Monday, 29 May 2017
የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ( ክፍል አስራ ሰ...የቃልኪዳኑ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ ስለመምጣቱ የተገኘ የክፍል ሁለት ትረካና የመጽሐፍቅዱስ እውነታ ክፍል አስራ ሰባት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን ይህ የቃልኪዳኑ ታቦት ትምህርት የመጨረሻውና የማጠቃለያው ትምህርት ነው በዚህ ትምህርት ውስጥ የምንመለከተው ከክብረ ነገሥት ጋር በተያያዘ መልኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት ፕሮፌሰር ግራንት ጄፈሪ የተሰኙ ካናዳዊ የመጽሐፍቅዱስ ምሁር "Armageddon :- Appointment of Destiny " በተሰኘው መጽሐፋቸውና እንደዚሁም " The Ark of the Covenant and the red Heifer " በሚል ባስቀረጹት ትምህርታዊ ቪዲዮአቸው የቃልኪዳኑ ታቦት ስለሚገኝበት ሥፍራ ወደፊትም ስለሚኖረው መለኮታዊ ሚና ሰፊ የሆነ ታሪካዊ ትንታኔና አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፕሮፌሰሩ ይህንን ታሪክ በትንታኔ ሲያቀርቡ አቀራረባቸው በክብረ ነገሥት ከተጻፈው ሃሳብ ጋር የተገናኘ ይመስላል ያቀረቡትም በዚህ መልኩ ነበር ወጣቱ ምኒሊክ አባቱን ጎብኝቶና በእሥራኤል የነበረውን ቆይታውን አጠናቆ ሲመለስ ሳለ አባቱ ንጉሥ ሰሎሞን ልጁ ምኒሊክ ከእናቱ ሀገር ከኢትዮጵያ እየመጣ በአይሁዳውያኑ ቤተመቅደስ ውስጥ ለማምለክ ስለሚቸግረውና መንገዱም ሩቅ ስለሆነ ለአምልኮት ሥርዓት ይዞት የሚሄደውን ታቦት ቅጂ ወይንም ት መሣሣዩን አሰርቶለት ነበር ይሁን እንጂ ምኒሊክ የአባቱን ከእግዚአብሔር መንገድ ሕግና ሥርዓት መራቅ ስለተመለከተና ልቡም በአሕዛባውያን ሴቶች ጣኦቶቻቸው ፍቅር በመነደፉ እጅጉን አዝኖ ትክክለኛውን ታቦት ከአይሁዳውያኑ ቤተመቅደስ ሰርቆ ወደ አክሱም ይዞ እንደመጣ ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል ታድያ ታሪኩን በታሪክ ደረጃ ብንቀበለውም ከዚህ በፊት እንደተማርነው ታቦቱ በኢዮስያስ ዘመን በቤተመቅደስ ውስጥ ስለነበር በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጣ ለማለት አንደፍርም 2ኛዜና መዋዕል 35 ፥ 3 እንደገናም በሴዴቅያስ ዘመን ወደ ባቢሎን ተማረከ ብንል እንኳ በሰሎሞን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ሄዶአል ብለናልና የተማረከው ከኢትዮጵያ ነው ? ወይንስ ከኢየሩሳሌም ? የሚለውን ጥያቄ ያስነሳብናልና የታሪክ መፋለስን ስለሚያስከትል ልክ አይሆንም 2ኛዜና መዋዕል 36 : 11— 23 እንደገናም ከእንግዲህ የእሥራኤል የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይጠሩትም አያስቡትም ተብሎ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረ ትንቢት ስላለ ትንቢተ ኤርምያስ 3 ፥ 16 ዘሩባቤል ባሰራው ቤተመቅደስ ታቦቱ አልነበረምና ለእሥራኤል ያልሆነ ታቦት ለእኛም አይሆንም ከዚህም ሌላ በሐዲስ ኪዳን ሕጉን በልቡናቸው አኖራለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ በማለት የተናገረ ነውና ዛሬ ሕጉ የተጻፈው በእኛ በልቡናችን ሰሌዳ ላይ እንጂ በግራሩ እንጨት ላይ አይደለም ዕብራውያን 8 ፥ 8 _ 13 ሌላው የሰው ወርቅ አያደምቅ እንደተባለው ታቦት የተሰጠው ለእሥራኤል ሕዝብ በመሆኑ የሌላ ሕዝብ ታሪክ ለራሱ ለዛው ሕዝብ እንጂ ለእኛ የሚጠቅመን ነገር አይደለም መጽሐፍቅዱሳዊው ምሁር ፕሮፌሰር ግራንት ጄፈሪ እንዳሉትም ታቦቱ ከእሥራኤል ኮፒ ሆኖ ወይንም ቅጂ ሆኖ ተመሣሣዩ መጣ ቢባል እንኳ አለበለዚያም ደግሞ ሰሎሞን በአሕዛብ ሴቶች ፍቅር በመነደፉ ምክንያት ልጁ ሚኒሊክ ቅር ተሰኝቶ ዋናውንና ኦርጂናሉን ታቦት ያመጣው ነው ብንልም ለእኛ በአሁኑ ሰዓት ወደ አዲሱ ኪዳናችን ወደ ኢየሱስ የተሸጋገርን በመሆናችን የሚጠቅመን ነገር የለም አዲሱ ኪዳናችን ኢየሱስ ወደ እኛ ወደ እያንዳንዳችን ሲመጣ ቅጂ ሆኖ ወይንም ኮፒ ሆኖ ከዚህም ሌላ ተሠርቆም የመጣ አይደለም መጽሐፍቅዱሳችን አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነው ለሚጠሩትም ባለጠጋ ነው ስላለን የሁላችን ጌታ ሊሆን ወደ እያንዳንዳችን መጣ ስለዚህ ይሄ ጌታ የአይሁዳዊውም የግሪኩም የአሕዛቡም ሆነ የጨዋውና የባርያውም ጌታ ነው በዚያው መጠን ደግሞ ለሚጠሩትም ባለጠጋ ነው በመሆኑም ይሄ ጌታ እንደ ብሉይ ኪዳኑ የቃል ኪዳን ታቦት ለእሥራኤል ብቻ የሆነ አይደለም ሮሜ 10 ፥ 8 _ 13 ከዚህ የተነሳ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስተሠርይ የእግዚአብሔር በግ እነሆ ተባለ ዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 29 ከዚህ ባሻገርም በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ባለ መለያየት ምክንያት ስለ አሕዛብ ሊናገረን ወዶ ልባቸውን በእምነት ሲያነጻ በእኛ እና በእነርሱ መካከል አንዳች አለየም ተባለ ሌላው ቀርቶ አብርሃም ሳይገረዝ በነበረ እምነቱና ከተገረዘም በኋላ ለሁሉም አባት የተባለ ነበረ ሮሜ 4 ፥ 11 እና 12 ን ይመልከቱ ትምህርታችን እንግዲህ በጥቅሉ ይህንን ይመስላል በሰላም ጀምረን እንድናጠናቅቅ የረዳንን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን አነሳስቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment