Friday 18 September 2020




https://scontent-yyz1-1.cdninstagram.com/v/t50.2886-16/49678356_2395772263829008_4076045340599758802_n.mp4?efg=eyJ2ZW5jb2RlX3RhZyI6InZ0c192b2RfdXJsZ2VuLjY0MC5mZWVkLmRlZmF1bHQiLCJxZV9ncm91cHMiOiJbXCJpZ193ZWJfZGVsaXZlcnlfdnRzX290ZlwiXSJ9&_nc_ht=scontent-yyz1-1.cdninstagram.com&_nc_cat=104&_nc_ohc=z8GSfQySUsYAX9O64bk&vs=18001623019104584_3577401597&_nc_vs=HBksFQAYJEdCUUk5Z0lRanI4eThZSUlBTkt2MVRha0JaRTRia1lMQUFBRhUAAsgBABUAGCRHR0E5X1FJNDVHMW5raUlIQUVZTXNkakFLOGhUYmtZTEFBQUYVAgLIAQAoABgAGwAVAAAYABa2jqToronfPxUCKAJDMywXQE4FHrhR64UYEmRhc2hfYmFzZWxpbmVfMV92MREAdeoHAA%3D%3D&_nc_rid=023715f9b8&oe=5F67AF37&oh=91ee1652a949a23a6e300022114f5866




አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሃሴት ቆመናል ደስታን ስለወለድሽ
የቀደመው እባብ እጅግ ተበሳጨ
በአሸዋ ላየ ቆመ መርዙን እየረጨ
ከልጅሽ ምስክር ሊያስቀር ከልጆችሽ
እጅጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ
ገብተሻል ላትወጪ አንዴ ከልባችን
ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን
የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ
ያየነው ባንቺ ነው የጠፋው ተገኝቶ
ወይኑን ያፈራሹ የወይን ሀረግ ድንግል
ምግብን የሰጠሽን በቀራንዮ መስቀል
ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ
የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ
የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ
ጸዋሪተ ፍሬ የሃዘናችነ መርሻ
ግቢ ከቤታችነ በረከታችን ነሽ
የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ
ከሀገረ ብንርቅ ከእለፍኝ ከጓዳችን
ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን
በአደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጂ
ለጻድቃን አይደለም ለሃጥኣን አማልጂ።

No comments:

Post a Comment