Monday, 22 May 2017

የቃል ኪዳኑ ታቦት ዛሬ አለ ወይ ? ስለ ቃልኪዳኑ ታቦት የአዋልድ መጻሕፍት ምን ይሉናል ? ድርሳነ ዑራኤልስ ? ...የቃል ኪዳኑ ታቦት ዛሬ አለ ወይ ? ስለ ቃልኪዳኑ ታቦት የአዋልድ መጻሕፍት ምን ይሉናል ? ድርሳነ ዑራኤልስ ? ክፍል አስራ አምስት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ በክፍል አስራ አራት ትምህርታችን ዛሬ የቃል ኪዳኑ ታቦት አለ ወይ ? ብለን ተነስተን ወደ መጽሐፍቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 113 በመሄድ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ሲያፈርስ ታቦቱ ያንጊዜ የጠፋ ይመስላል ምክንያቱም ዘሩባቤል በሠራው ቤተመቅደስ ውስጥ ታቦቱ አልነበረም የሚለውን ሃሳብ አንስተን ነበር የተነጋገርነው ይህ ብቻ አይደለም 2ኛ ነገሥት 25 ፥ 18 ን መጽሐፈ ዕዝራ 2 ፥ 1 ጀምሮ የተጻፈውንም በማንሳት ታቦቱ ከቤተመቅደስ ወጥቶ እንደነበረና በ607 ዓመተ ዓለም ገደማ ቤተመቅደሱ በፈራረሰበት ወቅት ይሄው ታቦት ከቤተመቅደሱ ወደ ባቢሎን ከተወሰዱት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ አይገኝም በኋላም ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሱት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥም ቢሆን አልተጠቀሰም በማለት በሰፊው ተማምረን ነበር ያለፍነው ነገር ግን ዛሬ ባቀረብኩት የክፍል አስራ አምስት ትምህርት የአዋልድ መጻሕፍቱም ሆኑ ድርሳነ ዑራኤል ከመጽሐፍቅዱሳችን በተለየ ሁኔታ የቃልኪዳኑ ታቦትም ሆነ እግዚአብሔር የሚገለገልበት ንዋየ ቅድሳቱ ጥቃቅኑና ትላልቁ ዕቃዎች በሙሉ ወደ ባቢሎን ለምርኮ የሄዱና በዚያውም የቀሩ መሆናቸውን ይጠቁማሉ መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ 1 ፥ 54 ፤ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል 9 ፥ 21 እና 22 ን መመልከት እንችላለን ከዚህም የተነሳ ነው እንግዲህ በድርሳነ ዑራኤል ዘሚያዝያ ገጽ 191 1985 ዓመተ ምሕረት ዕትም ላይ በግዕዙ ቃል ወአጥፍአ ማኅቶተ ብርሃንነ ወተመዝበረት ታቦተ ሕግነ እዝራኒ ርዕያ ወተናገራ ያለው ወደ አማርኛው ስተረጉመው የዓይናችን ብርሃን እንደጠፋና የእግዚአብሔር የሕጉ ማደርያ ጽዮን ታቦት እንደተማረከች አታይምን ? ሲል እዝራ አይቶ ተናገራት የሚለን ስለዚህ የመጽሐፍቅዱሱ መዝገበ ቃላት በነገረን መሠረት ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ሲያፈርስ ታቦቱ ያንጊዜ የጠፋ ይመስላል ከተባለ በመጽሐፍቅዱሳችን የማስረጃ ቃል መሠረትም ታቦቱ ወደ ባቢሎን ከሄዱትና ከተመለሱት ዝርዝር ዕቃዎች መካከል ከሌለ በአዋልድ መጻሕፍቱም ሆነ በድርሳነ ዑራኤል በተዘገበው ሃሳብ መሠረት ታቦቱ እንዴት ወደ ባቢሎን ተማርኮ በዚያው ሊቀር ቻለ ? እኛስ የትኛውን እንመን ? መጽሐፍቅዱሳችንን ? ወይንስ የአዋልድ መጻሕፍትንና ድርሳነ ዑራኤልን ? መልሱን በቀላሉ ለመመለስ እኛ ማመን ያለብን መጽሐፍቅዱሳችን ላይ የሠፈረልንንና የተጻፈልንን እውነት ነው ለምን ? ስንል መጽሐፍቅዱሳችን በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ ነው እንደገናም ይኸው የትንቢቱ የመጽሐፍ ቃል በሰው ፈቃድ ያልመጣ በመሆኑ ማንም ሰው ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደለትም 2ኛ ጴጥሮስ 1 ፥ 20 እና 21 በመሆኑም በእግዚአብሔር መንፈስ በተጻፈው ቅዱስ መጽሐፋችን ከልባችን ማመን ይገባናል ለምን ስንል መጽሐፉ አሁንም በሌላ ቦታ ከእርሱም አታጐድሉም በእርሱም ላይ አትጨምሩም ብሎናልና ዘዳግም 4 ፥ 2 ፤ ራዕይ 22 ፥ 18 እና 19 ስለዚህ በዚሁ በመጽሐፍ ቃል ላይ ጸንተን በመቆም ይህንኑ መጽሐፍቅዱሳችን የነገረንንና ሌሎችንም የተማማርናቸውን የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች ጨብጠን ለትውልዱ የእግዚአብሔር የሆነውን እውነት ማስተላለፍ ይጠበቅብናል የተማርነውን ቃል እንድንኖርበትና ለሌሎችም እንድናስተላልፈው እግዚአብሔር ይርዳን ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39 yonasasfaw8@gmail.com

No comments:

Post a Comment