Saturday 12 October 2019





ጠቃሚ ምክር


( ክፍል አራት  )


ከሰማኋቸውና ካነበብኳቸው


የዕለት እንጐቻ



« ፎከስድ የሆነ ውሃ እኮ ድንጋይ ይሰብራል  »


ከኢንጂነር ዘማሪ ግዛቸው የተወሰደ የክፍል ሁለት የምስክርነት ቃል 


ሙሉውን ሃሳብ ለማግኘት ከዚህ በታች ሊንኩን ስለማስቀምጠው ገብታችሁ መስማት ትችላላችሁ   https://youtu.be/2Or8Ruv5x9U


ውድ ወገኖቼ ሆይ የጌታ ሰላም ይብዛላች በማለት መልዕክቴን እቀጥላለሁ :: ይሄ የድሮ ዘማሪ ይህንን ሃሳብ ያነሳው ፎከስድ የሆነ አገልግሎት የሚያስገኘውን ውጤታማነት ለመግለጽ ነው :: ከዚህም የተነሳ ይሄ የተወደደ ዘማሪ ከአምስት ዓመት በፊት ፎከስድ ወይንም ዳይሬክትድ ሆኖ ለማገልገል ምኞቱን ለጌታ በጸሎት እንዺህ ሲል ገለጸ :: «ጌታ ሆይ በጌታ ውጪ እንዳለ እንደሰበቀ ጦር ፎከስድ ሆኜ እንዳገለግልህ እርዳኝ » ::  ወገኖቼ ምን ዓይነት ድንቅ ጸሎት ነው :: ይሄ ሃሳብ ነው እንግዲህ  እኔንም ውስጤን ቀስቅሶ ከወንድሜ ኢንጂነር ዘማሪ ግዛቸው ጋር የተያያዘውን መልዕክቴን  እንዲህ ስል ለእናንተ ለማቅረብ የወደድኩት ::

የልብ ንጽሕናንና ለውጥን የሚፈልጉ ሰዎች በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ቃል ወደሚያገለግል ወደ አንድ አገልጋይ ሄደው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት ይባላል :: የልብ ንጽሕናና ለውጥን ማግኘት እንፈልጋለን ስለዚህ ለዚህ ጉዳያችን ምን ማድረግ እንዳለብን ብትመክረን አሉት :: አገልጋዩም ሲመልስ  የወሃ ጠባይ ለስላሳ ነው  ፣ የድንጋይ ጠባይ ጠጣር ነው  ነገር ግን ውሃ በጠርሙስ ተደርጎ ከድንጋዩ በላይ ከተያዘና ውሃ የሚያንጠባጥብ ከሆነ ቀስ በቀስ ድንጋዩ መሰባበሩ አይቀርም  ፣ ቃለ እግዚአብሔርም ለስላሳ ነው  ፣ ልቡናችን ደግሞ ጠጣር ነው ነገር ግን ሰው የእግዚአብሔርን ቃል አዘውትሮ የሚሰማ ከሆነ ልቡናው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለፈሪሃ እግዚአብሔር ማለትም እግዚአብሔርን ለመፍራት ቦታ መስጠቱ አይቀሬ ነው አላቸው ይባላል :: ከዚህ ጋር ተያይዞ ፦————————————————

የዘማሪ መጋቢ ዳንኤል አምደ ሚካኤልን የመዝሙር ሊንክ አስቀምጫለሁ በመስማት ተባረኩ   https://youtu.be/alU0JgcK2hc 

https://youtu.be/b1yufNRFMs0


አባ ዮናስ ጌታነህ 


No comments:

Post a Comment