Friday 30 March 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 4 ) ክፍል አራት የዛሬው ትምህርታችን ማርያም መካከለኛ የሆነችበትን የኦርቶዶክስ አስተምህሮን የምናይበት ጊዜ ነው ማርያም መካከለኛ ናት የተባለችባቸውን ወደ ሦስት የሚደርሱ ነጥቦችን እንመለከታለን 1ኛ ) የክብርዋም ገናናነት በማለት ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ብለዋታል 2ኛ ) ከረግረግ መሸጋገርያ የጽድቅ መሰላል የሆንሽ ማርያም ሆይ ለምኚልን ብለዋታል 3ኛ ) እንደገናም ለማርያም መካከለኛነትንና አስታራቂነትን ሊስጡም ፈልገው ማርያም አርጋለች ስለዚህ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ አድርጋችሁ አክብርዋት ሲሉ ይገልጻሉ መጽሐፍቅዱሳችን ግን እውነተኛውና ትክክለኛው መካከለኛ ኢየሱስ ለመሆኑ መጽሐፍቅዱሳዊ አስረጂ በመስጠት ያብራራል ጥቅሶቹንም እነሆ ብለናል 1ኛ ጢሞቴዎስ 2 : 5 / ዘፍጥረት 28 : 12 / ዮሐንስ ወንጌል 1 : 52 ውድ ወገኖቼ ትምህርቱን በእንዲህ መልኩ በአክብሮት ላብራራላች ወድጃለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com

Sunday 18 March 2018

D.r Zebene Lemma Debate with Loser Pastor ክፍል 1--አቤት ዉሸት ምነዉ ፓስተር? ደግሞ ኦ...በፓስተር ዶክተር ቶሎሳ ጉዲናና በዶክተር ቀሲስ ዘበነ ለማ የነበረውን ውይይት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስ በዚህ ጉዳይ ከዚህ በፊት መልስ መስጠቴን አስታውሳለሁ ይሁን እንጂ አሁንም ይህንን መልስ ያዘጋጀሁት የውይይቱ ሃሳብ በፌስቡክ ፔጄ ላይ እኔና ትምህርቴን ለመቃወም ሲባል ተጽፎና ተለጥፎ ስላገኘሁት ፣ ላልፈውም ስላልፈለኩ ነው ተቃውሞውም እንዲህ የሚል ነው ሳራ የድንግል ማርያም ልጅ · Friends with N Lov Man and 3 others ህምምምምም በትክክል የመጽሃፍ ቅዱስ ቁጥርና ምእራፍ ሳታቁ ነው እንዴ የስነ መለኮት ምሩቅ ኣናት ላይ ፊጥ ምትሉት ለማንኛውም መብታችሁ ነው መለፍለፍ ማን ይከለክላችኋል ብትጮሁ ብታብዱ ። ሳራ የድንግል ማርያም ልጅ · 4 mutual friends https://youtu.be/uW1kSwfVB5g ለቢንያም እና ለኣቶ ዮናስ ይህ you tube ተመልከቱት ፡እንኳን እናንተን ከኛ የተሻለ እውቀት የሌላችሁ ዋናው የፕሮቴስታንት ምሁር ፕሮፊሰር ቶሎሳ እንዴት በመጽሃፍ ቅዱስ ዙርያ ስያጨናንቃቸው ማየት ትችላላቹ ወገኖች የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ በማለት ሰላምታዬን እያስቀደምኩ አሁን በቀጥታ ወዳዘጋጀሁት መልስ እገባለሁ ቤተመቅደስ በሐዲስኪዳን አንድና በኢየሩሳሌም ብቻ ያለ ስለሆነ እንኩዋን አይደለም በሐዲስኪዳን በብሉይ ኪዳን እንኳ ከኢየሩሳሌም ውጪ ቤተመቅደስ እንዲሠራ የተነገረ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የለም ከዚህ የተነሳ በሐዲስ ኪዳን ቤተመቅደስ ስንል የገነባነውና ወደፊትም የምንገነባው ጣራና ጉልላት ያለው ሕንጻ የለንም ወደፊትም አይኖረንም ሊኖረንም አይገባም ለምን? ስንል መጽሐፍቅዱሳችን እንደነገረን የዛሬዎቹ የሐዲስኪዳን ቤተመቅደሶች በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ታጥበን የዳንን የጌታ አማኞች ነን 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 9 _ 11 ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 9 ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 19 እና 20 ታድያ ዛሬ በሐዲስኪዳን ድንጋይ ኮልኩለን ፣ ሲሚንቶን በውሃ ለውሰንና አቡክተን የምንሰራው መቅደስ ከሌለን ደግሞ በቤተመቅደስ ውስጥ ልንቀድስበት የምናኖረው ታቦት የለንም ፣ ታቦት ከሌለን ደግሞ በመቅደስ ውስጥ ገብቶ የሚቀድስልን ክህነቱም ለእርሱ ብቻ የሆነ እኛም አስቀዳሽ ተብለንና ተሰይመን እርሱ ቀዳሽ እኛ አስቀዳሽ ልንሆንለት የተዘጋጀልን ካህን የለንም ደግሞም እንዲህ ያለ ካህን ልንሾምም ሆነ ልናዘጋጅ አይገባም ከዚህም ሌላ መጽሐፍቅዱሳችን የነገረን ቀዳሽነት ለካህን አስቀዳሽነት ደግሞ ለምዕመን ብሎ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ እስከወጣን ድረስ እኛ ሁላችን የንጉሱ ቀዳሾችና አስቀዳሾች መሆናችንን ነው የነገረን 1ኛ ጴጥሮስ 2 ፥ 9 እና 10 ፤ ራዕይ 1 ፥ 6 ፤ ራዕይ 5 ፥ 9 _ 14 ዘበነ ግን ይህ ዓይነቱ የመጽሐፍቅዱስ እውነት ስላልተገለጠለትና ወደዚህም ዓይነት መጽሐፍቅዱሳዊ መረዳት ስላልመጣ እንዲሁ ያለ እውነተኛ ማስረጃ አካኪ ዘራፍ ብሎና ከሜዳ ተነስቶ ለፈለፈ 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 20 እና 21 ወንጌልን በመስበክ የክርስቶስ የመከራው ተካፋይ የሆኑትን ሐዋርያትና የብሉይ ኪዳን ነቢያትንም በዚሁ በወንጌሉ ምክንያት የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በዋሻ በምድር ጉድጓድ እንደተቅበዘበዙ መጽሐፉ ስለሚናገር የገዳም ሕይወት ነው የኖሩት ሲል ባልተጻፈበት መንገድ ተርጉሞ ሰዎች ወደ ገዳም ገብተውና በዋሻ ተደብቀው በጸለዩት ጸሎት ነው የሚድኑት በማለት የኢየሱስን ብቸኛ አዳኝነትና በክርስቶስ ሥራ ብቻም የተገኘውን ደኅንነት ሊያስተባብል ሞከረ ነገር ግን አሁንም መዳን በኢየሱስ ብቻ ስለሆነ ኢየሱስ ብቻውን ያድናል የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ የምትለዋን ቃል ደግሞ ነጥሎ በማውጣትና ለገዳማዊ ሕይወትም ሆነ አመሠራረት በመስጠት ወንጌልን በዓለም ዞረው የመሠከሩትን አባቶች ሳይቀር እንደ ገዳም መነኩሴና ባሕታዊ ለጽድቅ ሲሉ በዋሻ ውስጥ የተቀረቀሩና የሞቱ እንደሆኑ አድርጎ በመቁጠር የምንኩስናንና የብሕትውናን አስፈላጊነት በጽኑ ሊያስረዳን ፈለገ ነገር ግን አሁንም ዘበነን አንድ እውነት ልነግረው የምፈልገው ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን ከሞተና እኛን ስለ ማጽደቅ ከተነሣ ሮሜ 4 ፥ 23 _ 25 ፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ፥ 3 እና 4 ይሄ እውነት የበራላቸው ነቢያቱም ሆነ ሐዋርያቱ የኢየሱስን ብቸኛ አዳኝነቱን አጽዳቂነቱንም ጭምር በትክክል ሰብከው ከመከራው ጽናት የተነሣ በዋሻና በምድር ጒድጓድ ከተቅበዘበዙ አዳኙና አጽዳቂው የኃጢአትንም ሥርየት የሚሰጠው ኢየሱስ እያለ ለምን ይሆን ዛሬ ድረስ ሰዎች ገዳም ገብተው ሰንሰለት ታጥቀውና ዳዋ ለብሰው ከሰውም ተለይተው እንዲህ ሲሰቃዩ የሚኖሩት ? ኢየሱስ ለመዳኛቸውም ሆነ ለኃጢአታቸው ሥርየት በቂ ሳይሆን ቀርቶ ? ወይስ የእኛ ኢየሱስን አለመስበክ ? ቀሲስ ዘበነ ለእነዚህ መጠይቆች የሰጠኸው ወደፊትም ቢሆን የምትሠጠው መልስ የለህምና ትምህርትህን እንደ እግዚአብሔር ቃል ብታስተካክል የሚል ምክር አለኝ አስተካክለህና ከዚህ ስሕተትህም ፈጥነህ ተመልሰህ ባይህ ለብዙዎች በረከት እንደምትሆን አምናለሁ ጌታ ይርዳህ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com

Saturday 10 March 2018

ለተወዳጁ ወንድማችን ዶክተር ወዳጄነህ የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስና የማስገንዘብያ ቃልለተወዳጁ ወንድማችን ዶክተር ወዳጄነህ የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስና የማስገንዘብያ ቃል የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዶክተር ወዳጄነህ መሐረነና የኤክሶዶስ ቲቪ ፕሮግራም አዘጋጅ በሆነችው እህታችን ቤተልሔም ታፈሰ መካከል በተደረገው ውይይት የቀረቡትን ሃሳቦች ተመልክተን ትክክል የሆነውን ትክክል ናቸው በማለትና አገልግሎታቸውንም ጭምር በመደገፍ ፣ በማበረታታት የተናገርን ሲሆን ትክክል ያልሆነውን ሃሳባቸውን ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እርምት እንዲያደርጉ ተገቢውን መልስ ሰጥተንበታል በተለይም በዚህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ እንድንነሳሳና መልስ እንድንሰጥበት ካደረጉን ነገሮች አንዱ የወንጌል ተቃዋሚዎችና አሳዳጆች ከሆኑት መካከል አብዛኞቹ የኦርቶዶክስ ዓበይት በዓላትንና አጽዋማትን እንደ መነሻ አድርገው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኢየሱስን አታውቅም ማለት በደል ነው ብለው የተናገሩትን የዶክተር ወዳጄነህን ንግጝር እና የማብራርያ ሃሳብ ምክንያት በማድረግ << ታላቅ ምስክርነት ፓስተር ዶክተር ወዳጄነህ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ሳያውቋት ለወጡትና ለሆዳቸው ብለው ለሚሰድቧት ትልቅ ትምህርት ነው >> ሲሉ ለተናገሩት ተቃዋሚዎቻችን መልስ ለመስጠት ስንል እኛም የዶክተር ወዳጄነህን የውይይት ሃሳቦች ማንሳትና እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነውን መልስ መስጠት ግድ ብሎናል እንደገናም ሁሉም ሰው እንዲሰማው እና እውነቱንም እንዲያውቅ ይህንን በቪዲዮ የቀረበ ምላሽ አዘጋጅተን ለቀናል ታድያ አገልጋይ ዶክተር ወዳጄ ነህ ከዚህ በፊት በነበረው አገልግሎታቸው በአብያተክርስቲያናት ዙርያ በተከፈተላቸው በር ሁሉ ታማኝ በመሆን ያስተላለፉትና የሰጡት ትምህርት በብዙዎች ዘንድ አስደሳችና ተወዳጅነትን ያተረፈላቸው መሆኑን ብዙዎች የሚመሠክሩትና እኛም የምናውቀው ጉዳይ ቢሆንም አሁን ላይ ለተደረገላቸው ቃለ ምልልስ ግን የተሳሳተ አስተያየትና እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ መልስ የሰጡ በመሆናቸው በሰማነው መልስ እራሳቸው ዶክተር ወዳጄነህን ሳይቀር ወደኋላ የተመለሱ ያክል ቆጥረን ከተቃዋሚ ጎራ የምንመድባቸው አድርጐናል ይሁን እንጂ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን እኛም ለዶክተሩ የምንሰጠው ትልቅ ምክር የአንድን ቤተ እምነት ዶክትሪንና የእምነት አስተምህሮ አንስቶ በአደባባይ ሊያውም በሶሻል ሚድያ እንዲህ ነው ሲሉ ከማውራትና ከመናገር በፊት የዛን ቤተ እምነት አስተምህሮ ከመነሻው አስቀድሞ በማወቅና አሁን ላይ ያለውንም ሁኔታ ደግሞ እንደሚገባ በመረዳት ከጅማሬ እስከ ፍጻሜው ያለውን እውነትና ስሕተቱንም ጭምር ጠንቅቆ በማወቅ ከመረጃ ጋራ መናገር በእጅጉ ያስፈልጋል እንላለን አለበለዚያ ግን ጉዳዩን አለማንሳቱም ሆነ አለመነካካቱ ይመረጣል የሚል ምክር ነው የምንሰጠው ይሁን እንጅ ይህንኑ ጉዳይ በአስተያየትና በምክር የምናልፈው ሳይሆን የዶክተሩንም የአደባባይ ይቅርታ እንፈልጋለን ለምን ቢባል ዶክተሩ ወደ ኦርቶዶክስ የተመለስኩኝ ትክክለኛ ኦርቶዶክስ በመሆኔ ነው ይህንን የተናገርኩት ቢሉ ኦርቶዶክስ ነኝ ያሉ በመሆናቸው በእኛ በኩል ከሃሳባቸው እንዲመለሱ ትምህርት ከምንሰጣቸውና ከምንጸልይላቸው ውጪ ሌላ ምንም ልንላቸው አንችልም ነበር ነገር ግን ዶክተሩ እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ አላሉም ኦርቶዶክስን ግን ከሥር መሠረቷ አብጠርጥረው የሚያውቋት ይመስል ተሃድሶ ፣ ማኅበረቅዱሳን እያላችሁ መዘላለፉ ቢቀርና ይቅርታ መጠያየቅ ብታደርጉ ሲሉ ሊመክሩን ወደዱ ይህ ብቻ አይደለም ጠባብ በሆነ ነገር ውስጥ ገብቶና አንድ ኦርቶዶክስ ይዞ ጴንጤ ማድረግ አግባብነት የሌለው እንደሆነ አያይዘው ሃሳባቸውን አክለዋል ይሁን እንጂ የእኛ አገልግሎት ግን እንደርሱ አይደለም በሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ በውስጥዋ ተወልደን ያደግንና መጻሕፍቶችዋ ሳይቀር የሚሉትን የተረዳን በመሆኑ ኦርቶዶክስን ወደ ጥንተ መሠረትዋ ለመመለስ እግዚአብሔር ያስነሳን ሰዎች ነን ኦርቶዶክስን ጴንጤ ልናደርግ የተነሣን ግን አይደለንም እርሳቸውም ይህንን አነሳሳችንን ከዚህ በፊት በነበረን መተዋወቅና ቅርርብ ውስጥ ጠንቅቀው ያውቁታል ከዚህ ሌላም በዚህ አገልግሎት ከእኛ ጋር ባይሰለፉም የአገልግሎታችን አጋዥ እንደነበሩ ላስታውሳቸው እወዳለሁ ታድያ ይሄ ሁሉ ነገር እያለ ዛሬ ይህን ማለቱ ለምን ይሆን ? ብያለሁ እንደገናም የተሃድሶና የማኅበረቅዱሳንን ግጭት ዶክተሩ ቀለል አድርገው በማየት የሠፈርና የጓዳኞች ግጭት ያክል ቆጥረው መዘላለፉ ቢቀርና ይቅርታ መጠያየቅ ቢኖር ማለታቸው ለሃሳቡ እንግዳና የሩቅ ሰው አድርገን እንድንቆጥራቸው ሊያደርጉን ሞክረዋል ይሁን እንጂ በዚህ አጋጣሚ ዶክተሩ በዚህ ነገር ገብተው ከሚቸጋገሩ የእኛን ነገር ለእኛ ቢተዉት መልካም ይሆናል ልላቸው እወዳለሁ ይቅርታን በተመለከተ ለይቅርታ ግን የማናችንም ልብ ክፍት ሊሆን ይገባል ብዬ እኔም የዶክተሩን ሃሳብ እጋራለሁ ይሁን እንጂ ግጭቱ ጊዜያዊ ግጭትና በቀላሉ በይቅርታ የሚታለፍም ሆነ የሚፈታ ግጭት አይደለም በእምነት መካከል የሆነ የልዩነት ግጭት ስለሆነ የሚፈታው ባለቤቱ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንደገናም መለያየቱም ሆነ ግጭቱ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ሳይሆን ከቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂ ከሆነው ሲኖዶስ ጋር ነው ማህበረ ቅዱሳን ግን በአባቶችና ተሃድሶ ስንባል ስያሜ ተሰጥቶን ከቤተ ክርስቲያኒቱ በተባረርነው ልጆቿ መካከል ጣልቃ ገብቶ በወንጌሉ ምክንያት የመጣውን ልዩነት እንደ እግዚአብሔር ቃል በቀላሉ እንዳይፈታ የቤተክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪ በመምሰል እያራገበ ፣ እያሟሟቀና እያጣላን ያለ ቡድን ነው ስለዚህ እኛ በአሁኑ ሰዓት ጉዳያችንንም ሆነ ጥያቄያችንን ይስማልንና መፍትሔ ይስጠን የምንለው ቅዱስ ሲኖዶስን ነው ማኅበረ ቅዱሳንን ግን አይደለም ከዚህ የተነሳ ምንም ውስጥ ከሌለና ከማይመለከተው ማህበረ ቅዱሳን ጋር እኛስ ምን ስንል ነው የምንጣላው ? እንደገናስ እንዴትስ ሆነን ነው የምንደራደረውና ይቅርታንስ የምንጠያየቀው ? ይልቁንም ማኅበረቅዱሳንን ለሁልጊዜ የምንመክራቸው አንድ እውነት እንደነበረ አስታውሳለሁ ያም ምንድነው ብትሉኝ አብዛኞቹ የቤተክርስቲያኒቱን የግዕዝ ቋንቋ የማያውቁና ጸዋትወ ዜማውንም ሆነ ቅዳሴውን ያልቀጸሉ በመሆናቸው ምስጢርን እንደሚገባ ያላደላደሉ ናቸው እንደገናም የቤተክርስቲያኒቱን አመሠራረትና የታሪክ እውነት በውል ያላወቁ በመሆናቸው ከዚህ በፊት በነበረው እምነትዋ ቤተክርስቲያኒቱ መጽሐፍቅዱስን መሠረት ያደረገችበትን እምነት ምን እንደሆነ ያልተገነዘቡ ናቸው ከዚህ የተነሳ ከመጽሐፍቅዱሱ ይልቅ ገድልና ድርሳንን በዋናነት ተቀብለው ይህንኑ ገድልና ድርሳን የእምነት አንቀጽ አድርጎ በመጥቀስ የቤተክርስቲያኒቱን እምነትም ሆነ የየግል የእምነት መረዳታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ እኛም ታድያ ይህንኑ ደከም ያለ መረዳታቸውን ስለምናውቅ ወደ ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል መረዳት እንዲመጡ እውነቱን ስለምንነግራቸው በብዙ ይጠሉናል ደግሞም ይጣሉናል ከዚህም ሌላ ይህም አልበቃ ብሎአቸው ከሲኖዶሱም ሆነ ከጳጳሳቱም ጋር ሊያጣሉን የሚሞክሩት በዚህ ምክንያት ነው ምስጢሩ እንግዲህ ይሄ ነው ዶክተር ወዳጄነህ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ አንተም በጉዳዩ አስበህበትና ጸልየህ ከልብህም ጋር ተማክረህ መረዳቶችህንና ነገሮችህን ሁሉ አስተካክለህ ዳግመኛ በጥሩ መንፈስና በንስሐ ልብ እንደምንገናኝ አምናለሁ ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com

Friday 9 March 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...

የጥምቀት ትምህርት የክፍል ሁለት ውይይት የጥምቀት ትምህርት የክፍል ሁለት ውይይት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን የጥምቀት ትምህርትን በክፍል ሁለት የውይይት ጊዜያችን አጠቃለነዋል በአጭሩ ትምህርቱን ለማስጨበጥ ያህል ጥቂት ማለት እፈልጋለሁ ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ዛሬ ላይ ለጥምቀት የተሳሳተ ትርጉም ሰጥታ ፣ በጥምቀት ዳግም መወለድና የጸጋ ልጅነት ይገኛል ስትል የጸጋ ልጅነትን ለማሰጠት ሕጻናትን ሳይቀር ማጥመቅ አስፈላጊ ነው ብላ በ አርባ ቀንና በ ሰማንያ ቀን የተወለዱ ሕጻናትን ብታጠምቅም ከዚህ በፊት በነበረው እምነትዋ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ የምትፈጸም ጥምቀት አንዲት ናት አንድ ጊዜ ከተፈጸመች ማለት ከተሰጠች በኋላ አትደገምም በካህን በኤጲስቆጶስ እጅ የምትፈጸመው ጥምቀት አንዲት ናት << ሊቀ ጳጳስ ወይም ጳጳስ ወይም ኤጲስቆጶስ ሳይመጣ አናጠምቅም አይበሉ ፤ የማጥመቅ ሥልጣን ያለው ያጥምቅ እንጂ የጥምቀት ሥልጣን አንዲት ናትና >> ተብሎ በሕገ ቀኖና ታዞአልና በማለት አስተምራለች ( አንቀጽ ሣልስ ፣ ቊጥር 29 ን ) ይመልከቱ ይህንን ማለትዋ እምነትዋ ከሐዋርያት እምነት ጋር ሲያያዝ የመጣ በመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን 4 ፥ 4 እና 5 ላይ የጥምቀትን አንዲት መሆንዋን ጥቅሶ ያስተማረውን ትምህርት አብነት አድርጋ ነው ይህ ብቻ አይደለም ሠለስቱ ምዕት በደነገጉት ጸሎተ ሃይማኖት በተሰኘው የእምነት መግለጫዋ ላይም ወነአምን በአሃቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ስትል ተናግራለች ከእነዚህ እውነቶች የተነሳ ታድያ አማናዊትዋ ማለትም እውነተኛዋ ጥምቀት አንዲትና የማትደገም መሆንዋ የታወቀ መሆኑን ለሁሉም ሰው ለማስገንዘብ እንወዳለን ይህ እንግዲህ የቤተክርስቲያኒቱ መልካም ጐንዋና አስተምህሮዋ በመሆኑ በዚህ ቀጥተኛና ትክክለኛ አቋዋምዋም እኛ ልጆችዋ ቤተክርስቲያኒቱን ልናመሰግናት እንወዳለን ይህ ብቻ አይደለም በአንቀጽ ሣልስ ቊጥር 27 በሕገ ቀኖና በፍትሕ መንፈሳዊ በተባለው መጽሐፍዋ ላይ ወተጠምቆትነሰ በማይ ውእቱ ተሳትፎትነ በሞተ ክርስቶስ ወእርገትነሂ እምነ ማይ ውእቱ ካዕበ አምሣለ ተንሲኦትነ ምስሌሁ በማለት ተናግራለች ወደ አማርኛው ስተረጉመው በውሃ መጠመቃችን በክርስቶስ ሞት አንድ መሆናችን ከውሃ መውጣታችን ሁለተኛ ከእርሱ ጋር የመነሳታችን ምሳሌ ተብሎ በሕገ ቀኖና ወይም በፍትሕ መንፈሳዊ ተደንጓል ማለት ሲሆን እንዲህ ስትል ከዚህ በፊት በነበረው እምነትዋና መረዳትዋ በመጽሐፍዋ ላይ ጽፋ ፣ ተናግራና አስተምራ አሁን ላይ ምን ነክቶአት ሕጻናት በተወለዱ በ አርባና በ ሰማንያ ቀን ተጠምቀው መንፈሳዊ ልጅነትን ያገኛሉ ስትል እስካሁን እስከ እኛ ዘመን ድረስ እንዳመነችና እንዳስተማረች ለእኔም ሆነ ለማናችንም ግልጥ አይደለም አደራረጉንም በተመለከተ መጽሐፍቅዱሳዊ ባለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አይደግፈውም ከዚህ የተነሳ በቅድምና የመረዳት እውነትዋም ሆነ በቃሉ እውነት መሠረት ተሃድሶ አድርጋ ወደ መጀመርያ እምነትዋና የማጥመቅ ሥርዓቷ ትመለስ እላለሁ ለምን ስንል ጥምቀት የጸጋ ልጅነትን ማግኛና ዳግም መወለጃ ሳይሆን እርስዋ በቀደመው ትምህርትዋ እንደገለጸችው ጥምቀት በክርስቶስ ሞትና መነሳት ለመተባበር የምናደርገው የእምነት ሥርዓት ነው ከዚህም ባሻገር አምኖ የዳነውን ሰው ለማጥመቅ ሥርዓተ ጥምቀቱ እንዴት መፈጸም እንዳለበት በሮሜ 6 ፥ 3 _ 5 የተጠቀሰውን መነሻ አድርጋ እንደገናም በሕገ ቀኖና በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀስ ሳልስ ሕገ ቀኖና ዘሰባልዮስ 107 ን በመጥቀስ ተጠማቂውን ሰው በሚያጠልቅና በታቆረ ውሃ ውሃ መጠመቅ እንዳለበት አጥማቂው ካህንም ተጠማቂውን በውሃ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያደረገ በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም ሊያጠምቀው እንደሚገባ ተጠማቂው በውሃ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ መጠመቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ሞትን ሽሮ የመነሳቱ ምሳሌ ነው ስትል ጽፋልናለች ደግሞም አስተምራለች የእኛም ጥያቄ ታድያ ይሄ መጽሐፍቅዱሳዊ የሆነው እውነት ይውጣና ቤተክርስቲያኒቱ ወደ መጀመርያው የእምነት መሠረትዋ ትመለስ ነው የምንለው ወድ ወገኖቼ ሆይ በትምህርቱ ላይ በሰፊው የተወያየንበት ስለሆነ ለተጨማሪ መረጃ በቪዲዮ የተለቀቀውን ተከታታዩን ትምህርት ስሙ ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካችሁ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com

Monday 5 March 2018

የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ (...የተቋቋመች ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ከአዳኟ ከኢየሱስ የተፋታችበት የቁልቁለቱ መንገድ ( ቊጥር 3 ) ክፍል አራት የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን :: ቤተክርስቲያናችን ከአዳኟ ከኢየሱስ ተለይታ ቁልቁለቱን መንገድ የመረጠችበትን የቊጥር 3 ሃሳብ እንመለከታለን :: የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የዚቅ መጽሐፍ ገጽ 174 ላይ << ከመ ትቤዙ ነቢያተ ወጻድቃነ አማን ተወልደት ………………. ማርያም >> አለን :: ወደ አማርኛው ስተረጉመው << ነቢያትንና ጻድቃንን ትዋጅ ዘንድ ………….. ማርያም በእውነት ተወለደች>> የሚል ትርጉም የሚሰጠን ነው :: መጽሐፍ ቅዱስ ግን እስመ ኩሎሙ አበሱ ወጌገዩ ወሐደጉ ስብሐተ እግዚአብሔር በማለት ይናገራል :: ወደ አማርኛው ስተረጉመው ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል ሮሜ 3 ፥ 23 ን እንመልከት:: ታድያ ድንግል ማርያምም የሰው ዘር ሆና ለዮሴፍ የታጨች በመሆንዋ የአዳም በደል በእርሱዋም አለና ከዚህ በደል ነጻ ናት ልንል አንችልም :: የአዳም በደል ስንል ደግሞ ጥንተ አብሶ ማለታችን እንደሆነ ለሁላችንም ግልጽ ሊሆን ይገባል የሉቃስ ወንጌል 2 ፥ 22 _ 32 እንመልከት:: ከዚህ አውነት የተነሳ ድንግል ማርያምም የኢየሱስን መድኃኒትነት ተቀብላ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሃሴት ታደርጋለች ያለች በመሆንዋ የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 47 ለበደለው ዓለምና በኃጢአቱም ምክንያት ሞት ለተፈረደበት ዓለም አዳኙ ኢየሱስ ብቻ ነው:: አዳኝነቱም እንዴት እንደሆነ ሐዋርያው ሊገልጽልን ነገር ግን በክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸጸድቃሉ አለን ::( ሮሜ 3 ፥ 24 ) ሐዋርያው ጴጥሮስ ደግሞ በክቡር በክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ በማለት የተዋጀንበትን እውነት ነገረን ( 1ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 19 ) የተዋጀ ሰው ማለት ደግሞ በዋጋ የተገዛ ማለት ነውና ለራሱ አይደለም ( 1ኛ ቆሮንቶስ 6 ፥ 20 ) ከእነዚህ የመጽሐፍቅዱስ እውነቶች አኳያ እንግዲህ ራስዋ ሳትቀር በክርስቶስ ደም የተዋጀችውን ድንግል ማርያምን ነቢያትንና ጻድቃንን ትዋጅ ዘንድ …….. ማርያም በእውነት ተወለደች ማለቱ ፍጹም መሳሳትና የመጽሐፍቅዱሱንም መሠረታዊ እውነት መካድ ይሆንብናልና ከዚህ ዓይነቱ ስሕተት ፈጥነን ልንመለስ ይገባል እላለሁኝ ሙሉውን ሃሳብ ለመከታተል በቪዲዮ የተለቀቀውን ትምህርት ስሙት ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com

Thursday 1 March 2018

ለሰዎች ዕድል መስጠት ( መክብብ 7 ፥ 20 ፣ ዘፍጥረት 39 ፥ 6 _ 10 ፣ ዕብራውያን 12 ፥ 1 _ 3 ፤ ዕብ...

በአንገታችን ላይ ስለምናስረው ማህተብ ታሪካዊ አመጣጥ ፣ ድንግል ማርያም ጌታ እየሱስ ክርስቶስን የወለደችው በሥጋ ...የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ በተለቀቀው ትምህርት በብዙ እንደ ተባረካችሁ እናምናለን:: ከትምህርቱ እንደተገነዘባችሁት ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ ነው የወለደችው አንጂ በመለኮቱ አልወለደችውም :: አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ ወለደችው የምንል ከሆነ በሥጋ የመጣበትን ዓላማ ፣ ሰው የሆነበትንም ምስጢር ፣ እኛን የሰው ዘር የሆነውን ሁላችንንም ያዳነበትን እውነት በብዙ የምንዘነጋ ስለምንሆን ትልቅ ስሕተት ውስጥ እንወድቃለን :: መጽሐፍቅዱሳችንም ሲናገር እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን ነው የሚለን ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 ን እንመልከት :: ስለዚህ ከአባቶቻችን በሥጋ የመጣው ክርስቶስ ፣ ከድንግል ማርያምም በሥጋ የተወለደው ክርስቶስ ፣ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው :: እንደገናም ድንግል ኢየሱስን ልትወልድ መልአኩ ሲያበስራት መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ነው ያላት የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 35 :: ታድያ ይሄ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም ሲወለድ የተወለደው በሥጋ ነው :: ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔርን ልጅ የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮት አይደለም :: ከዚህም ባሻገር ክርስቶስ የእኛን የማዳን ሥራ ሲያከናውን ኃጢአታችንን የተሸከመው በሥጋው ነው :: ሐዋርያው ጴጥሮስ በምዕራፍ 2 ቊጥር 24 ላይ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ይለናል :: ከዚህ ምንባብ ተነስተን እንግዲህ ድንግል ማርያም አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ አትወልደውም አምላክን የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮቱ ግን አይደለም ብለን ባንናገር ጴጥሮስ የተናገረውና ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋው የፈጸመው ይሄ ሁሉ እውነት የሚቀርብን ስለሚሆን : —— 1ኛ ) ክርስቶስ የመጣበትን የማዳን ዓላማ በብዙ እንስታለን 2ኛ ) ክርስቶስ በሥጋው የፈጸመልንን ይህንን እውነት ስለምንስት መዳናችን ሳይቀር አጠራጣሪ ይሆን ነበር :: ነገር ግን እኛ ከዚህ በተለየ መልኩ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በሥጋ ነው የተወለደው ብለን ስላመንን ለማዳን የመጣበትን ዓላማ አልሳትንም :: በክርስቶስ የሆነልንና የተፈጸመው ፣ እኛም አምነንበት በተቀበልነው የመዳናችን እውነት እርግጠኞች ነን ከዚህ የተነሳም ኢየሱስ አዳኝ ማርያምንም የኢየሱስ እናት መሆኗን እንናገራለን የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 ፣ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 3 ን ይመልክቱ :: አባቶቻችንም በዚህ ጉዳይ የመጽሐፍቅዱሱን ቃል በመከተል በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይና በሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸው ሳይቀር ይህንኑ እውነት ተናገሩ ትምህርቱን በዚሁ ቪዲዮ የለቀቅነው በመሆኑ ሁሉንም አሁን ማብራራት አልችልምና የተለቀቀውን ትምህርት ስሙ :: በጥቂቱ ዋናውን ሃሳብ መጥቀስ ቢያስፈልግ ግን በዚሁ በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ አንድምታ ላይ ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብዕሲ ወአድሃነነ የሚለውን ሊተረጉሙልን ፈቀደ ብሎ ነበርና ወዶም አልቀረ ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ :: ተወልዶም አዳነን :: << በሥጋ አለ በመለኮቱ አትወልደውምና አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብዕቱ እንዲል >> ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጽ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተወለደ ያጠይቃልና :: ልደት ቀዳማዊ ተአውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል :: ዳግመኛ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ ዕሩቅ ብዕሲ ባሉት ነበርና :: ሶበሰ ተወልደ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተኃዘብዎ ወእምረሰይዎ ሐሰተ ሲሉ ገልጸውታል :: በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ቅዱስ ሳዊርያኖስ ኤጲስቆጶስ ዘሀገረ ገብሎን እንዲህ ሲል ያስተማረውን እንጠቅሳለን በማለት ተናገሩ :: በማይመረመር ልደት በተወለደው በአካላዊ ቃል እናምናለን :: ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር ቀዳማዊ ደኃራዊ እርሱ ነው :: ዳግመኛ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በምድር ላይ ከቅድስት ድንግል ማርያም እርሱ በሥጋ ተወለደ :: በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል :: ይኸውም እግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ተናገረ ( ሃይማኖተ አበው ገጽ 105 ቊጥር 2 እና 3 ይመልከቱ ) :: ታድያ ከዚህ ከሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንዳየነው ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ማርያም ባይወለድ ኖሮ በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል ተብሎ አይጻፍልንም ነበር :: እኛም ከዳግማዊው አዳም በዳግመኛ ልደት አንወለድም ነበር :: ሃሳቡ ይህን ይመስላል ወገኖች ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39

የተወደዳችሁ ወገኖች ሰላም ለእናንተ ይሁን በዚህ በተለቀቀው ትምህርት በብዙ እንደ ተባረካችሁ እናምናለን:: ከትምህርቱ እንደተገነዘባችሁት ድንግል ማርያም አምላክን በሥጋ ነው የወለደችው አንጂ በመለኮቱ አልወለደችውም :: አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ ወለደችው የምንል ከሆነ በሥጋ የመጣበትን ዓላማ ፣ ሰው የሆነበትንም ምስጢር ፣ እኛን የሰው ዘር የሆነውን ሁላችንንም ያዳነበትን እውነት በብዙ የምንዘነጋ ስለምንሆን ትልቅ ስሕተት ውስጥ እንወድቃለን :: መጽሐፍቅዱሳችንም ሲናገር እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን ነው የሚለን ሮሜ 9 ፥ 4 እና 5 ን እንመልከት :: ስለዚህ ከአባቶቻችን በሥጋ የመጣው ክርስቶስ ፣ ከድንግል ማርያምም በሥጋ የተወለደው ክርስቶስ ፣ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው :: እንደገናም ድንግል ኢየሱስን ልትወልድ መልአኩ ሲያበስራት መንፈስቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ነው ያላት የሉቃስ ወንጌል 1 ፥ 35 :: ታድያ ይሄ ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከድንግል ማርያም ሲወለድ የተወለደው በሥጋ ነው :: ድንግል ማርያምም የእግዚአብሔርን ልጅ የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮት አይደለም :: ከዚህም ባሻገር ክርስቶስ የእኛን የማዳን ሥራ ሲያከናውን ኃጢአታችንን የተሸከመው በሥጋው ነው :: ሐዋርያው ጴጥሮስ በምዕራፍ 2 ቊጥር 24 ላይ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ በመገረፉ ቊስል ተፈወሳችሁ እንደ በጐች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ይለናል :: ከዚህ ምንባብ ተነስተን እንግዲህ ድንግል ማርያም አምላክን በአምላክነቱ ማለትም በመለኮቱ አትወልደውም አምላክን የወለደችው በሥጋ ነው በመለኮቱ ግን አይደለም ብለን ባንናገር ጴጥሮስ የተናገረውና ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋው የፈጸመው ይሄ ሁሉ እውነት የሚቀርብን ስለሚሆን : —— 1ኛ ) ክርስቶስ የመጣበትን የማዳን ዓላማ በብዙ እንስታለን 2ኛ ) ክርስቶስ በሥጋው የፈጸመልንን ይህንን እውነት ስለምንስት መዳናችን ሳይቀር አጠራጣሪ ይሆን ነበር :: ነገር ግን እኛ ከዚህ በተለየ መልኩ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በሥጋ ነው የተወለደው ብለን ስላመንን ለማዳን የመጣበትን ዓላማ አልሳትንም :: በክርስቶስ የሆነልንና የተፈጸመው ፣ እኛም አምነንበት በተቀበልነው የመዳናችን እውነት እርግጠኞች ነን ከዚህ የተነሳም ኢየሱስ አዳኝ ማርያምንም የኢየሱስ እናት መሆኗን እንናገራለን የማቴዎስ ወንጌል 1 ፥ 21 ፣ የሐዋርያት ሥራ 4 ፥ 12 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 2 ፥ 1 _ 3 ን ይመልክቱ :: አባቶቻችንም በዚህ ጉዳይ የመጽሐፍቅዱሱን ቃል በመከተል በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይና በሃይማኖተ አበው መጽሐፋቸው ሳይቀር ይህንኑ እውነት ተናገሩ ትምህርቱን በዚሁ ቪዲዮ የለቀቅነው በመሆኑ ሁሉንም አሁን ማብራራት አልችልምና የተለቀቀውን ትምህርት ስሙ :: በጥቂቱ ዋናውን ሃሳብ መጥቀስ ቢያስፈልግ ግን በዚሁ በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ አንድምታ ላይ ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርአ ብዕሲ ወአድሃነነ የሚለውን ሊተረጉሙልን ፈቀደ ብሎ ነበርና ወዶም አልቀረ ዘር ምክንያት ሳይሆነው ከድንግል ተወለደ :: ተወልዶም አዳነን :: << በሥጋ አለ በመለኮቱ አትወልደውምና አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብዕቱ እንዲል >> ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለጽ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደተወለደ ያጠይቃልና :: ልደት ቀዳማዊ ተአውቀ በደኃራዊ ልደት እንዲል :: ዳግመኛ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆን ኖሮ ዕሩቅ ብዕሲ ባሉት ነበርና :: ሶበሰ ተወልደ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ዘከማየ ብዙኃን እምተኃዘብዎ ወእምረሰይዎ ሐሰተ ሲሉ ገልጸውታል :: በሃይማኖተ አበው መጽሐፍም ቅዱስ ሳዊርያኖስ ኤጲስቆጶስ ዘሀገረ ገብሎን እንዲህ ሲል ያስተማረውን እንጠቅሳለን በማለት ተናገሩ :: በማይመረመር ልደት በተወለደው በአካላዊ ቃል እናምናለን :: ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር ቀዳማዊ ደኃራዊ እርሱ ነው :: ዳግመኛ ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ በምድር ላይ ከቅድስት ድንግል ማርያም እርሱ በሥጋ ተወለደ :: በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል :: ይኸውም እግዚአብሔር ቃል ነው በማለት ተናገረ ( ሃይማኖተ አበው ገጽ 105 ቊጥር 2 እና 3 ይመልከቱ ) :: ታድያ ከዚህ ከሃይማኖተ አበው መጽሐፍ እንዳየነው ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል ማርያም ባይወለድ ኖሮ በዚህ ዓለም የተወለደው ሰው ሁሉ ከዳግማዊ አዳም ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ይገባዋል ተብሎ አይጻፍልንም ነበር :: እኛም ከዳግማዊው አዳም በዳግመኛ ልደት አንወለድም ነበር :: ሃሳቡ ይህን ይመስላል ወገኖች ተባረኩ ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን Contact https://www.facebook.com/yonas.asfaw.39
 Primary: yonasasfaw8@gmail.com yonasgetaneh@ymail.com