Friday 20 May 2016

የመልእክት ርዕስ : - ፊተኝነት የእግዚአብሔር ጉዳይ ነው ( ዘፍጥረት 48 ፥ 15 _ 22 ) የመልእክት ርዕስ : - ፊተኝነት የእግዚአብሔር ጉዳይ ነው ዘፍጥረት 48 ፥ 15 _ 22 ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው ዘፍጥረት 48 ፥ 20 በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው ( አዲሱ መደበኛ የመጽሐፍቅዱስ ትርጉም) (ዘፍጥረት 48 ፥ 20) Thus he put Ephraim before Manasseh ( Genesis 48 : 20 ) ፊተኝነት በእግዚአብሔር ቤት የእግዚአብሔር ስምምነት እንጂ የሰዎች የጋራ ስምምነት አይደለም በዮሴፍ ቤት በሁለቱ ወንድማማቾች መካከል የነበረው ፊተኝነት ያዕቆብንም ሆነ ዮሴፍን የተመለከተ የእነርሱንም የየግል ስምምነት እና ፍላጎት ያሳተፈ እንዲሁም የነዚህኑ የብላቴኖችን የውስጥ ፈቃደኝነት ሳይቀር የጠየቀ ፊተኝነት አልነበረም ታድያ በዚህ ክፍል ላይ እንደምንመለከተው ትንሹ ኤፍሬም ከትልቁ ከምናሴ ይልቅ ፊተኛ ሲሆንና እግዚአብሔርም ፊተኛ ሲያደርገው የአሕዛብ ሙላት ሊሆን እንጂ ፊተኛ መሆን ስለነበረበት አይደለም በመሆኑም ዛሬም በእኛ ዘመን እኛ ፊተኛ የምንሆነው ፊተኛ መሆን ስለነበረብን አይደለም እንዲህ የምናስብ ከሆነ ከምንጊዜውም በላይ የተሳሳትን መሆናችንን ከወዲሁ ልናውቅ ይገባል ፊተኞች የሆነው እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው ነገር ስላለ እና እኛም የምንሆነው የምናደርገውም ነገር ስላለ ነው ፊተኝነት እኛ የምንቀድምበት ፣ በይገባኛልና ያስፈልገኛል ስሜት ውስጥም ሆነን የምንቆምበት ጉዳይ ሳይሆን እግዚአብሔር እኛን ለተልእኮው ፍጽምናና ለሙላቱ የሚያስቀድምበት የእግዚአብሔር መርሃ ግብር ነው እግዚአብሔር እኛን ባስቀደመበት ነገር ሁሉ ሙላት አለ በምትኩም ሃዘን በደስታ ፣ ልቅሶ በሳቅ ፣ ስቃይ በእፎይታ ይለወጣል የሰይጣን ተግዳሮትና የቃልኪዳን ሥራውም ይፈርሳል እኛ ስንቀድም ግን ይሄ ሁሉ የለም እንደውም የስቃዩ ፣ የተግዳሮቱ ፣ የለቅሶውና የሐዘኑ መጠን ከሚቀንስ ይልቅ በዚያው ልክ እየጨመረ ይመጣል ዛሬ እንደውም እየሆነ ያለው ይሄ ነው ይህ እንግዲህ ታድያ በጉልህ የሚያሳየው ሽንፈታችንንና ውርደታችንን ነው በመጽሐፍቅዱሳችን እግዚአብሔር ፊተኛ አድርጎ ከሚያስቀድማቸው ውጪ ፊተኛ ሆነው እንቅደም ሲሉ የቀደሙ እንደዛሬው እንደ እኛ ዘመን እንደ አሸን ባይፈሉም በቁጥር ግን ጥቂቶች ናቸው ፊተኞች ሁዋለኞች ይሆናሉ ተብሎ በተጻፈውም ቃል መሠረት እነርሱም ወደ ሁዋላ ቀርተዋል አንዳንዶቹም በንስሐ ተስተካክለዋል ታድያ የዛሬው በራስ የመጣ ፊተኝነት ግን ጊዜ አግኝቶ መቼ እንደሚስተካከል በውል ባላውቅም ፊተኝነት የእግዚአብሔር ጉዳይ ሆኖልን በቪዲዮ ትምህርቴ ላይ እንደዘረዘርኩዋቸው ቅዱሳን ሰዎች ይሄው የፊተኝነት ጉዳይ እኛን የሚመለከት ሆኖና እኛኑ ፈልጎ የመጣ ከሆነ እኛንም እንደነዚሁ ቅዱሳን ሰዎች በትክክለኛው እና በተገቢው ቦታችን ላይ መጥተን ለጥቅም እንድንሆን ወደፊት ይውሰደን ያኔ ለብዙዎች በረከት እንሆናለን ጌታ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ በመቀጠልም ይህን ቪዲዮ እንድትከታተሉ በማክበር እጋብዛለሁ የ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry አገልጋይ ቀሲስ ዮናስ ጌታነህ

No comments:

Post a Comment