል አራት )

5ኛ ) የመጣል ሕይወት ከፊቴ ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን……………….. ( ክፍል አምስት )

6ኛ ) ለዳዊት የተገባው የተስፋ ቃልና የዳዊት በእውቀት ቃል የሆነ ልመናው ( ክፍል ስድስት )

7ኛ ) እግዚአብሔር ከንጉሥ ሰሎሞን ጋር የገባው ኪዳን ( ክፍል ሰባት )

8ኛ ) ሰሎሞን እንደ እግዚአብሔር ቃል ባልሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ( ቊጥር 1 እና ቊጥር 2 ) (ክፍል ስምንት )

9ኛ ) እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም ( ክፍል ዘጠኝ )

10ኛ ) እግዚአብሔርን ስንከተል ወይንም ከእግዚአብሔር ጋር ስንሆን ( ቊጥር 1 እና ቊጥር 2 ) ( ክፍለ አስር )

11ኛ  ) ሰዎች እግዚአብሔርን መከተል የሚተዉት መቼ ነው ( ክፍል አስራ አንድ )

12ኛ  ) ኢየሱስ የመጣው ከገዛ መንገዳችን ተመልሰን እርሱን እግዚአብሔርን እንድንከተልና የራሱም የእግዚአብሔር    እንድንሆን ነው  ( ክፍል አስራ ሁለት )

13ኛ  ) እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ ( ቊጥር 1 እና ቊጥር 2 ) ( ክፍል አስራ ሦስት )

14ኛ  ) ክርስቶስ ስለ እኛ ራሱን የሰጠበትና በፍቅር የምንመላለስበት እውነት ( ቊጥር 1 እና ቊጥር 2 ) ( ክፍል አስራ አራት )

15ኛ  ) ካሌብ በዘኊልቊ 14 8 መሠረት 1) የእግዚአብሔርን ፍቅር መሠረት አድርጎ የተናገረ ነው  ( ክፍል አስራ አምስት )

16ኛ  ) ካሌብ በዘኊልቊ 14 8 መሠረት 2 ) መወደዱ ገብቶት የተከተለ ነው  ( ክፍል አስራ ስድስት)

17ኛ ) ካሌብ በዘዳግም 1 36 መሠረት 3 ) እግዚአብሔርን ፈጽሞ የተከተለ ነው  ( ክፍል አስራ ሰባት )

18ኛ ) ካሌብ በዘኊልቊ 13 30 መሠረት በእግዚአብሔር የተማመነ ነው የሚሉ ናቸው ቅዱሳን ወገኖች በዋና አርዕስቱ ( ክፍል አስራ ስምንት )

መሠረት እነዚህን ተከታታይ የሆኑ ንዑሳን አርዕስቶች ለእናንተ ለወገኖቼ በዝርዝር ማቅረቤ በፌስቡክ ድኅረ ገጼም ሆነ በዩቲዩብ አድራሻ ገብታችሁ ለመከታተል እንዲያመቻችሁ ለመርዳት ነው በእናንተ በወገኖቼ ጸሎትና እገዛ እኔንም ጌታ ረድቶኝ እነዚህን የዘረዘርኳቸውን ትምህርቶች ለእናንተ አቅርቤያለሁ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው አሜን 


                                    ተፈጸመ



የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry 






ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ 

No comments:

Post a Comment