Wednesday 25 May 2016

መጽሐፍቅዱስን የማመን ምክንያት መጽሐፍቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው Part 1




መጽሐፍቅዱስን የማመን ምክንያት መጽሐፍቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው Part 1

Image result for bible pictures      Image result for bible pictures




1ኛ) መጽሐፍቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ክሌም ያደርጋል (ሙሉ መብት ይዞ ወይንም የእግዚአብሔር ቃል ነኝ ብሎ ይናገራል)


እውነተኛውን ነገር በዚህ ውስጥ ስንመለከት መጽሐፍቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነኝ ሲል ክሌም የሚያደርግ ወይንም ሙሉ መብት ይዞ ማለትም  የእግዚአብሔር ቃል ነኝ ብሎ የሚናገር ብቻ ሳይሆን እርሱ የመነሻም ሃሳብ ነው 
 Related imageImage result for the bible claims to be the word of godImage result for the bible claims to be the word of god

) በ1ኛ ተሰሎንቄ 2 13 መሠረት በሰው የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ወይንም ምንጩ መለኮታዊ      ( የእግዚአብሔር የሆነ )  እርሱ የእግዚአብሔር ቃል ነው 

  በ1ኛ ተሰሎንቄ 2 13 ላይ እንዲህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል እናገኛለን 

ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን 



  ) በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3 16 መሠረት እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት በሙሉ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው

 አሁንም በ2ኛ ጢሞቴዎስ 3 14 _ 17 አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ይለናል

) በ2ኛ ጴጥሮስ 1 20 እና 21 መሠረት ይህ የትንቢት መጽሐፍ መጽሐፍቅዱስ ተነሳሽነት አግኝቶ ወይንም ኢንስፓየርድ ሆኖ የተጻፈ መጽሐፍ ነው


2ኛ ጴጥሮስ 1 20 እና 21 እንዲህ ይላል ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ


2ኛ )  መጽሐፍ ቅዱስ የስነ ምግባር አቅጣጫን የሚሰጥ ነው

መጽሐፍቅዱስ የስነ ምግባር አቅጣጫን ለመስጠት የሚረዳ መጽሐፍ ብቻ አይደለም ሌላው ቀርቶ ሕዝቦች እግዚአብሔርን  በሙሉ መብት ለማመን በማይችሉበት ጊዜ በቁዋሚነት ነገሮች ትክክል ወይንም ስሕተት መሆናቸውን በስሜታቸው አንድ ነገር እንዳለ እንዲያውቁ ይሆናሉ ምክንያቱም እግዚአብሔር በራሱ መልክ ፈጥሮአቸዋልና ትክክለኛውንና  ስሕተቱን በስሜታቸው እንዲያውቁ ንቃትን እርሱ ይሰጣቸዋል



ሮሜ 2 14 _ 16 የተጻፈልን ሃሳብ ይህንን እውነት ያሳየናል ይህም የእርሱ የስነ ምግባር ሕግ ይባላል


  ) ሮሜ 2 14 _ 16  ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል ይለናል

) በትንቢተ ኢሳይያስ 45 19 ላይ ጌታ እግዚአብሔር አንድን አዋጅ አውጆአል

በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ ቅንንም አወራለሁ

 

)በትንቢተ ኢሳይያስ 48 17 _ 18 እግዚአብሔር ለእኛ የተሻለና የበለጠ ነገር አጥብቆ ፈልጎአል

ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅሕም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር

 

) የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ወይንም ሕግጋትን ስንታዘዝ ምን ዓይነት ልምምድ እናገኛለን ? መልሱን ለእናንተ _________________________




) ደራሲው እግዚአብሔርን የጠየቀው ነገር


በትእዛዝህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ ( መዝሙር 119 66 _ 67 )



No comments:

Post a Comment