የጾምና የጸሎት ጥሪ
ጽራህ ኀቤየ ወአወስአከ ወእነግር አቢያተ ወኃይላተ ዘኢተአምሩ
ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ
ነገርን አሳይሃለሁ
|
ትንቢተ ኤርምያስ 33 : 3
በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ አንድ አምላክ ስም አሜን
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰላም ለእናንተ ይሁን እንደምን ሰንብታችኋል
እግዚአብሔር ረድቶን የቃልኪዳኑ ታቦት በሚል አርዕስት የቃልኪዳኑ ታቦት ምስጢር ምን
እንደሆነና ዛሬ ላይ በሐዲስኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ መሆኑን በስፋት ተማምረናል
ይህንንም ትምህርት በእግዚአብሔር ጸጋ እንድናጠናቅቅና ከተሰጠውም ትምህርት
ተገቢ የሆነውን መንፈሳዊ እውቀት እንድንገበይ የረዳንን እግዚአብሔርን ከልብ
እናመሰግነዋለን በቀጣዩ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ሥዕል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ቤተክርስቲያን እንዴት ይታያል ? ሥዕል በቤተክርስቲያን እንዴት ተጀመረ ? የሚሉትንና
ሌሎችንም በሥዕል ዙርያ የተነገሩ ሃሳቦችን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እያየን
እንማማራለን በመቀጠል ግን ከዚህ በፊት በተማማርንባቸውም ይሁን ወደፊት
በምንማማራቸው መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶች ዙርያ እነዚህን የመሣሠሉ እውነተኛና
ቤተክርስቲያን እንዴት ይታያል ? ሥዕል በቤተክርስቲያን እንዴት ተጀመረ ? የሚሉትንና
ሌሎችንም በሥዕል ዙርያ የተነገሩ ሃሳቦችን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እያየን
እንማማራለን በመቀጠል ግን ከዚህ በፊት በተማማርንባቸውም ይሁን ወደፊት
በምንማማራቸው መጽሐፍቅዱሳዊ እውነቶች ዙርያ እነዚህን የመሣሠሉ እውነተኛና
መጽሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶች ሰርጸው በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት
የቤተክርስቲያኒቱን ሕይወትና ማንነት የሚለውጡበት ጊዜ እንዲሆን ጥንታዊትና
ሐዋርያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችንም በእነዚህ ቃሎች ተለውጣና በዚሁ
በእውነተኛው መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል እውነት ወደ ጥንተ መሠረቷ ተመልሳ
ወንጌልን ብቻ እንድትሰብክ በብርቱ ወደ እግዚአብሔር የምንጮህበትና የምንማልድበት
ጊዜ ይሆናል ይህ ጊዜ የሚሆነው በመደበኛው የትምህርት ፕሮግራማችን ሐሙስ ጁን 2
10 ሰዓት ላይ ነው መቅረት አይፈቀድም መጸለይ የምትፈልጉ ሁሉ በዚህ ፕሮግራም ላይ
ተገኝታችሁ መጸለይ የምትችሉ መሆናችሁንም ከወዲሁ እናስታውቃለን ከዚህም ሌላ
ጸሎት የሚያስፈልጋቸውና መጸለይም የሚፈልጉ ሁሉ የዚሁ ፕሮግራም እድምተኞች
እንዲሆኑ በመጋበዝ እንድትተባበሩን ከትልቅ አክብሮት ጋር እንጠይቃለን ጌታ
ዘመናችሁን ይባርክ
ጸ ጸ
ሎ ሎ
ት ት
ጸ
ሎ
ት
አቤቱ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ
ሰቆቃወ ኤርምያስ 5 ፥ 21
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
ከ Joshua Breakthrough Renewal Apostolic Ministry
ቀሲስ አባ ዮናስ ጌታነህ
http://www.Facebook.com/yonas.asfaw.39
yonasasfaw8@gmail.com
No comments:
Post a Comment