Tuesday, 9 May 2017
የሙሴን ሕግ ያልተከተለ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ያለ የታቦትና የጽላት አሠራር ( ክፍል አስራ አንድ )የሙሴን ሕግ ያልተከተለ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ያለ የታቦትና የጽላት አሠራር ክፍል አስራ አንድ ታቦት የጽላቱ ማደርያ ነው ዘጸአት 40 ፥ 20 ጽላቱ ደግሞ ቅዱስ ቃሉ የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት ነው ዘጸአት 34 ፥ 27 እና 28 ስለዚህ እነዚህ ሁለት ነገሮች ዛሬም በሐዲስ ኪዳን አሉ ይሉናል ሆኖም ግን አሰራሩ ሙሉ በሙሉ የሙሴን ሕግ የተከተለ አይደለም ዘጸአት 25 ፥ 10 _ 18 ይሁን እንጂ ያም ቢሆን ፦ 1ኛ ) ታቦትን የመቅረጽና የመሥራት ሂደት የቀኖና ጉዳይ እንጂ የዶግማ ጉዳይ ስላልሆነ ይሉናል ይህን ማለታቸው ደግሞ ታቦትን የመቅረጽና የመሥራት ሂደት መጽሐፍቅዱሳዊም ቢሆን በእኛ እምነት ግን ቀኖናዊና ሥርዓታዊ በመሆኑ በሐዲስ ኪዳን ታቦት ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍጥረት 1 ፥ 31 መሠረት እግዚአብሔርም የፈጠረውን ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውንም ስለማይንቅ ከግራር እንጨት ሌላ በማይነቅጽ በሌላ እንጨትም ከተገኘ ታቦትን እንሠራለን ይላሉ 2ኛ ) ጽላቱንም በተመለከተ ከቻልን በመጽሐፉ ቃል መሠረት ከድንጋይ ጽላት መቅረጽ እንችላለን ዘጸአት 34 ፥ 1 ፣ 4 ፣ 27 እና 28 ካልቻልን ጽላቱንም ከማይነቅዝ እንጨት መቅረዝ እንችላለን በሌላ በኩልም ይላሉ ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን ካልቻልን ደግሞ በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል በተጨማሪም የጽላቱ ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እንችላለን ይላሉ ይሁን እንጂ መጽሐፍቅዱሳችን ፦ ሀ ) የብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፎአልና ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ለእኛ የብሉይ ኪዳኑ ዓይነት ታቦት የለንም ነው የሚለን ይሁን እንጂ የሕጉ ማደርያ መቅደሶቹ እኛ ስንሆን ታቦታችን ደግሞ ዛሬ በሐዲስ ኪዳን ኢየሱስ ነው ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እም ዕፅ ዘኢይነቅዝ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ትርጉም ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል ( ምንጭ ውዳሴ ማርያም ዘሰንበት ) 2ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 7 _ 11 ፤ ቆላስያስ 2 ፥ 17 ፤ ዕብራውያን 10 ፥ 1 ፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 3 ፥ 16 እና 17 ለ ) እንደገናም ከተጻፈው አትለፍ ተብለናል ከዚህም ሌላ የአምላካችሁን ቃል ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኳችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም ከእርሱም አታጎድሉም የሚሉትና የመሣሠሉት ቃሎች ስለተጻፉልን 1ኛ ቆሮንቶስ 4 ፥ 6 ፤ ዘዳግም 4 ፥ 2 ፤ የማቴዎስ ወንጌል 5 ፥ 19 ፤ ራዕይ 22 ፥ 19 እርግጥ ነው በሐዲስ ኪዳን ታቦት መሥራት የለብንም ታቦትን ሊሰሩ ለሚፈልጉም ታቦትን በተመለከተ ከተለያዩ የመጽሐፍቅዱስ ማስረጃዎቻችን አኳያ ለመስራት ማሰብም ሆነ መነሳት የለባቸውም ነው የምንላቸው ይሁን እንጂ ታቦት አላቸው ፣ ታቦት ሰርተዋል የተባሉ ሰዎች ቢኖሩም እንኳ በራሱ ታቦቱን የሰሩት በተጻፈው ቃል መሠረት ባለመሆኑ የያዙትም ሆነ የእኔ የሚሉትና የቀረጹት ታቦታቸው የሙሴን ሕግ የተከተለ ባለመሆኑ ትክክል አይደለም ታቦት እንስራ ብለው ቢያስቡ እንኳ መስራት ያለባቸው በተጻፈው ቃል መሠረት ባለመሆኑ ተግባሮቻቸውም ሆኑ ሥራዎቻቸው ከእግዚአብሔር ቃል የወጣ ነው የሚል ምላሽ ነው ያለን እንደገናም ይህንኑ እውነት ተከትሎ ማንኛውንም ነገር እንደ እግዚአብሐር ቃልና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሠረት ማድረግ እንዳለብን የእግዚአብሔር ቃል በግልጽነት ያስተምረናል ጌታ እግዚአብሔር በዚህ እውነት ይባርከን ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment