Monday 7 October 2019






ጠቃሚ ምክር


( ክፍል ሦስት )


ከሰማኋቸውና ካነበብኳቸው


የዕለት እንጐቻ



አንድ ወንድም ወደ አንድ አገልጋይ መጥቶ ብዙ ሃሳቦች ወደ ልቡናዬ መጥተው እያስቸገሩኝ ነው ብሎ ጠየቀው :: አገልጋዩም እንዲህ ሲል መከረው ::  በውስጥህ ያለውን አየር ተንፍሰህ ወደ ውጪ አውጣውና  መልሰህ አየር ወደ ውስጥ አስገብተህ ተንፍስ አለው :: ይህም ወንድም አገልጋዩ እንዳለው በውስጡ ያለውን አየር  ተንፍሶ  ወደ ውጪ አስወጣውና መልሶ አየር ወደ ውስጥ አስገብቶ ተነፈሰ:: አገልጋዩም እንደገና ይህንን ወንድም እንዲህ ሲል መከረው :: ከዚህ በኋላ አንዴ ወደ ውስጥ ያስገባኸውን አየር ተንፍሰህ ወደ ውጪ አስወጥተሃልና መልሰህ አየር ወደ ውስጥህ አታስገባ አለው :: ይህም ሰው አልችልም አለ :: አገልጋዩም ይህንን ሰው መልሶ አየህ ወደ ልቡናህ መጥተው የሚያስቸግሩህንም ሃሳቦች እንደዚህ ወደ ውስጥህ አለማስገባት ትችላለህ አለው ይባላል :: 

አንድ ዘማሪ እንዲህ ሲል ዘመረ ፦— 


አላስተናግድም በሬንም አልከፍትም 

ከኢየሱሴ ሌላ እንግዳ አልፈልግም …………………





አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ 

የሕይወትህ መውጫ ከእርሱ ነውና 

የአፍህን ጠማማነት ከአንተ አውጣ ሐሰተኞቹን ከንፈሮችም ከአንተ አርቅ 

( መጽሐፈ ምሳሌ 4 23 እና 24 )


እርሱም አለ ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ ሃሳብ ዝሙት መስረቅ መግደል ምንዝርነት መጎምጀት ክፋት ተንኮል መዳራት ምቀኝነት ስድብ ትዕቢት ስንፍና ናቸውና ይህ ክፉ ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል 

( የማርቆስ ወንጌል 7 14 - 23 )


በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ በጎነት ቢሆን ስጋናም ቢሆን እነዚህን አስቡ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል 

( ፊልጵስዩስ 4 8 እና 9 )


የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነውን ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ 

( ሮሜ 12 1 - 3 )


ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ በአዕምሮአችሁ መንፈስ ታደሱ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ 

( ኤፌሶን 4 22  - 24 )



አባ ዮናስ ጌታነህ 

No comments:

Post a Comment