Wednesday 25 May 2016

መጽሐፍቅዱስ የመጨረሻ የሕይወት ጥያቄን ይመልሳል Part 2

መጽሐፍቅዱስ የመጨረሻ የሕይወት ጥያቄን ይመልሳል Part 2







Image result for the bible answers life's ultimate questionsRelated image

3ኛ ) መጽሐፍቅዱስ የመጨረሻ የሕይወት ጥያቄን ይመልሳል











 Related imageRelated image





Related image
  








በአንድ ወቅት በአንድ ሁኔታና ነገሮች ላይ ሁልጊዜ የሚያስብ ሰው ስለ መፈጠሩና ስለ መኖሩ መሠረታዊ ጥያቄዎችን ይጠይቃል ከየት መጣሁ ? ለምን እዚህ ሆንኩ ? የሕይወት አላማው እቅዱና ግቡ ምንድነው ? እኔ ስሞት ምን እሆናለሁ ? መጽሐፍቅዱስ ስለ እነዚህ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ያቀርባል እነዚህ ሁሉ ስሜት ይሰጡናል መጽሐፍቅዱስ እኛን ለመምራት በእግዚአብሔር ሃሳብ የተሰጠበት ወይንም ኢንስፓየርድ ከሆነ

) በዘፍጥረት 1 1 ላይ በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ይለናል ስለዚህ ይህ ዓለምና በስነ ፍጥረት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ  የመጣው ከእግዚአብሔር ነው ማለትም የዚህ ሁሉ ፈጣሪውና አስገኚው እግዚአብሔር ነው

) በዘፍጥረት 1 26 _ 27 ላይ እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ይለናል ስለዚህ የሰውን ዘር የፈጠረው እግዚአብሔር ነው

) ዓለምንና በውስጥዋ ያሉትን ሁሉ እንዲሁም የሰውን ዘር በመፍጠር ሙሉ መብት ይዞ ወይንም ፈጣሪ ነኝ ብሎ የተናገረው ማነው ? ስንል

 ኢሳይያስ 45 12 ላይ በተጻፈው ቃል መሠረት ይህንን ሙሉ መልስ እናገኛለን

እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ፤ እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፥ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ ይለናል

) በሐዋርያት ሥራ 17 24 _ 28 መሠረት እግዚአብሔር እንዲፈልጉትና እንዲሹት ይፈልጋል

ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ፦ እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን ይላል

) ለዚህ እንድንኖር የጠራን ክርስቶስ ነው ለየቱ ስንል 2 ቆሮንቶስ 5 14 _ 15 እንደሚገባ ይመልስልናል


ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ


) የሰው ዘር ምን ሊያደርግ የተጠራ ነው ? ስንል መልሱን አሁንም መጽሐፈ መክብብ 12 13 _ 14 ይመልስልናል

የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና  ይለናል

) በዮሐንስ ወንጌል 11   25 _ 26 ላይ ደግሞ ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት ይለናል ስለዚህ ኢየሱስ ለሚያምኑበት ትንሣኤና ሕይወት በመሆኑ የሚያምኑበት ቢሞቱም ሕያው ይሆናሉና ለዘላለም አይሞቱም

) በዮሐንስ ወንጌል 14 1 _ 3 ላይ ደግሞ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ ይለናል

) የማያምኑ ሰዎች መጨረሻ ደግሞ የት ሊሆን እንደሚችል የራእይ መጽሐፍ ምእራፍ 21 8 ይዘረዝረዋል

ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው  ሞት ነው



4ኛ ) ትንቢታዊ ቃሎችን ሥራ ላይ ማዋል  


 


ብዙ ሰዎች የመጨረሻውንና ውድቅ የሆነውን የሰው ሃሳብ ይጠራጠራሉ ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻ የመጨረሻውን ያውቃል ነገር ምክንያት ነው እውነት እና እርግጠኛ ነገር መጽሐፍቅዱስ የያዘው ብዙ ሥራ ላይ የዋሉ ትንቢታዊ ቃሎችን ፣ መለኮታዊ ኢንስፓይሬሺኖችን በጥቅሉ የሚያቀርብ ነው ለኤሎች መጻሕፍቶች ተቆጥረው የማያልቁ እንደ መጽሐፍቅዱስ ያሉ ትንቢታዊ ቃሎችን አልያዙም ከዚህ በመቀጠል ጥቂት የሆኑ የመጽሐፍቅዱስ ትንቢታዊ ቃሎችን እንመልከት

) በትንቢተ ኢሳይያስ 46 10 ላይ      በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ ይለናል ስለዚህ ነቢዩ የመጨረሻውን ከመጀመርያው በማንሳት ያውጃል

) በኢሳይያስ 7 14 እና በማቴዎስ 1 : 18 _ 25 መሠረት ኢየሱስን ያሳሰበው ግድም ያለው ትንቢታዊ ቃል የመጣው እና ሥራ ላይ የዋለው ከላይ በተገለጸው ምንባብ መሠረት ነው

ኢሳይያስ 7 14 -  ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች

የማቴዎስ ወንጌል 1 18 _ 25 _ የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ  እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ     ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦    እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው ይለናል

) በትንቢተ ሚክያስ 5 2 እና በማቴዎስ 2 1 _ 6  መሠረት   ትንቢታዊው  ቃል ኢየሱስ የት የተወለደ ነበር ይለናል ስንል መልሱን በዚሁ በጠቀስነው የመጽሐፍቅዱስ ቃል ላይ እናገኘዋለን


 በትንቢተ ሚክያስ 5 2 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል ይለናል


በማቴዎስ 2 1 _ 6  መሠረት ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት ይለናል


) 700 ዓመት ወደፊት የሚያመሳክረው ይህ ምዕራፍ የሚለው


የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም
በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም
በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር
እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል
ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ የሚል ነው



) ኢየሱስ ይህንን ትንቢታዊ ቃል ሥራ ላይ  አዋለ

 

ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ  የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች ይለናል የሉቃስ ወንጌል 24 20 _ 24


) ይህ ትንቢታዊ ቃል ሥራ ላይ የዋለው መቼ ነበር _________________

መልሱን ለእናንተ ለአንባቢዎች እተዋለሁ



No comments:

Post a Comment