Saturday 22 August 2020

ፍሬምናጦስ ማድረግ የነበረበትና ያልነበረበት


ለውይይት የቀረበ ሐሳብ

ከዚህ ቀደም ሲል ክርስትናና ኢትዮጵያ የተዋወቁት በጀንደረባው ነውን? የሚለው ሐሳብ ለውይይት የቀረበ ቢሆንም ይህ ነው ጠቃሚ ሐሳብ (አስተያየት) የሚሰጥ ሰው አልተገኘም፡፡

አሁን ደግሞ በሌላ ርዕስ ሌላ የውይይት ሐሳብ ቀርቧል፣



የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጳጳስ የሆነው ፍሬምናጦስ ለቤተ ክርስቲያንም ለሀገርም የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ነገሮችን ያደረገ መሆኑን መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን ከእነዚያ መልካም ሥራዎቹ እና አገልግሎቱ ጎን ለጎን ከዚህ በታች ለቀረቡት ሁለት ነጥቦች ትኩረት አለመስጠቱ ቤተ ክርስቲያንን ምን ያህል እንደጎዳት ሁላችን እየተመለከትነው ያለነው ነገር ነው፤

ሀ) ዲያቆናትን ሲሾም ትኩረት አድርጎ የነበረው አይሁዳውያኑ ላይ ነበር፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት ሊቀርብ የሚችለው የብሉይ ኪዳን እውቀት ያላቸው መሆናቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ‹‹እነዚህም ካህናት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአይሁድ ባህል ሥር እንዲሰድ አስተዋጽኦ አድርገዋል››፡፡ በመሆኑም ፍሬምናጦስ በሰው መረጣ ወቅት፤

1) አይሁዳውያኑ ላይ ትኩረት ከማድረግ ከኢትዮጵያውያንም ለድቁና የሚበቁ ሰዎችን አሰተምሮና አብቅቶ ቢሆን ኖሮ፣

2) አይሁዳውያኑ ምንም እንኳ በመሲሑ ለማመን ፈቃደኛ ቢሆኑም አይሁዳዊነታቸው ተጽዕኖ እንደሚያሳድርባቸው በመገመት ክርስትና ባህልን መሠረት ያላደረገና በራሱ የሚቆም መሆኑን አስተምሮ ቢሆን፤

ለ) ፍሬምናጦስ ከማረፉ በፊት ማድረግ የነበረበትን አለማድረጉ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ ጉዞ የሚተካውን ሰው የማብቃት ሥራ ያለሠራ መሆኑን ያሳያል፡፡ እሱን የሚተኩትና ከእርሱ ኅልፈት በኋላ ቤተ ክርስቲያኒቱን ባለችበት ሁኔታ ይዘው የወንጌል ሥርጭቱን የሚያስቀጥሉ ሰዎች የማብቃት ሥራ ባለመሥራቱም ምክንያት የእሱን ኅልፈት ተከትሎ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ መሪዋን (አስተዳዳሪዋን) ፍለጋ ወደ ግብፅ ቤተ ክርስቲያን ለማማተር እንደትገደድ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከግብፅ ይመጡ የነበሩት ጳጳሳት የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ከማሳደግና ወደተሻለ የወንጌል አገልግሎትና ሕይወት ከመውሰድ ይልቅ በተቃራኒው ይዘዋት የተጓዙት ፍሬምናጦስ ማድረግ የነበረበትን ባለማድረጉ ምክንያት ነው፡፡

@gedlatnadersanat

No comments:

Post a Comment