Monday 31 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ሰባት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ሰባት ) የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሰባት ትምህርቴ ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ አማላጅነት ዙርያ እንደተለመደው የተሳሳቱ ሰዎች የተሳሳተ ማብራርያ እንዲህ ሲሉ ሰጥተዋል ምልጃ የፍጡር ሥራ ነው ሊያውም የጻድቃን ፣ የሰማዕታትና የመላዕክት ሥራ ነው እንጂ የክርስቶስ ሥራ አይደለም ክርስቶስ የጸለየው ፣ የሰገደው ለእኛ አብነት ሊሆነን ነው በአጠቃላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ያደረጋቸው ሥራዎች ወይንም የፈጸማቸው ተግባሮች ሁሉ ለአብነት ፣ ለአርአያ ያደረጋቸው ናቸው ክርስቶስ ለእኛ ሲል በለበሰው ሥጋ የተቀበለው መከራ እንዳልተሰማው ያሳያል ነገር ግን አማላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ? ሲል የጸለየው ጸሎት በለበሰው ሥጋ ሥቃይ ተሰምቶት ሳይሆን መከራ በደረሰባችሁ ጊዜ እናንተም እንደዚሁ ጸልዩ ለማለት የተደረገ ምሳሌ እንደሆነ ያመለክታል ሲሉ አስተምረዋል ይህ ነው እንግዲህ አውጣኪነት በፍጹም ሰውነቱ የሰራቸውን የአስታራቂነት ሥራዎች ለአርአያነት ብቻ የተደረጉ አስመስሎ ማለፍ የሰው ልጆችን ደኅንነት ከንቱ ያደርጋል በእርግጥም ከተፈጸሙት የደኅንነት ሥራዎችና የምልጃ ተግባሮች ጀርባ አርአያነታቸውም ጎልቶ ታይቷል እውነቱ ይሄ ሆኖ ሳለ ታድያ ሰዎቹ አሁንም የተሳሳተ መረዳታቸውን ቀጥለውበት ጌታችን በዲያብሎስ የተፈተነው ዲያብሎስ ከአጠገቡ የሚደርስ ሆኖ አይደለም ለአርአያነት ወይንም ለምሳሌነት ብቻ ሳይሆን ለአብነትም ጭምር ያደረገው ነው ፤ የጸለየውም የሚጎድለው ነገር ኖሮት ለማሟላት ሳይሆን ለአርአያነት እንደሆነ እናምናለን በአጠቃላይ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት የዘጋውን ገነት ለመክፈት ጸሎት ልመና ያላስፈለገውን ጌታ ፈያታዊ ዘየማን ከአዳም አስቀድሞ ገነት እንዲገባ የፈቀደ አምላክ እንዴት ዝቅ ያለ ሥራ ሠራ ለማለት ተሞከረ እንደገናም አምላክ ሰው ሆነ ማለት ፍጡር የነበረውን ሥጋ ተዋሃደ እንላለን እንጂ ፍጹም ሰው ሆነ አንለውም የሚሉትንና ሌሎችንም ሃሳቦች እነዚሁ ሰዎች ሰንዝረዋል እነዚህን ሃሳቦች በትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል በመመዘን ምልጃው አስታራቂነቱና ፍጹም ሰው መሆኑ እንዴት እንደሆነ ቅድሚያውን ወስደን ከመጽሐፍቅዱሳችን ፣ አያይዘንም የአባቶች መጽሐፍ ከሆኑት ሃይማኖተ አበው ፣ ቅዳሴ ፣ ሰዓታትና ጾመ ድጓ ከተባሉት ኦርቶዶክስ ከምትጠቀምባቸው መጻሕፍት ውስጥ እነዚሁ ሃሳቦች ማለትም ምልጃው አስታራቂነቱና ፍጹም ሰው መሆኑ እንዴት እንደሆነ እንደ ቃሉ እውነት ተጽፈውና ሰፍረው የተገኙ በመሆናቸው ከቃሉ ጋር በማመሳከርና ትክክለኛውን መልስ በመስጠት እንደሚከተለው በዚሁ ቪዲዮ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ ታድያ ይህንን ትምህርት በመስማት በዚሁ ትምህርት እንደምትባረኩ አምናለሁ ጌታ ዘመናችሁን ይባርከው ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Friday 28 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ስድስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል ስድስት ) በክፍል ስድስት ትምህርታችን በተደጋጋሚ በአንጋፋዋና ሐዋርያዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ውስጥም ሆነ ከቤተክርስቲያኒቱ ተገፍተው በወጡ አገልጋዮች በሚሰጠው የኢየሱስ የአማላጅነት ትምህርት ተጽዕኖ ሥር የወደቁ አንዳንድ ሰዎች ከመጽሐፍቅዱሱም ሆነ በመደበኛነት በግዕዙ ካለ ቃልና የአባቶች ትምህርት ነጻ የሆኑ ሰዎች በመሆናቸው እንዲሁ ተጠቅቼ ፣ መልስም አጥቼ ፣ ባዶ የቀረውን እጄን ከምሰጥ ሲሉ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ብቻ ተይዘውና ተውተርትረው ለወረወሩት የፈሪ ዱላ የተሰጠ መጽሐፍቅዱሳዊ መልስ ነው እንደገናም ቤተክርስቲያኒቱ የመጽሐፍቅዱሱን እውነተኛ አስተምህሮ ለመቀበሏ ማረጋጋጫ የሚሆን እንደ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍና ከመሣሠሉት መጽሐፎች ተጠንቶ በማስረጃነት የቀረበ በመሆኑ ከትምህርቱ ጋር በተያያዥነት ቀርቧል ይሄ ትምህርት ታድያ እንዲህ ላሉ ሰዎች ትክክለኛውን ምላሽ ከትክክለኛው ማብራርያ ጋራ የሰጠ ቢሆንም ከዚህም ባሻገር ቤተክርስቲያኒቱ የዛሬን አያድርገውና ከዚህ በፊት በነበረው መረዳቷ ትክክለኛ መሠረት ላይ እንዳለች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ማብራርያ ሰጪና ጠቋሚ የሆነ ትምህርትም ነው የተወደዳችሁ ወገኖቼ የክርስቶስ ኢየሱስ የአማላጅነቱን ትምህርት ዛሬ ላይ ላቅርበው እንጂ ማንኛውም በልዩ ልዩ ርዕስ የቀረበ መጽሐፍቅዱሳዊ ትምህርት ሁሉ በትክክለኛው መንገድ በሚሰጥበት ጊዜ ሁልጊዜም ተጽዕኖ አለው ተጽዕኖም ፈጣሪ ነው ይህንን ከመጽሐፍቅዱስ በብዙ ሥፍራዎች ላይ ልንመለከት እንችላለን በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን ? እነሆም ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል ፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ? ብለው የጠየቁ በተጽዕኖ ሥር የወደቁ ሰዎች ናቸው በሌላም ክፍል ላይ ሄደን ስንመለከት በጌታ ዘመንና በጌታም የወንጌል ትምህርት ጊዜ የነበሩ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፦ አንድ ስንኳ ልታደርጉ እንዳይቻላችሁ ታያላችሁን ? እነሆ፥ ዓለሙ በኋላው ተከትሎት ሄዶአል ተባባሉ ይለናል የሐዋርያት ሥራ 5 ፥ 28 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 12 ፥ 19 ን እንመልከት ታድያ እነዚህንና የመሣሠሉት በዘመኑ የነበሩ የሕግ መምህራን ሮሮዎችና ጩኸቶች ሁሉ ከእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ጫና የተነሣ የመጡ የምሬት ድምጾች ናቸው ይህንን ተጽዕኖ ለመከላከለም ሆነ ለመቋቋም አቅም ያጡ ሰዎች ያስተጋቡት የፍርሃት ድምጽ ፤ ታድያ ይሄ ድምጽ በየዘመናቱ እነዚህን ዓይነት በመሠሉ ሰዎች ሲስተጋባ ታይቷል ዛሬም ድረስ በተመሣሣይ መልኩ በመስተጋባት ላይ ይገኛል ይህ እንግዲህ የሚያሳየን ወገኖቼ የወንጌሉ ሬሾ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረና ከፍ እያለ እያደገም መምጣቱን ነው ስለዚህ እኛ እውነተኞቹ የወንጌል አገልጋዮችም ስለሆነው ነገር በብዙ ደስ ሊለንና ጌታንም ልናመሰግን ይገባል ስል ለእግዚአብሔር ባሮች ፣ የመከሩም ሥራ ተሳታፊዎች ሁሉ መልእክቴን ለማስተላለፍ እፈልጋለሁ ከዚህም ሌላ ሥራችንንም ከዛሬ ይልቅ ነገ በተቀላጠፈ ሁኔታ በከፍተኛም የእግዚአብሔር ብርታትና ኃይል በመንፈስቅዱስም ጉልበት መቀጠል እንዳለብን ይሰማኛል የዚሁ ቀጣይ የክፍል ሰባት ትምህርት በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ ይቀርብላችኋል እስከዚያው ተባረኩ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Monday 24 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አምስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አምስት ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ከረማችሁ ለዚህች ለተባረከች ቀን ያደረሰን አምላክ ክብር ይግባው በመቀጠልም በዛሬው ዕለት የምንመለከተው ሃሳብ የብሉይ ኪዳኑን ሊቃነ ካህናት አስታራቂነት ከሐዲስኪዳኑ ሊቀካህናችን ከኢየሱስ ጋራ ያላቸውን ልዩነት በንጽጽርና በዝርዝር የምንመለከተው ይሆናል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ዕብራውያን 7 ፥ 23 _ 25 ን መሠረት በማድረግ የአባቶች መጽሐፍና የቤተክርስቲያን መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ አበው የተሰኘው መጽሐፍ እንዲህ ይለናል ፦ ኤጲፋንዮስም ፦ ጌታ አስታራቂ ሆኖ በመምጣቱ የቀደሙ አስታራቂዎች የነበራቸውን ጉድለት ያሟላ መካከለኛ ነውና ቤዛ ( ምትክ ሆኖ የሚሞት ) እና አዳኝ መሆኑን አስረድቷል እንዲህ በማለት « ወበእንተ ዝንቱ እግዚእ መጽአ ወተሠገወ እምእጓለ እመሕያው ወኮነ እግዚአብሔር ቃል ሰብአ ከመ የኃበነ መድኃኒተ በመለኮቱ ወይሙት ቤዛነ በትስብእቱ » ጌታ ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከሰው ወገን ተወለደ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ አምላክ በመሆኑ ያድነን ዘንድ ሰው በመሆኑም ቤዛ ሆኖ ይሞትልን ዘንድ ( ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 58 ፥ ክፍል 13 ቊጥር 50 ) በማለት ነገረን በመሆኑም ጌታ አስታራቂ ሆኖ በመምጣቱ የቀደሙ አስታራቂዎች የነበራቸው ጉድለት ምን እንደሚመስል ወደ ሰባት ያህል የሚደርሱ ነጥቦችን ከመጽሐፍቅዱሳችን በማንሳትና ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ አስታራቂነት ጋር በማነጻጸር ትምህርቱ በዚህ መልኩ በቪዲዮ በሰፊው ተብራርቶ ቀርቦላችኋል ስሙት ተባረኩበት ለሌሎች ላልሰሙ ሰዎችም ሼር በማድረግ የአግልግሎቱ ተካፋዮች ሁኑ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አምስት ) የኢየሱስ አማላጅነት ( ክፍል አምስት ) የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች እንዴት ከረማችሁ ለዚህች ለተባረከች ቀን ያደረሰን አምላክ ክብር ይግባው በመቀጠልም በዛሬው ዕለት የምንመለከተው ሃሳብ የብሉይ ኪዳኑን ሊቃነ ካህናት አስታራቂነት ከሐዲስኪዳኑ ሊቀካህናችን ከኢየሱስ ጋራ ያላቸውን ልዩነት በንጽጽርና በዝርዝር የምንመለከተው ይሆናል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ዕብራውያን 7 ፥ 23 _ 25 ን መሠረት በማድረግ የአባቶች መጽሐፍና የቤተክርስቲያን መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ አበው የተሰኘው መጽሐፍ እንዲህ ይለናል ፦ ኤጲፋንዮስም ፦ ጌታ አስታራቂ ሆኖ በመምጣቱ የቀደሙ አስታራቂዎች የነበራቸውን ጉድለት ያሟላ መካከለኛ ነውና ቤዛ ( ምትክ ሆኖ የሚሞት ) እና አዳኝ መሆኑን አስረድቷል እንዲህ በማለት « ወበእንተ ዝንቱ እግዚእ መጽአ ወተሠገወ እምእጓለ እመሕያው ወኮነ እግዚአብሔር ቃል ሰብአ ከመ የኃበነ መድኃኒተ በመለኮቱ ወይሙት ቤዛነ በትስብእቱ » ጌታ ከወዲያ ዓለም ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከሰው ወገን ተወለደ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ አምላክ በመሆኑ ያድነን ዘንድ ሰው በመሆኑም ቤዛ ሆኖ ይሞትልን ዘንድ ( ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 58 ፥ ክፍል 13 ቊጥር 50 ) በማለት ነገረን በመሆኑም ጌታ አስታራቂ ሆኖ በመምጣቱ የቀደሙ አስታራቂዎች የነበራቸው ጉድለት ምን እንደሚመስል ወደ ሰባት ያህል የሚደርሱ ነጥቦችን ከመጽሐፍቅዱሳችን በማንሳትና ከሊቀካህኑ ከኢየሱስ አስታራቂነት ጋር በማነጻጸር ትምህርቱ በዚህ መልኩ በቪዲዮ በሰፊው ተብራርቶ ቀርቦላችኋል ስሙት ተባረኩበት ለሌሎች ላልሰሙ ሰዎችም ሼር በማድረግ የአግልግሎቱ ተካፋዮች ሁኑ ጌታ ዘመናችሁን ይባርክ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 20 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል አራት የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል አራት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን በክፍል አራት ትምህርታችን የምንመለከተው አሁን ላይ ባላችው ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ሦስት ዓይነት ሰዎች አሉ እነርሱም ፦ 1ኛ ) የኢየሱስን አማላጅነት ጨርሰው የሚክዱ 2ኛ ) ኢየሱስ ያማለደው እስከ መስቀል ሞት ድረስ ብቻ ነው ከዚያ በኋላ ግን በአባቱ ቀኝ በጌትነቱ ስለተቀመጠ አያማልድም የሚሉ አሉ መከራከርያ ጥቅሳቸው ደግሞ ዕብራውያን 5 ፥ 7 ሲሆን እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋራ ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት እያለ የሚቀጥል ነው 3ኛ ) ሦስተኛዎቹ ደግሞ ኢየሱስ አሁንም ስለ እኔ ይማልዳል ብለው የሚያምኑ ናቸው ዕብራውያን 7 ፥ 23 _ 25 ታድያ ይህንን መጠይቅ ወደ እያንዳንዳችን ስመልሰው ከእነዚህ ከሦስቱ መካከል እኛ በየትኛዎቹ ጎራ ነን ? መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎችና ለትምህርቱ ተከታታዮች እተወዋለሁ በእኔ በኩል ግን ለትምህርቴ ተከታታዮች እንደ ተጻፈልን እንደ እግዚአብሔር ቃል ለማስተላለፍ የምፈልገው ሰዎች ሁሉ ከዚህ የትምህርት ግርታና ግራ መጋባት ውስጥ ጨርሰው እንዲወጡ ፦ 1ኛ ) ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ እንዲያምኑ ( ሮሜ 9 ፥ 1 _ 5 ) 2ኛ ) ክርስቶስ በሥጋ ከድንግል እንደተወለደ አውቀው ወላዲተ አምላክ የሚለውን የእምነት አስተሳሰብ ወላዲተ ኢየሱስ በሚለው እንዲተኩ ወይንም እንዲለውጡ ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ዘእንበለ ዘርዓ ብዕሲ ወአድኀነነ ትርጉም እንበለ ዘር ማለትም ያለ ወንድ ዘር ክርስቶስ ከድንግል በሥጋ ተወለደ የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነው የሰኞ ውዳሴ ማርያም ) 3ኛ ) ክርስቶስ በሥጋ እንደ ሞተ እንያዲምኑ ( 1ኛ ጴጥሮስ 3 ፥ 18 ) 4ኛ ) በሦስተኛውም ቀን ሲነሳ በሥጋውም ጭምር የተነሳ አምላክ ነው እንጂ ሥጋውን ጥሎ የተነሳ አምላክ አለመሆኑን እንዲያውቁ እና እንዲያምኑ ይህንንም የምንረዳው ሀ ) ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን ማለቱ ከዚህ የተነሳ ቶማስም ጌታዬ አምላኬም ብሎ መመለሱ ኢየሱስም ስላየኸኝ አምነሃል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ማለቱ ( ዮሐንስ ወንጌል 20 ፥ 26 _ 31 ) ለ ) እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ ከማር ወለላም ሰጡት ተቀብሎም በፊታቸው በላ ይለናልና ይህንን ማድረጉ ( የሉቃስ ወንጌል 24 ፥ 36 _ 43 ) ሐ ) ከዚያም መልስ 40 ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን ማሳየቱ ( የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 3 ) መ ) ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ ማለቱ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ መቀበሏ ( የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 9 ) ሠ ) ከዚህም ሌላ መላዕክት በድምጻቸው እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል ? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል ማለታቸው ( የሐዋርያት ሥራ 1 ፥ 10 እና 11 ) ረ ) ይህንንም ሁኔታ ኢየሱስ እንዲህ ሲል አስቀድሞ መናገሩ ነገር ግን እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለው በዚያን ጊዜ ሊቀካህናቱ ልብሱን ቀዶ ተሳድቦአል እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለምን ያስፈልገናል ? እነሆ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል ምን ይመስላችኋል ? አለ ይለናል ( የማቴዎስ ወንጌል 26 ፥ 62 _ 68 ) በዚህ ቃል መሠረትም ይህ ሊቀካህናት ብቻ ሳይሆን ዛሬም የኢየሱስን በአምላክነቱ ብቻ ሳይሆን በሰውነቱም ጭምር በኃይል ቀኝ መቀመጥና በሰማይ ደመና መምጣት የሚያሳምማቸው የዘመናችን አውጣኪ ሊቃነ ካህናት ልብሳቸውን መቅደዳቸው የማይቀር ዕዳ ሆኖባቸዋል ስለዚህ ባገኙት የፌስቡክ ድኅረ ገጾች ሁሉ ኢየሱስ በአምላክነቱ ብቻ ሳይሆን በሰውነቱም ጭምር የሰራውንና የሆነውን ነገር በሰሙ ቁጥር ሲቆጡ ፣ ሲሳደቡና ከበዛው ብስጭታቸውም የተነሳ ልብሶቻቸውን ሳይቀር ሲቀዱ እነርሱም ሲቀደዱ እናያቸዋለን ደግሞም እንሰማቸዋለን ለዚህ ሁኔታቸው የምንሰጣቸው መልስም ከሰሙን!! እኛ ሳንሆን እውነቱን የገለጠው የመጽሐፍቅዱሱ ቃል ነውና ሳትበሳጩ ፣ ሌላም ሌላም ደረጃ ላይ ሳትደርሱ ከመጽሐፉ ሃሳብ ጋር በጊዜ ተስማሙ ነው የምንላቸው ኢየሱስ በሰውነቱም ጭምር ወደ ሰማይ መውጣቱ ፣ ማረጉና በአብ ቀኝ መቀመጡ በአምላክነቱ ለመቀመጥ ብቻ ሳይሆን ለአስታራቂነትና ለአማላጅነትም ጭምር ነው ይህንንም የዕብራውያን ጸሐፊ እንዲህ በማለት ይገልጸዋል ፦ _ ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀካህናት አለን እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት ( ዕብራውያን 8 ፥ 1 እና 2 ) ታድያ በዚህ ቃል መሠረት ለእኔስ እንዲህ ያለ ሊቀካህናት የለኝም የሚል ሰው ካለ የለኝም ያለው ለራሱና ራሱ ስለሆነ ምርጫው ነውና መብቱ ነው እንላለን ቃሉ በተገለጠለት ጊዜ ግን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀካህናት ለእኔም አለኝ ማለቱ አይቀርምና አሁን ላይ ባለው ነገሩ ቃሉን በፍቅር እንነግረዋለን እንጅ ልናስጨንቀውም ሆነ ልናስገድደው አንፈልግም _ በዕብራውያን 7 ፥ 26 ላይ ደግሞ እንዲህ ያለ ሊቀካህናት አለን ብቻ ሳይሆን ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀካህናት ይገባናል እያለ ሊቀካህናቱ ይገባናል የተባለበትን ዝርዝር ሁኔታ በጥልቀት ያስረዳል ( ዕብራውያን 7 ፥ 26 _ 28 ) ስለዚህ እኛ የሰው ልጆች ዛሬ ክርስቶስ በሰውነቱም ጭምር የመነሳቱን ፣ የማረጉን ፣ በአብ ቀኝም የመቀመጡንና የማማለዱን ጭምር ክደን እንዲህ ያለ ሊቀካህናት የለኝም ፣ አያስፈልገኝምም ከምንል ይልቅ አለኝ ያስፈልገኛል ማለቱ አማራጭ የሌለው ውሳኔያችን ቢሆን በበለጠና በተሻለ ሁኔታ ይህ ውሳኔያችን ደግሞ ደኅንነታችንን ሙሉ እና እርግጠኛ ያደርገዋል እንጂ የሚጎድልብን ነገር የለም አባቶችም በትምህርታቸው አያይዘው ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ ሊያሳዩን ፦ ዳግመኛ በችንካር በጦር የቆሰለውን የእኛን መከራ ተቀበለ አሉን ( ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 2 ፥ 6 _ 7 ) ቅዱስ ባስልዮስም " የሁሉ ፈጣሪ እንደ እኛ ያለ ሞትን በሥጋ ሞቶ ለሰው ሁሉ ሕይወትን ሰጠ " በማለትም ነገረን ( ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 15 ፥ ቁጥር 2 _ 3 ) ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለመዳናችን ከሰማይ ወረደ ከመንፈስቅዱስ የተነሳ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ ሲል የቅዳሴው መጽሐፍ ደግሞ ተናገረን ( ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ቊጥር 5 እና 6 ) ውድ ወገኖቼ ሆይ እዚህ ላይ ሃይማኖተ አበውንም ሆነ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴን መረጃዎች ማቅረቤ እነዚህን መጻሕፍት በመጽሐፍቅዱሳችን ከተጻፈው ቃል ጋር እኩል ሥልጣን ለመስጠትና እነዚህም መጻሕፍት የመጽሐፍቅዱስ ያክል ሥልጣን ያላቸው ናቸው ለማለት ብዬ ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዘመኗ የእውነትን ቃል የተቀበለችና የምትሠብክ መሆኑን እነዚህ መጻሕፍቶችዋ የሚጠቁሙ በመሆናቸው ወደ ትክክለኛው የመጽሐፍቅዱሱ ቃል እውነት እንድትመለስ ለመርዳት ነው በመጨረሻም ልል የምፈልገው ከመጽሐፍቅዱሳችንም ሆነ ከአባቶች ትምህርት በመነሣት ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚታመን መንፈስ ከእግዚአብሔር ነው ስለሚል ከእነዚህ እውነቶች የተነሣ እኔና እናንተም ስለ ክርስቶስ ያለንን መረዳት አስተካክለን ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ በመታመን ከእግዚአብሔር ልንሆን ይገባል 1ኛ ዮሐንስ 4 ፥ 1 _ 6 አለበለዚያ ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ ካልታመንን የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ያገኘናል በምትኩም ከእግዚአብሔር መሆናችን ይቀርና ከሰይጣን እንሆናለ ለዚህም ነው ዮሐንስ በመልዕክቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ነው ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል አሁንም እንኳ በዓለም አለ ያለን ቸሩ መድኃኔዓለም ጌታ ከዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ይጠብቀን መረዳታችንንም አስተካክሎ ፣ እኛም የእውነቱንና የስሕተቱን መንፈስ በዚሁ በተገለጠው ጌታ አውቀን በዚህ በትክክለኛውና በተገለጠው እውነተኛ ቃል ጌታ እግዚአብሔር ይምራን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Monday 17 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሦስት የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሦስት የክፍል ሦስት ትምህርት የኢየሱስን አስታራቂነት የምንመለከትበት ክፍል ነው 1ኛ ) ኢየሱስ ያስታረቀን በሞቱ ነው እናንተም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በሃሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ ቆላስያስ 1 ፥ 21 _ 23 2ኛ ) ሞቱ ምክንያታዊ ነው በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደተቸገረ ቆጠርነው …………………ትንቢተ ኢሳይያስ 53 ፥ 4 ፤ 1 _ 12 3ኛ ) የመሞቱና የማስታረቁ ውጤትና አጀማመሩ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር ይኸውም ዲያብሎስ ነው በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ ዕብራውያን 2 ፥ 14 ኢየሱስ ያስታረቀን በሞቱ ነው ሞቱ ደግሞ ምክንያታዊ እና ለውጤት የሆነ ሞት ነው ኢየሱስ ያስታረቀን በሞቱ ስለነበረ እርቁ ሙሉ ነው በመሆኑም ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ግማሽ የሆነ ማስታረቅን አላደረገልንም ስለዚህ እርቁ ሙሉ ነው ያልኩት ከዚህ የተነሳ ነው ታድያ በሞቱ የተፈጸመ እርቅ እያለ ሌላ የመታረቅያ መንገድ መፈለጉ አግባብነት ያለው አይደለም መጽሐፍቅዱሳችንም ሲናገር እንዲህ አለ ሰው በሕግ ሥራ የሚጸድቅ ከሆነ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ አለን ገላትያ 2 ፥ 21 ይመልከቱ የትምህርቱ ዋና ዋና ሃሳቦች እንግዲህ እነዚህ ናቸው ይበልጥ ቪዲዮውን ስትሰሙ ደግሞ ትባረኩበታላችሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Thursday 13 July 2017

የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሁለት ( ቊጥር 1 )የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሁለት ( ቊጥር 1 ) ስለተፈጠረው የኔትዎርክ ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን ይሁን እንጂ ትምህርቱ ሳይቋረጥ በሁለት ተከታታይ ቪዲዮዎች የቀረበ በመሆኑ ተከታተሉት የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሁለት የኢየሱስ አማላጅነት ትምህርት ከመጽሐፍቅዱሳችን ባሻገር በቤተክርስቲያኒቱ ካሉ የአባቶች መጽሐፍ ውስጥ ተጠቅሰውና ተጽፈው ስለሚገኙ በትምህርቱ ውስጥ ደረጃ በደረጃ ተዘርዝረውል ከዚያ መልስ ደግሞ የኢየሱስ ምልጃ ያመጣውን ውጤት ከመጽሐፍቅዱሳችን መልስ እንዲሁ የአባቶችን መጽሐፍ አንስተን ተመልክተናል ከእነዚህ ሃስቦች ውስጥም ዋና ዋናዎቹን መጥቀስ ቢያስፈልግ መጽሐፍቅዱሳችን በትንቢተ ኢሳይያስ 53 ፥ 12 ላይ ከዓመጸኞችም ጋር ተቆጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ ስለ ዓመጸኞችም ማለደ ያለውን በአባቶች መጽሐፍ በሃይማኖተ አበው ገጽ 124 ( 1986 ) ወይም ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 79 ክፍል 50 ቊጥር 38 ላይ እርሱ ራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነስቶአልና አለን ምልጃው ስላስገኘልንና ስላመጣልን ውጤት ደግሞ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ሊነግረን ወዶ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ከፊትሕ ት ጋር ደስታን አጠገብከኝ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ አለን መዝሙር 16 ፥ 11 ፣ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 28 ታድያ የሕይወትን መንገድ ያየነው ክርስቶስ በመስቀል ጐዳና ተጉዞና በዚሁ መስቀል ላይ ሕይወቱን ከፍሎ ባሳየው ምልጀ ውስጥ ነው በዚህ የኢየሱስ የማማለድ ጸሎት በተገኘ ውጤት ራሱ ኢየሱስ መንገድና እውነት ሕይወትም ሆነን በእኔ በቀር ካልሆነ ማንም ወደ አብ አይመጣም አለን የሐንስ 14 ፥ 16 ዕብራውያን 10 ፥ 19 ይህንን የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ተንተርሰው አባቶቻችን ደግሞ እስመ መኑሂ ዘይክል በፂሃ ኃበ እግዚአብሔር ዘእንበለ ወልድ አሉን ወደ አማርኛው ስተረጉመው ያለ ወልድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚቻለው የለም የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነው ሃይማኖተ አበው ገጽ 297 ፥ 8 ይመልከቱ ውድ ወገኖቼ ሆይ ትምህርቱ ወሳኝና በጣም ጠቃሚ ፣ ብዙ የሆኑ የእግዚአብሔር እውነቶችን ያዘሉ ሃሳቦችን የያዘ ስለሆነ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ቪዲዮውን ስሙት በመካከል ግን በኔት ወርክ ችግር ምክንያት ትምህርቱ ተቋርጦ ነበር ወዲያው ብዙም ሳልቆይ ሁለተኛውን ክፍል ቀጥዬ ለዛሬ ያዘጋጀሁትን ትምህርት በለቀኩት የሁለተኛው የቪዲዮ መልዕክት አጠቃልዬዋለሁ ስለተፈጠረው ችግር ከእኔ የመጣ ሳይሆን የኔት ወርክ ችግር በመሆኑ ይቅርታ ለማለት እወዳለሁ እንግዲህ እነዚህን የተለቀቁ ሁለት ቪዲዮዎች በየተራ ስሟቸው በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሁለት (ቊጥር 2 ) የኢየሱስ አማላጅነት ክፍል ሁለት ስለተፈጠረው የኔትዎርክ ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን ይሁን እንጂ ትምህርቱ ሳይቋረጥ በሁለት ተከታታይ ቪቪዲዮዎች የቀረበ በመሆኑ ተከታተሉት የተወደዳችሁ ወገኖች በክፍል ሁለት የኢየሱስ አማላጅነት ትምህርት ከመጽሐፍቅዱሳችን ባሻገር በቤተክርስቲያኒቱ ካሉ የአባቶች መጽሐፍ ውስጥ ተጠቅሰውና ተጽፈው ስለሚገኙ በትምህርቱ ውስጥ ደረጃ በደረጃ ተዘርዝረውል ከዚያ መልስ ደግሞ የኢየሱስ ምልጃ ያመጣውን ውጤት ከመጽሐፍቅዱሳችን መልስ እንዲሁ የአባቶችን መጽሐፍ አንስተን ተመልክተናል ከእነዚህ ሃስቦች ውስጥም ዋና ዋናዎቹን መጥቀስ ቢያስፈልግ መጽሐፍቅዱሳችን በትንቢተ ኢሳይያስ 53 ፥ 12 ላይ ከዓመጸኞችም ጋር ተቆጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ ስለ ዓመጸኞችም ማለደ ያለውን በአባቶች መጽሐፍ በሃይማኖተ አበው ገጽ 124 ( 1986 ) ወይም ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 79 ክፍል 50 ቊጥር 38 ላይ እርሱ ራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነስቶአልና አለን ምልጃው ስላስገኘልንና ስላመጣልን ውጤት ደግሞ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ሊነግረን ወዶ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ ከፊትሕ ት ጋር ደስታን አጠገብከኝ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ አለን መዝሙር 16 ፥ 11 ፣ የሐዋርያት ሥራ 2 ፥ 28 ታድያ የሕይወትን መንገድ ያየነው ክርስቶስ በመስቀል ጐዳና ተጉዞና በዚሁ መስቀል ላይ ሕይወቱን ከፍሎ ባሳየው ምልጀ ውስጥ ነው በዚህ የኢየሱስ የማማለድ ጸሎት በተገኘ ውጤት ራሱ ኢየሱስ መንገድና እውነት ሕይወትም ሆነን በእኔ በቀር ካልሆነ ማንም ወደ አብ አይመጣም አለን የሐንስ 14 ፥ 16 ዕብራውያን 10 ፥ 19 ይህንን የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ተንተርሰው አባቶቻችን ደግሞ እስመ መኑሂ ዘይክል በፂሃ ኃበ እግዚአብሔር ዘእንበለ ወልድ አሉን ወደ አማርኛው ስተረጉመው ያለ ወልድ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚቻለው የለም የሚለውን ትርጉም የሚሰጠን ነው ሃይማኖተ አበው ገጽ 297 ፥ 8 ይመልከቱ ውድ ወገኖቼ ሆይ ትምህርቱ ወሳኝና በጣም ጠቃሚ ፣ ብዙ የሆኑ የእግዚአብሔር እውነቶችን ያዘሉ ሃሳቦችን የያዘ ስለሆነ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ቪዲዮውን ስሙት በመካከል ግን በኔት ወርክ ችግር ምክንያት ትምህርቱ ተቋርጦ ነበር ወዲያው ብዙም ሳልቆይ ሁለተኛውን ክፍል ቀጥዬ ለዛሬ ያዘጋጀሁትን ትምህርት በለቀኩት የሁለተኛው የቪዲዮ መልዕክት አጠቃልዬዋለሁ ስለተፈጠረው ችግር ከእኔ የመጣ ሳይሆን የኔት ወርክ ችግር በመሆኑ ይቅርታ ለማለት እወዳለሁ እንግዲህ እነዚህን የተለቀቁ ሁለት ቪዲዮዎች በየተራ ስሟቸው በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ በማለት የምሰናበታሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com

Friday 7 July 2017

የሥዕል መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት በእናት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ዘጠኝየሥዕል መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት በእናት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ክፍል ዘጠኝ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በቅድሚያ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን በማለት የከበረ ሰላምታዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ በመቀጠልም በክፍል ዘጠኝ ትምህርታችን ላይ ከላይ በተመለከታችሁት አርዕስት በቪዲዮ የተላለፈ ትምህርት አዘጋጅቼ ለቅቄያለሁ የትምህርቱን ጭብጥ ሃሳብ በአጭሩ ለማስቀመጥ ኦርቶዶክሳዊት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ሥዕልን በተመለከተ ሦስት ዓይነት መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ታቀርባለች እነርሱም ፦ 1ኛ ) ቅዱሳት ሥዕላት 2ኛ ) ርኩሳን ሥዕላት ( ጣዖታት ) 3ኛ ) ዓለማውያን ሥዕላት የተወደዳችሁ ወገኖች በሦስት ደረጃ ተከፍለውና ተመድበው የተቀመጡትን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ሰጥታ ያስቀመጠቻቸውን ትምህርቱ በጥልቀት በመዳሰስና ትክክለኛ የሆነ መጽሐፍቅዱሳዊ የትምህርት እውነታን በማስያዝ ለሕዝባችን ተገቢውን ምላሽ ያቀርባል ለዛሬ የተመለከትናቸው ቅዱሳት ሥዕላትን በተመለከተ መጽሐፍቅዱሳችን ትክክለኛ ትርጉም ሰጥቶ ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው ስለዚህ ስግደት ፣ አምልኮ ፣ ውዳሴ ይገባቸዋልና ሥለን ልናመልካቸው ፣ ልናስመልካቸው ይገባል ብለን ስንጠይቅ መጽሐፍቅዱሳችን አሁንም ለዚህ የሚሰጠን መልስ የለም ቅዱሳት ሥዕላትን ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው ስንል የጠራናቸው እኛ እንጂ መጽሐፍቅዱሳችን አይደለም በሙሴ አማካኝነት በታቦቱም ላይ ሆነ በመጋረጃው ላይ የተሠሩት ኪሩብ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት እንዲሰራው የተደረጉ ኪሩቦች ናቸው እነዚህን ኪሩብ በመስራት ታድያ የታዘዘው ሙሴ እንጂ እኛ አይደለንም እንደገናም ሙሴን እግዚአብሔር ሲያዘው ማደርያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም ነው ያለው ዘጸአት 26 ፥ 30 በመሆኑም ሙሴ እግዚአብሔር ያላሳየውን አላቆመም የእግዚአብሔር ነቢይ ሙሴ ይህንንም ያደረገው በዓላማ ነው በሰማይ የነበረው የእግዚአብሔር አምልኮ በምድርም እንዲቀጥል እግዚአብሔር ስለፈቀደ በሙሴ አማካኝነት ይህንን አደረገ ምስጢሩ እንግዲህ ይሄ ነው ርኩሳን ሥዕላት የተባሉትም በተለያዩ መልኮች የሚሳሉ ሆነው የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚቃወሙና የሚሳሉ በተቃራኒው ደግሞ የሰይጣንን ክፉ ተግባራት የሚያወድሱት በሙሉ ናቸው በዚህ ዘመንም የጣኦት አምላኪዎች የሚጠቀሙባቸው ሥዕሎች የአምልኮ ምልክቶችና ጽሑፎች ወዘተርፈ ከዚህ ይመደባሉ ይሉናል ኦርቶዶክሳውያኑ የሥዕል ስነ አፈታት ባለቤቶች አያይዘውም በመጽሐፍቅዱስ ከሚገኙ ርኩሳን ሥዕሎች መካከል ፦ 1ኛ ) እስራኤላውያን በጥጃና በተለያዩ እንስሳት ምስል ሰርተው ያመልኳቸው የነበሩት ዘጸአት 32 ፥ 1 _ 10 2ኛ ) በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ንጉሡ አቁሞት የነበረው ከወርቅ የተሠራ ምስል ትንቢተ ዳንኤል 3 ፥ 1 _ ፍጻሜ 3ኛ ) ከነአናውያን ያመልኳት የነበረችው አስታሮት የተባለችው የሴት ምስል ወዘተ የመሣሠሉት ርኩሳን ሥዕላት ተብለው ይጠራሉ ሲሉ አሁንም ኦርቶዶክሳውያኑ መጽሐፍቅዱሳዊ ስነ አፈታት ይሰጣሉ መሣፍንት 2 ፥ 13 ፤ መሣፍንት 3 ፥ 7 ፤ መሣፍንት 10 ፥ 6 እና የመሣሠሉትን ብዙ የብዙ ብዙ ጥቅሶች መመልከት እንችላለን ከዚህ በተጨማሪም እነዚህ ርኩሳን ሥዕላት ፣ ርኩሳን ሥዕላት ተብለው ለመጠራታቸው የማጠናከርያ ጥቅሶች ናቸው ሲሉ እነዚህን የመጽሐፍቅዱስ ክፍሎች በአስረጂነት ያቀርቧቸዋል ዘዳግም 7 ፥ 25 ፤ 1ኛ ነገሥት 12 ፥ 28 _ 30 ፤ ትንቢተ ዳንኤል 11 ፥ 31 ፤ 12 ፥ 11 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 24 ፥ 15 _ 18 መመልከት ይቻላል ይሁን እንጂ ወገኖቼ ጌታ እግዚአብሔር ቅዱሳት ሥዕላትና ርኩሳን ሥዕላት ሲል ለይቶ የሚጠራቸው ሥዕሎች የሉትም ለእግዚአብሔር ሁሉም ሥዕሎች አንድ ዓይነትና እኩል ናቸው ለምን ስንል በዘጸአት 20 ፥ 1_ 6 ላይ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ ተብሎ ተጽፎልናል በዘዳግም 4 ፥ 15 ጀምሮ የተጻፈውን ስንመለከት ደግሞ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ ተብሎ ነው የተጻፈልን ወደ ሐዲስኪዳን ስንመጣም እግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ እግዚአብሔርን የምናመልከው በእውነትና በመንፈስ ነው የዮሐንስ ወንጌል 4 ፥ 23 እና 24 እንመልከት በመሆኑም ለርኩሳን ሥዕሎች የተሰጡ ጥቅሶች በሙሉ ቅዱሳን የተባሉ ሥዕሎችንም የሚመለከቱ በመሆናቸው አንዱ ከሌላው የተለየ ወይም የተሻለ የምንለው ነገር አይደለም በክፍል አስር ትምህርታችን ዓለማውያን ሥዕላት የሚለውን ተመልክተን የዚህን አርዕስት ማጠቃለያ ሃሳብ በመስጠት የክፍሉን ትምህርት በዚሁ እንቋጫለን አያይዘንም ወደ ቀጣዩ የትምህርት ክፍል እናልፋለን እስከዚያው ተባረኩ የምላችሁ ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ ነኝ God bless u all http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 https://www.youtube.com/yF76GIi_rCQ yonasasfaw8@gmail.com