Saturday 5 October 2019




የሰላማችን ምልክት 


ትዕምርተ ሰላምነ 


የሰላምህ ምልክት መስቀልና የመስቀል ደመራ  ከመስቀል ደመራም መልስ ሰላምን አገኛለሁ ስትል የምትቀባው አመድ አይደለም :: እሬቻም ስትል የምታከብረው በዓል  ከዛፉም ስር ወስደህ ግንባርህ ላይ የምትቀባውና የምትለቀለቀው ቅቤ አይደለም :: የሰላምህ ምልክት በእርሱ የምትታመንበትና የምትደገፍበት የመዳኛህ ግንብ የሆነው የሕይወት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ክርስቶስ ነው ::

የመጀመርያይቱ ያልተከለሰችዋና የልተበረዘችዋ ንጹሑን ወንጌል የሰበከችዋ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያናችን 


ትዕምርተ ሰላምነ ዘኪያሁ ንትአመን ዓረፍተ መድኃኒትነ በዘቦቱ ናሰምክ ዕብነ ሕይወት ርዕሰ ማዕዘንት ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል  አስተምራናለች :: 


ትርጉም በእርሱ የምንታመንበት የሰላማችን ምልክት  ፣ በእርሱ የምንደገፍበት የመዳናችን ግንብ  የሕይወት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው { መጽሐፈ ሰዓታት  ( የሰዓታት መጽሐፍ ) ገጽ 121  }


ኤፌሶን 1 : 11 - 22 ቆላስያስ 1 : 19 - 20   1ኛ ጴጥሮስ 3 : 18 - 22


የሰላማችን ምልክት ኢየሱስና ኢየሱስ ብቻ ነው 


አባ ዮናስ ጌታነህ 



No comments:

Post a Comment