Wednesday 30 September 2020

 የአገልግሎቱ መሥራች : ----- እንኳን ደህና መጣችሁ ወደ ኦርቶዶክስ ተሃድሶ ሐዋርያዊ አገልግሎት ዌብሳይት አገልግሎቱ የተመሠረተው በአባ ዮናስ ጌታነህ ሐዋርያዊ አገልጋይ ሲሆን አባ ዮናስ ጌታነህ የዚህ የኦርቶዶክስ ተሃድሶ ሐዋርያዊ አገልግሎት መሥራችና መሪ ነው አባ ዮናስ ጌታን ማገልገል የጀመረው በኢትዮጵያ የካላንደር አቆጣጠር ከ1985 - 1996 በኢትዮጵያ ሲሆን ከዚያም ወደ ካናዳ በመምጣት ይህንኑ አገልግሎት ከ1996 - 2013 እስካሁን ድረስ በማገልገል ላይ ይገኛል ጌታ እግዚአብሔር በአባ ዮናስ ልብ ውስጥ ይህንን ይህንን ራዕይ ያስቀመጠው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባዘጋጀችው የሰዋስወ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የኛ ዓመት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ነው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በውስጡ ላለው ለእግዚአብሔር ድምጽ ታዞ ይህንን አገልግሎት በዚያው በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥ ለውስጥ በማገልገል ቆይቶ በ1990 ዓመተ ምህረት ከአምስት መነኮሳት ጋር በመሆን በአደባባይ ትልቅ የጀማ ክሩሴድ በኤግዚቢሺን ማዕከል በማዘጋጀትና በመስበክ አገልግሎቱን ይፋ አደረገ ኦርቶዶክስም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርሱንና ጓደኞች መነኰሳትን የእኛ አገልጋዮች አይደሉም በማለት ትክክለኛ ያልሆነ የውግዘት ደብዳቤ አስተላልፋ ከቤተክርስቲያኒቱ አውግዛ ለይታቸዋለች ከዚያ በኋላ ነው ይሄ አገልግሎት በካናዳ ሀገር ቀጥሎ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ የደረሰው ይህ አገልግሎት አሁንም ነጻ የሚያወታውን ብቸኛ የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ወንጌል ለመስበክና የዳኑትንም ሰዎች ተከታትሎ በማስተማር የክርስቶስ ደቀመዝሙር ለማድረግ የታመነና የተዘጋጀ ነው ይህ አገልግሎት አሁንም ነጻ የሚያወጣውን ብቸኛ የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ወንጌል የሚሰብክና የዳኑትንም ሰዎች ተከታትሎ በማስተማር የክርስቶስ ደቀመዝየሚያደርግ ነው 

No comments:

Post a Comment