Sunday 20 October 2019

የልዳው ጊዮርጊስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ተብሎ የተነገረበትን የዘመናት ተረት የሻረ አስደናቂ የክርስቶስ ወንጌል ... = የልዳው ጊዮርጊስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው ተብሎ የተነገረበትን የዘመናት ተረት የሻረ አስደናቂ የክርስቶስ ወንጌል ዛሬ ተሰበከ ክርስቶስ ራስ በሆነበት ቦታ ጊዮርጊስን ራስ ያለች ቤተክርስቲያን ይህ አልበቃ ብሏት ደግሞ የልዳው አንበሳ ሦስት ጊዜ ሞቶ ሦስት ጊዜ ተነሣ ስትል ጊዮርጊስን ቀን መድባና በዓል ሰርታ ብታከብረውም ፣ ሃይማኖተ አበው የተባለው የገዛ መጽሐፍዋ ግን ይህንን ተረት ተቃውሞ ክርስቶስ ጌታችን ከሙታንም ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ማንንም በሥጋ እንዳላስነሣ አስተውል ሲል ተናገረ ( ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 59 ፥ 49 እና 50 ) :: ይህንን እውነት ይዘን ነው እንግዲህ ከመጽሐፍቅዱስ እውነት ጋር በማገናዘብ ለእናንተ ለአድማጮች ዛሬ ይህንን መልዕክት ለማድረስ የወደድነው ስለዚህ መልዕክቱን በመስማት ተባረኩ ለሌሎችም ሼር ሸር ሼር አድርጉ ይብቃን እንግዲህ ዘመኑ የወንጌል እንጂ የተረትና የተረት አባቶች ዘመን አይደለም :: ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን አባ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment